ፎቶ ፦ ጉምሩክ ኮሚሽን በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት " ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።
ኮሚሽኑ ፤ በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት " ውስጥ ተደብቀው የገቡ ፦
👉 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ፣
👉 ሀርዲስኮች
👉 ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገልጿል።
ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ፦
- የኤክትሮኒክስ እቃዎቹ (ላፕቶፕ፣ ሀርድዲስክ፣...) የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሲስተም ዩኒት ውስጡን ባዶ በማድረግ የገቡ ናቸው።
- በተገኘ የፍተሻ ውጤት ሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።
- የተፈፀመዉ #የንግድ_ማጭበርበር ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፤ ምርመራም እየተጣራበት ነው።
- በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ ተሰጥቷል።
መረጃው ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia