TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🥇ጉዳፍ - ወርቅ 🥈ለተሰንበት - ብር 🥉እጅጋየሁ - ነሃስ የኔዘርላንዷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ውድድሩን በአንደኝነት ለመጨረስ በተቃረበችበት ወቅት ወድቃ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆናለች። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ❤️ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የወርቅ ፣ ብር ፣ ነሃስ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች።

በሀንጋሪ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የስፖርት ባልደረባ ከላይ የተያያዙትን ፎቶዎች አድርሶናል።

More 👇
https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ❤️ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የወርቅ ፣ ብር ፣ ነሃስ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። በሀንጋሪ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የስፖርት ባልደረባ ከላይ የተያያዙትን ፎቶዎች አድርሶናል። More 👇 https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x @tikvahethiopia
" የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል " - ጉዳፍ ፀጋይ

የወርቅ አሸናፊዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከድሏ በኃላ ስለ ቡድን ስራ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ የተሰማትን ስሜት ተጠይቃ ተከታዩን ብላለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፦

" ተነጋግረን ነበር የገባነው።

ዋናው ነገር #ወርቁን ማምጣት ስለሆነ ተነጋግረን እኔ 16 እና 17 ፤ ከዛ ሁለት ዙር ሲቀር በራሳችንን አቅም መሄድ ነበርና ወርቁ ከራሳችን እንዳይወጣ ነበር ጥረት ስናደርግ የነበረው።

እግዚአብሔርም ሲጨመርበት ነውና ውጤት የሚያምረው የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል። "

ጉዳፍ ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው እግሯ እየደማ ሲሆን ይህ እንዴት እንደተፈጠረ ተጠይቃ መልሳለች።

" ሩጫ ላይ እንዲህ ያለው ነገር ያጋጥማል። በሩጫው መሃል ላይ ተነክቼ ነው እንደዛ የሆነው። 17 ወይም 18 ላልፍ አካባቢ ነው እግሬ የደማው " ብላለች።

ምናልባት ሲፋን ሀሰን ባትወድቅ ኖሮ ውጤቱ ይቀየር ነበር ? ተብላ ተጠይቃም መልሳለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፥

" እኔ እስከመጨረሻው ድረስ በጭራሽ እጅ አልሰጥም ብዬ ነው የገባሁት። ምክንያቱም እኔ ህዝቤ ይደግፈኛል ከሚገባው በላይ ፤ ወርቅ ማምጣት ምን ያህል እንደሆነ የህዝቡን ስሜት አይቻለሁ ፤ ከጎኔ ሆነው የሚደግፉኝ የኢትዮጵያ ህዝብ አሉና እነሱን ለማስደሰት ፣ ለራሴም ታሪክ ስለሆነ እስከመጨረሻው ተስፋ አልቆረጥኩም " ብላለች።

ሲፋን ሀሰን ምን አለች ?

በመጨረሻ ጥቂት ሰደንዶች ላይ ወድቃ ተሸናፊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን " ተገፍቼ ነበር " ስትል ቃሏል ለቢቢሲ ሰጥታለች።

" እሷ ወደ ውጭ እየሮጠች ነበር እናም ተዘግቶብኝ ነበር " ያለችው ሲፈን ፤ " ግን ምን ታደርጋለህ ስፖርት ነው፣ ሊከሰት ይችላል " ስትል ተናግራለች።

የመጨረሻውን ትንቅንቅ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://publielectoral.lat/+rbdEU4UaEdQxYWFk

የቪድዮ ባለቤት ፦ አረጋ ከፈለው
ፎቶ ፦ @tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የህዝባችን ፀሎት ሰምሯል " - ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ አሸናፊዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ከድሏ በኃላ ስለ ቡድን ስራ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ የተሰማትን ስሜት ተጠይቃ ተከታዩን ብላለች። ጉዳፍ ፀጋይ ፦ " ተነጋግረን ነበር የገባነው። ዋናው ነገር #ወርቁን ማምጣት ስለሆነ ተነጋግረን እኔ 16 እና 17 ፤ ከዛ ሁለት ዙር ሲቀር በራሳችንን አቅም መሄድ ነበርና ወርቁ ከራሳችን እንዳይወጣ ነበር ጥረት ስናደርግ…
" ውጤት የሚያስቀይር ስህተት የለም "

ከ10,000 ሜትር ሴቶች ውድድር በኃላ በሲፋን ሀሰን ጉዳይ የሀገሯ ሆላንድ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ዓለም አትሌቲክስ የዳኞች ቡድን ስለተፈጠረው ነገር ማረጋገጫ ለማግኘት ሄደው የነበረ  ቢሆንም ፤ ውጤት ሊያስቀይር የሚችል ስህተት እንደሌለ ተነግሯቸው መመለሳቸው ተሰምቷል።

Credit ፦  ሀይለ እግዚአብሔር አድሀኖም

More 👇
https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ምክንያቱ በግልፅ ይፋ ባልተደረገበት " ላልተወሰነ ጊዜ " የታገዱ በሞተር ስራ የሚተዳደሩ ዜጎች ቅሬታቸውን ገለፁ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን መጀመሪያ እስከ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም ማገዱ ፤ ከዛም በኃላ እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። በከተማዋ ሞተር ለምን እንደታገደ በቢሮው በኩል እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያም ይሁን…
እገዳው ተነሳ።

የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በሙሉ ከነገ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ተጨማሪ ተሳፋሪ ሳይጨምሩ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደሚቻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ከተፈቀደው የሰው መጫን አቅም በላይ በሚጭኑ ማህበራትና አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጿል።

አሽከርካሪዎችም ለትራፊክ አደጋ መንስኤ ከሆኑ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ የራስ ቆብ መከለያ (ሄልሜት) አለመጠቀም፣ ከወንጀል ድርጊት በመራቅና ወንጀል የሚፈጽሙ ሲያጋጥሙም ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ቢሮው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

ዛሬ በ2ኛው ቀን የቡዳፔሽት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን የሀገራችን ልጆች በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቁበት የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።

ተወዳዳሪዎቻችን እነማን ናቸው ?

- በሪሁ አረጋዊ ፣
- ሰለሞን ባረጋ ፣
- ይስማው ድሉ
- ታደሰ ወርቁ (ተጠባባቂ)

በወንዶች 10000ሜ ሀገራችን ወርቅ ያመጣችው በ2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር።

የዛሬ ምሽት ውድድሮች ከመጀመራቸው አስቀድሞ አረንጓዴውን ጓርፍ ያሳኩት አትሌቶቻችን (ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ለተሰንበት ግደይና እጅጋየሁ ታዬ) እንዲሁም አሰልጣኞች ሜዳሊያዎቻቸው ይረከባሉ።

ፎቶ ፦ የትላንት ምሽቱ አስደሳች ድል በቲክቫህ ኢትዮጵያ የስፖርት ባልደረባ ከሀንጋሪ - ቡዳፔሽት

ተጨማሪ መረጃዎችን በቲክቫህ ኢትዮጵያ - ስፖርት ይከታተሉ👇
https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia