TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በተጋጋሚ የታረመው /edit/ የተደረገው የመንግስት ሰራተኛው ህልፈተ ህይወት !

የአብክመ መሬት ቢሮ ባልደረባ የሆነ ወጣት ባየ በዛ ትናንት ምሸት ታህሳስ 22/2015 ባህር ዳር ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የሰራተኛውን ህልፈት በተመለከተ ግን የሚሰራበት ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰራጨው መረጃ አወዛጋቢ ሆኖ ተገኝቷል።

ቢሮው በቅድሚያ ባልደረባው " ባልታወቀ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ብሎ የገለፀ ሲሆን በኃላ ቆየት ብሎ " ባልታወቁ አካላት ጥቃት በደረሰበት ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ሲል አስተካክሏል።

ቆየት ብሎ ቢሮው ባልደረባው  "በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ብሏል። ከዚህ ማስተካከያ በኃላም " የትራፊክ አድራሹ መሰወሩን ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ባህር ዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብሏል።

በ45 ደቂቃዎች በፊት ደግሞ በአስተያት መስጫው ላይ ቢሮው ባልደረባው በትራፊክ አደጋ መሞቱን አረጋግጣለሁ ሲል ፅፏል።

በመጨረሻም ቢሮው መረጃውን ከገፁ ላይ ሙሉ በሙሉ አጥፍቶታል።

እንዴት አንድ ተቋም የራሱ የባልደረባውን ህልፈት በተመለከት አጠራጣሪ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ለህዝብ ያሰራጫል ?

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamily በትላንትናው ዕለት የ2ኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍትና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ዘመቻ መካሄድ ጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር በጥቂት ቀናት 7 ሺህ በላይ መፅሀፍትና 3 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር መሰብሰቡና በአማራ ክልልና በደቡብ ክልል ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ በአዲስ አበባ ላለ የህዝብ ቤተመፅሀፍ መከፋፈሉ ይታወሳል። በዚህኛው ዙር በመፅሀፍት ደረጃ ከ30 ሺህ በላይ ለመሰብሰብ ታስቧል። በዚህ ዙር…
#ምስጋና

በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም)

ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል።

የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው።

ስራው ከመፅሀፍ ባለፈ የትምህርት መሳሪያዎችን ያካተተ ሲሆን ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ #ከየቤተሰቦቻችን መኖሪያ አካባቢ በመሄድ የተሰበሰቡ ፦

ትላንት ቅዳሜ ፦

- አቶ ዳንኤል ቦጋለ ከልጃቸው ነብዩ ዳንኤልና ከመላ ቤተሰባቸው ጋር መደበኛ መፅሀፍት 58 ፣ አጋዥ 2 ፣ የህፃናት 2 ፣ ልብወለደ 1 ፣ የግል ት/ቤት 11 መፅሀፍት አበርክተዋል።

- ወ/ሮ ኑሪያ አደም ከልጆቻቸው ሲያ አህመዝ ፣ ሀናን አህመድ፣ ረምላ አህመድ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 9 አጋዥ መፅሀፍት ፣ መዝገበ ቃላት 3 ፣ መደበኛ 19 መፅሀፍት እና አንድ ሞኒተር አበርክተዋል።

- ወ/ሮ ሰብለ ተሾመ ከልጆቻቸው በረከት ፍስሃ፣ በእምነት ፍስሃ፣ በፍቅር ፍስሃ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 38 መደበኛ መፅሀፍ 5 አጋዥ መፅሀፍ አበርክተዋል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የ5 ሺህ ብር 106 መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።

- ዶ/ር አለማየሁ ሀብተገብርኤል ከልጆቻቸው ቤተልሄም ፣ መክሊት፣ ዳግማዊት እና በመላው ቤተሰባቸው ስም አንድ #ከለር_ፕሪንተር እና #ሞኒተር አበርክተዋል።

#ይቀጥላል
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምስጋና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም) ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል። የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው። ስራው ከመፅሀፍ…
#የቀጠለ

ዛሬ እሁድ፦

- ካሌብ ጌትነት 10 መደበኛ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘሚል ሀሰን እና አቶ አብድላዚዝ አህመድ ከልጃቸው ነሂማ አብድላዚዝ መሀመድ ጋር 31 መደበኛ መፅሀፍ ፣ 2 የግል ት/ቤት መፅሀፍ አበርክተዋል።

- መቅደስ ደረጀ መደበኛ 55 መፅሀፍ አበርክታለች።

- ናታን ደመቀ 8 አዲስ አጋዥ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬ ከልጆቻቸው ፀጋ ተመስገን፣ ሜሎና ተመስገን፣ ናርዶስ ተመስገን ጋር በመላው ቤተሰባቸው ስም 7060 ብር ወጪ አድርገው 45 መፅሀፍ ገዝተው አስረክበዋል።

- ወ/ሮ ህይወት እንድርያስ ከልጃቸው ቤዛዊት ነጋሽ ጋር 10 አጋዥ ፣ 3 መደበኛ መፅሀፍ አስረክበዋል።

- ሀዊ ጨምዴሳ 20 አጋዥ መፅሀፍት፣ 34 መደበኛ መፅሀፍት አስረክባለች።

- ወ/ሮ ፀጋ ለማ፣ ከልጆቻቸው በእምነት ወንደሰን፣ ያሬድ ወንደሰን እና እድላዊት ወንደሰን 25 መደበኛ እና 5 አጋዥ መፀሀፍት አበርክተዋል።

- አሚር መኑር 48 አጋዥ ፣ 14 መደበኛ መፅሀፍ አበርክቷል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል ከለቡ 28 መደበኛ መፅሀፍት ፣ 29 አጋዥ መፅሀፍት፣ 4 ልብወለድ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ኤግዞም የፋርማሲ እቃዎች አከፋፋይ 3000 ብር ወጪ የሆነባቸው መፅሀፍት አስረክቧል።

- አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል የ2000 ብር መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።

ሁላችሁንም ቤተሰቦቻችንን እናመሰግናለን።

በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

የትላንት ቅዳሜ እና የዛሬ እሁድ #ድምር ብቻ ፦

👉 1,089 መፅሀፍት
👉 2 ላፕቶፕ
👉 2 ሞኒተር
👉 1 ፕሪንተር

#አዲስ_አበባ

#ይቀጥላል
TIKVAH-ETHIOPIA
#የቀጠለ ዛሬ እሁድ፦ - ካሌብ ጌትነት 10 መደበኛ መፅሀፍት አበርክቷል። - ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘሚል ሀሰን እና አቶ አብድላዚዝ አህመድ ከልጃቸው ነሂማ አብድላዚዝ መሀመድ ጋር 31 መደበኛ መፅሀፍ ፣ 2 የግል ት/ቤት መፅሀፍ አበርክተዋል። - መቅደስ ደረጀ መደበኛ 55 መፅሀፍ አበርክታለች። - ናታን ደመቀ 8 አዲስ አጋዥ መፅሀፍት አበርክቷል። - ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬ ከልጆቻቸው ፀጋ ተመስገን፣ ሜሎና…
#የቀጠለ

የዚህ ሳምንት (የቅዳሜ እና እሁድ) ስራ በዚህ በስኬት ያበቃ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ በየአካባቢያችሁ እንመጣለን።

ምን መስጠት ይቻላል ?

👉 ከ9 - 12 ማንኛውም መፅሀፍ
👉 ከ1 - 8 #አጋዥ ብቻ (መደበኛው ስለተቀየረ)
👉 ያገለገለ ማንኛውም ኮምፒዩተር / ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ታብሌት
👉 ፕሪንተር
👉 የፕሪንተር ቀለም
👉 ነጭ ወረቀት

ዘመቻው ሲጠናቀቅ ከሌሎች ቁሳቁሶች ውጭ ከ30,000 እስከ 40,000 መፅሀፍ ለመሰባሰብ ታቅዷል። ሁሉም መፅሀፍት እና ቁሳቁስ በጦርነት የተጎዱ ት/ቤቶችን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ይከፋፈላሉ።

ውድ ቤተሰቦችቻን መፅሀፍ እና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁስ ለማስረከብ በ 0919743630 ላይ ደውሉልን / @tikvahethiopiaBOT ላይ ፃፉልን።

የትም መሄድ ሳይጠበቀባችሁ በየደጃፋችሁ መጥተን እንቀበላችኃለን።

ማሳሰቢያ ፦ በገንዘብ የሚደረግ ማንኛውም ድጋፍ ተቀባይነት የለውም።

#5ኛው_ዓመት_የመማሪያ_ቁሳቁስ_ማሰባሰብ_ስራ #2ኛውዙር

#AddisAbaba
#TikvahFamily

@tikvahethiopia
" በእሳት አደጋው 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ውድሟል "

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ገልጿል።

ኮሚሽኑ አደጋው ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ መድረሱን አመልክቷል።

በገበያ ማዕከሉ ከሚገኙ 1 ሺ 600 ሱቆች ውስጥ 84 የሚሆኑት ላይ የእሳት አደጋው የደረሰ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት 1 ሺህ 516 የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ማትረፍ (500 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት) መቻሉን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በሰጠው መረጃ ፦

- አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እና 95 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው ነበር።

- አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 4 ሰዓት 28 ደቂቃ ወስዷል።

- በአደጋው እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

- የአደጋ መንስኤ እየተጣራ ነው።

- የሾላ የገበያ ማዕከል በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ የገበያ ማዕከላት ውስጥ አንዱ ነው።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ድሬድዋ

የኮንቴይነር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠጥ ላይ የሚገኘው የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ በድሬዳዋ ተጨማሪ የጭነት አገልግሎት የሚሰጥበት ጣቢያ መከፈቱን አሳውቋል።

ጣቢያው ፤ ደንበኞች ያላቸውን ጭነት በፈለጉት ቦታና ሰዓት ለማድረስ የሚስችል ተጨማሪ አማራጭ በመሆን  ያገለግላል ብሏል።

የኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ፤ የባቡር ኮንቴይነሮች የጭነት አገልግሎት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ ዋና ዋና ከተሞች መካከል በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ የተጀመረው የጭነት አገልግሎት አሁን ካሉት ዋና ዋና የእቃ ማጓጓዣ ጣቢያዎች ማለትም፦
- እንዶዴ፣
- ሞጆ፣
- አዳማ
- ናጋድ ጣቢያ በተጨማሪ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ " በድሬዳዋ ባቡር ጣቢያ የተጀመረው የጭነት አገልግሎት የጅምላ ጭነት ማጓጓዝ ለሚፈልጉ ደንበኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ወደሚፈልጉት የሀገሪቱ ክፍል ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው " ያለ ሲሆን ዋጋ በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብሏል።

#EDR

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ጉምሩክ ኮሚሽን በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት "  ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ፤ በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት " ውስጥ ተደብቀው የገቡ ፦

👉 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ፣
👉 ሀርዲስኮች
👉 ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ፦

- የኤክትሮኒክስ እቃዎቹ (ላፕቶፕ፣ ሀርድዲስክ፣...) የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሲስተም ዩኒት ውስጡን ባዶ በማድረግ የገቡ ናቸው።

-  በተገኘ የፍተሻ ውጤት ሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።

- የተፈፀመዉ #የንግድ_ማጭበርበር ተግባር  በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፤ ምርመራም እየተጣራበት ነው።

- በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ ተሰጥቷል።

መረጃው ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia