TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ለግብፅ እና ሱዳን ! ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " ...የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ ለሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ እኛ ኃይል በማመንጨት ኢኮኖሚያችንን የማሻሻል በጭለማ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ብርሃን እንዲያገኙ ከመፈለግ ውጭ እነሱን የመግፋት፤ የመጉዳት ዓላማ እንደሌለን በተደጋጋሚ ገልፀናል። ዘንድሮ ሶስተኛው ሙሊት ያረጋገጠው 22 ቢሊየን ገደማ ሜትር ኪዩቢክ ውሃ መያዝ የሚያስችል ስራ እንዲሁም…
#የምስራች🎉

የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡

በግድቡ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችም የደስታ ስሜታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከለውጡ በኋላ በፕሮጀክቱ ላይ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ስራዎች ተጠናቀው የግድቡን የመካከለኛው ክፍል ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ ስድስት መቶ ሜትር እንዲሁም ግራና ቀኙን ስድስት መቶ አስራ አንድ ሜትር ማድረስ መቻሉን ገልጿል።

ከሶስት ዓመት በፊት ለዘመናት ከባህር ጠለል በላይ በአምስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ይፈስ የነበረው የአባይ ወንዝ ዛሬ ለሦስተኛ ዙር በግድቡ አናት ላይ የፈሰሰው ከባህር ጠለል በላይ በስድስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት የግድቡ ግራና ቀኝ ጠርዝ ከባህር ጠለል በላይ ስድስት መቶ አርባ አምስት ሜትር የደረሰ ሲሆን የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 % ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ፍብረካና ተከላ 61 % እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራ 73 % ፣ አጠቃላይ አፈፃፀሙ ደግሞ 83 ነጥብ 3 % ደርሷል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፍታ ከመሬት 145 ሜትር ሲሆን ርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡

የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ ላይ 130 ሜትር፥ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ነው።

በበጀት ዓመቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ2 ዩኒት ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ለማድረግ የያዘው እቅድ ተሳክቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የምስራች🎉 የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡ በግድቡ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችም የደስታ ስሜታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከለውጡ በኋላ በፕሮጀክቱ ላይ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ስራዎች ተጠናቀው የግድቡን የመካከለኛው ክፍል ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ…
#BREAKING

ሶስተኛው ዙር ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ።

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር ሙሌት በስኬት ተጠናቆ ውሃ በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግድቡን ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ለማብሰር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኘታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለግብፅ እና ሱዳን ! ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " ...የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ ለሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ እኛ ኃይል በማመንጨት ኢኮኖሚያችንን የማሻሻል በጭለማ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ብርሃን እንዲያገኙ ከመፈለግ ውጭ እነሱን የመግፋት፤ የመጉዳት ዓላማ እንደሌለን በተደጋጋሚ ገልፀናል። ዘንድሮ ሶስተኛው ሙሊት ያረጋገጠው 22 ቢሊየን ገደማ ሜትር ኪዩቢክ ውሃ መያዝ የሚያስችል ስራ እንዲሁም…
ለሱዳን እና ግብፅ !

ዛሬ በጉባ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በተዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት ፦

" ... 85 ፐርሰንቱን የአባይ ውሃ Contribute ስናደርግ ቆይተን ላለፉት ዘመናት ሳንጠቀም መቆየታችን #የሚያስቆጭ ቢሆንም አሁን መልካም ጅምር በመታየቱ የሚገባንን ተጠቅመን ፤ የሚገባቸውን ለወንድሞቻችን ሰጥተን በጋራ ለማደግ በእኛ በኩል ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ እገልፃለሁ "

@tikvahethiopia
" የቦነስ እና የደሞዝ እርከን ጭማሪ ተፈቅዷል " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ እና ከባንኩ ጋር ለሚሠሩ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሠራተኞች ቦነስ እና የደሞዝ እርከን ጭማሪ መፍቀዱን አስታወቀ።

ይህ የቦነስ እና የደሞዝ ጭማሪ የተፈቀደው ባንኩ በ2014 (2021/22) በጀት ዓመት አመርቂ ውጤት በማስመዝገቡ ምስጋና ለማቅረብ እና በአዲሱ በጀት ዓመት ከእስካሁኑ የላቀ ስኬትን ሰራተኞች እንዲያስመዘግቡ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከእቅድ አንጻር የ114.4 በመቶ አፈፃፀም በማስመዝገብ 27.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውሷል።

@tikvahethiopia
" እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል "

ወንጀል የሚፈፅሙበትን ቦታ ቀድመው አይተውና መርጠው ከጨረሱ በኋላ የራይድ ተጠቃሚ መስለው ደውለው በመጥራት የመኪናውን አሽከርካሪ በመግደል መኪናውንና ስልኩን ይዘው የተሰወሩት ግለሰቦች በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጡ።

ጉዳዩ እንዲህ ነው፦

1ኛ ተከሳሽ የአብስራ ሰለሞን እና 2ኛ ተከሳሽ በላይነው ንጉስ ካልተያዘው ግብረ-አበራቸው ጋር በመሆን ነሃሴ 6/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ራይድ ደውለው አሽከርካሪውን በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል የሰዎች እንቅስቃሴ ወደማይበዛበት ገባ ያለ ቦታ ይጠራሉ።

ሆራ ትራዲንግ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሲደርሱ 2ኛ ተከሳሽና ያለተያዘው ግብረ-አበራቸው አሽከርካሪ ንጉስ ከፍያለውን አንገቱን አንቀው በመያዝ ወንበር ስር ሲያስተኙት 1ኛ ተከሳሽም መኪውን እየነዳ ሟችን ወደኋላ በመዞር በተደጋጋሚ በጩቤ ሆዱ ላይ በርካታ ቦታ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል።

በኃላም የሟችን ቪትዝ መኪና፣ የሞባይል ስልክና ያደረገውን ጫማ አጠቃላይ ድምሩ 758,250 ብር የሚያወጣ ንብረት ወስደው ይሰወራሉ።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግ ቆይቶ በፈፀሙት ከባድ ውንብድና ወንጀል በፍትሕ ሚኒስቴር ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ተከሳሾች ክሱ ፍ/ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈፀምንም በማለት ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረብ አስረድቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ችሎትም የዐቃቤ ህግና ተከሳሾችን ክርክር ሲከታተል ከቆየ በኋላ ተከሳሾች ጥፋተኛ ናቸው በማለት እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

#ፍትህሚኒስቴር

@tikvahethiopia
ከስራ ቦታ እንደወጡ ያልተመለሱት አቶ ኢብራሂም በያን !

በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ፣ ቀበሌ 04 ነዋሪ እና የሐጂ መሐመድ ሪል ስቴት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢብራሂም በያን ሠይድ መጋቢት 29/2014 ከሥራ ቦታ እንደወጡ እስከአሁን አለመመለሳቸውን ፤ የት እንዳሉም እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

በወቅቱ አቶ ኢብራሂም ከሥራ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ የስልክ ግንኙነት እንደነበራቸው የገለፁት ቤተሰቦቻቸው ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ግን የስልክ ግንኙነቱ መቋረጡን፤ የስልክ ግንኙነቱ ሲቋረጥም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው #ጀርመን_አደባባይ አካባቢ እንደነበሩን አታውሰዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ትራፊክ ጽ/ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ጠይቀውም ምንም ፍንጭ ባለማግኘታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳመለከቱ የገለጹት የአቶ ኢብራሂም ወንድም አብዱልሀዲ በያን እና የቅርብ ቤተሰባቸው ሩቅያ ሀሰን በወቅቱ ጉዳዩን መዝግቦ መርማሪ በመመደብ ተከታትሎ እንደሚያሳውቋቸው ፖሊስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ቢሆንም ግን ከመጋቢት 29 ቀን 2014 እስከ ዛሬ ምንም አይነት መፍትሄ እንዳልተገኘ አስረድተዋል።

አቶ ኢብራሂም ለረጅም ጊዜያት በመጥፋታቸውና ያሉበት ቦታ ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አሁንም ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

የኢብራሂም ቤተሰቦች አቶ ኢብራሂምን ያየ ወይንም ያሉበትን ቦታ የሚያውቅ በስልክ 0911149306፣ 0911616199 ፣ 0911438549 ላይ በመደወል እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🙏

ከ5ኛው ዓመት የቀጠለው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናክሯል።

የተለያዩ መማሪያ መፅሀፍትን ማበርከት የምትፈልጉ የቤተሰቦቻችን ለተጨማሪ መረጃ 👇
t.me/TikvahUniversity/4671?single
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #Update ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ። ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ…
#ችሎት

ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ በባንክ ሂሳባቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያንቀሳቀሱ ተጠርጣሪ ባለሙያዎች መኖራቸውን ፖሊስ ገለጸ።

ፖሊስ ይህን የገለፀው ተጠርጣሪዎቹን ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበበት ወቅት ነው።

በጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ (ኮንዶሚኒዬም) ዕጣ ከህግ ውጪ ግለሰቦች እንዲካተቱ አድርገዋል ተብለው ከተጠረጠሩ ከ8 የሶፍትዌር ባለሙያዎች መካከል በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤት ገልጿል።

ቤት ድረስ እየተኬደ በዕጣው የሚገባው ሰው ገንዘብ ይከፍል እንደነበርና ደላላ ተቋቁሞ ከባለሙያ ጋር እየተገናኙ በዕጣው እንዲካተቱ የተደረጉ ግለሰቦች ነበሩ ሲል ፖሊስ ለፍ/ ቤት አስረድቷል። 

በተጨማሪም ፖሊስ ሶፍትዌሩን ካለሙት ባለሙያዎች መካከል ሲስተሙ የማልማት ተግባር በተከናወነበት ጊዜያት ብቻ #በሚስቶቻቸው ሂሳብ ውስጥ በርካታ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሂሳባቸው ያቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎችም እንደነበሩ ማስረጃ ማግኘቱን ጠቅሶ ለችሎት አስረድቷል።

(Credit : Journalist Tarik Adugna)

ያንብቡ :
https://telegra.ph/Condominium-08-12-2
TIKVAH-ETHIOPIA
ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች ! ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል። በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች። የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦ 🥇6 ወርቅ፣ 🥈5 ብር 🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

በካሊ በተደረገው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና #ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ አዳሩን ስካይ ላይት ያደርጋል።

ነገ ከማለዳው አንድ ሰዓት ከ30 ጀምሮ ከስካይ ላይት ሆቴል በመነሳት በፓትሮልና በሲቲ ቱር ባሶች ታጅቦ በአዲስ አበባ ከተማ የተመረጡ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ዜጎችን “ እንኳን ደስ አላችሁ ” እንደሚሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

በዕለቱም በስካይ ላይት የማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

በ19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ6 ወርቅ፣5 የብር እና1 የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሜሪካና ጃማይካን ተከትላ ሶስተኛ መውጣቷ ይታወሳል።

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#KenyaElection🇰🇪 የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ? ኬንያ እያካሄደች ያለችውን 5ኛው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ይገኛሉ። 🇪🇹 አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገውን 'ብሬንትረስት ፋውንዴሽን'ን በመወከል ምርጫውን እየታዘቡ ናቸው። አቶ ኃይለማርያም…
#Kenya🇰🇪

የኬንያ ምርጫ ውጤት ከምን ደረሰ ?

ጎረቤት ሀገር #ኬንያ ከቀናት በፊት ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳደረገች ይታወቃል።

እስካሁን ድረስ የምርጫው አሸናፊ አልታወቀም። ቆጠራውም አልተጠናቀቀም።

የውጤት ቆጠራው ምርጫው ከተጠናቀቀበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ እየተካሄድ ይገኛል።

እስካሁን ያለው ውጤት ከላይ ተያይዟል።

ከላይ በምስሉ ላይ የተያያዘው የምርጫ ውጤት የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ክፍል ምርጫውን ከሚያስፈጽመው ኮሚሽን ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ዋቢ አደርጎ ያሰራጨው ነው።

@tikvahethiopia