TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ለዩትዩብ (YouTube) ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ፦ " ...በዳይስፖራ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ሚዲያዎች ለዩትዩብ ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው። ተመልከቱ ሀገር ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር እነኚህ ጦርነቶች ካልቆሙ ሩዋንዳን የሚያስንቅ ፣ ሶሪያን የሚያስንቅ በጣም…
" ለሰላም መስፈን የምንሰራው ስራ ይቀጥላል " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በአውሮፓ ሀገራት እና በሰሞን አሜሪካ ሲያካሂዱት የነበረውን " Galatoomaa Tour " ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል።

አቶ ጃዋር መሀመድ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ ሀገራቸው በሰላም መመለሳቸውን ዛሬ አሳውቀዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ በተለያዩ ከተሞች በነበሩ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ለተካፈሉ ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት ገልፀው ለሰላም መስፈን የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፤ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ የመከሩ ሲሆን በእስር ቤት ቆይታቸው ድምፅ ለሆኗቸው፣ አብረዋቸው ለነበሩ " ምስጋና " አቅርበዋል።

ከማህበረሰቡም ዘንድ ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎችም መልስ ሲሰጡ ቆይተዋል።

በተለይም በየመድረኩ ላይ በተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ስለ ጦርነት ማቆም፣ ስለ ሰላም እና ድርድር አስፈላጊነት ፅኑ አቋማቸውን በተደጋጋሚ አስረግጠው ተናግረዋል።

ሚዲያዎችም እንዲሁም ደግሞ ከኢትዮጵያ ርቀው በውጭ ሀገር ያሉ ሰዎች በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዳይኖርና በቀጣይ የማያባራ እልቂት እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም በማሳሰብ ለሀገሪቱ ህዝብ ሲሉ በ #ሰላም ጉዳይ አበክረው እንዲሰሩ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር።

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና የፋይናንስ ሴክተሯ !

በ2014 በጀት ዓመት ማለቂያ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር እውነታዎች ፦

• የባንኮች ብዛት 👉 30

• የባንክ ቅርንጫፎች ብዛት 👉 8,944

• ጠቅላላ የባንኮች ካፒታል (በብር) 👉 199.1 ቢሊዮን ብር

• ጠቅላላ የባንኮች ሀብት (በብር) 👉 2.4 ትሪሊዮን ብር

• ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ (በብር) 👉 1.7 ትሪሊዮን ብር

• የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 16.3 ሚሊዮን

• የዴቢት ካርድ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 30.7 ሚሊዮን

• የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 43.3 ሚሊዮን

• የኤቲኤሞች (ATM) ብዛት 👉 6,902

• የፖስ ብዛት 👉 11,760

• የኢንሹራንስ ተቋማት ብዛት 👉 18

• የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብዛት 👉 40

መረጃ ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#BREAKING

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን መሆኑን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች…
#Update

" ሶስተኛው የግድቡ ሙሌት በሂደት ላይ ይገኛል " - ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ

ዛሬ የ2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጫ ማብሰሪያ ስነስርዓት ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ከተናገሩት ፦

" ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ በያዝነው ዓመት በ2014 ለማከናወን ከተያዙ አብይ እቅዶች መካከል በሁለት ዩኒት ማለትም በሁለት ታርባይንና ጀነሬተሮች ኃይል ማመንጨት አንዱ ሲሆን ይህ እቅድ ተሳክቶ በ2ቱም ዩኒቶች ኃይል ማመንጨት ተችሏል።

ከለውጡ በኃላ በፕሮጀክቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ከተወሰደ በሶስት ዓመታት ውስጥ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታብረት ስራዎችን በማጠናቀቅ የመካከለኛውን የግድብ ከፍታ ከሃያ አምስት ሜትር ወደ መቶ ሜትር ማድረስ ተችሏል።

እንደዚሁም የግድቡን ግራና ቀኝ በትንሹ እስከ ስድስት አርባ አምስት የደረሰም አለ ወይም ከባህር ጠለል በላይ እስከ ስድስት አርባ አምስት ወይም መቶ አርባ አምስት ሜትር ከመሰረት ከፍ ያለ በተጨማሪ በትንሹ እስከ መቶ አስራ አንድ ሜትር ከፍ በማድረግ ሁለት ሙሊቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን #ሶስተኛው_ሙሊት_በሂደት ላይ ይገኛል ።

ከምንም ደረጃ ተነስቶ ሁለት ተርባይኖች እና ጄነሬተሮች በመትከል ኃይል ማመንጨት ተችሏል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ " ክላስተር " አደረጃጀትን ባለማጽድቅ ብቸኛ የሆነው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሐሙስ ነሐሴ 5/2014 እንደሚያካሂድ ተገልጿል። የአስቸኳይ ጉባኤውን መጠራት የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ እንዳረጋገጡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል። ድረገፁ አነጋግሬያቸዋለሁ ያላቸው ሶስት የጉራጌ ዞን ምክር…
#Update

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል።

የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብን 52 የምክር ቤት አባላት ተቃውመታል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 97 አባላት ያሉት ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ 91 ያህሉ ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ምክር ቤቱን የተቀላቀሉ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ስድስት አባላት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ተመራጮች ናቸው።

ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 5 ቀን 2014 በተካሄደው የዞኑ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ከተገኙ 92 የምክር ቤት አባላት መካከል 40ዎቹ ውሳኔውን ደግፈው ድምጽ መስጠታቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል። የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው…
#ተጨማሪ

" መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል።

የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን #ብቸኛው ሆኗል።

ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። 

ፎቶ ፦ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ " መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል። የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ…
#GurageZone

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ በክልል የመደራጀት ውሳኔን ማፅናቱና የክላስተር አደረጃጀቱን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ መሆኑን ደስታውን ሲገልጽ ግን በሰላማዊ መንገድ መሆን እንዳለበት በዞኑ የተቋቋመው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳስቧል።

ኮማንድ ፖስቱ ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ ፤ የጉራጌ ዞን ም/ቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብን በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ማድረጉን ገልፀው ምክር ቤቱ በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን ሲገልጽ በሰላማዊ መንገድ መሆን አለበት ብለዋል።

የዞኑ ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

በቀጣይ የዞኑ ም/ቤት ያጸደቀው በክልል የመደራጀት ውሳኔ መንግስት ምላሽ እስኪሰጥበት ድረስ የዞኑ ህዝብ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

በተጨማሪ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ፤ የዞኑ ምክር ቤት የክላስተር አደረጃጀትን በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ መንግስት በቀጣይ አቅጣጫ እስኪያስቀምጥ እና ውሳኔ እስኪሰጥ የዞኑ ህዝብ ሰላሙን በመጠበቅ በልማት ስራው ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው ከዞኑ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ሶስተኛው የግድቡ ሙሌት በሂደት ላይ ይገኛል " - ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ዛሬ የ2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጫ ማብሰሪያ ስነስርዓት ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሀሮ ከተናገሩት ፦ " ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ በያዝነው ዓመት በ2014 ለማከናወን ከተያዙ አብይ እቅዶች መካከል በሁለት ዩኒት ማለትም በሁለት ታርባይንና ጀነሬተሮች ኃይል ማመንጨት አንዱ ሲሆን ይህ…
ለግብፅ እና ሱዳን !

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ...የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ ለሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ እኛ ኃይል በማመንጨት ኢኮኖሚያችንን የማሻሻል በጭለማ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ብርሃን እንዲያገኙ ከመፈለግ ውጭ እነሱን የመግፋት፤ የመጉዳት ዓላማ እንደሌለን በተደጋጋሚ ገልፀናል።

ዘንድሮ ሶስተኛው ሙሊት ያረጋገጠው 22 ቢሊየን ገደማ ሜትር ኪዩቢክ ውሃ መያዝ የሚያስችል ስራ እንዲሁም 2 ሁኒት ጀነሬት ማድረግ የሚያስችል ስራ ቢሰራም በታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም አይነት የውሃ እጥረት እንዳያጋጥም ኢነርጂ ጀነሬት እያደረግን ከዚያ ባሻገር Bottom outlet የሚባለው ከውጭ የሚታየው በከፍተኛ ግፊት የሚሄደው ውሃ አንድም ቀን ሳይቋረጥ እንዲሄድ የተደረገበት ዋነኛው አላማ ሌሎች ወንድሞቻችንን የመጉዳት ሳይሆን እኛ የመጠቀም፤ የማደግ ፍላጎት ስላለን ያንን በተግባር ለማሳየት ነው።

ይህ እየፈሰሰ ያለው ውሃ ቢገደብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ውሃ ሊይዝ ይችላል።

ለእነሱ የሚገባቸውን እየለቀቅን እኛ በረዘመ ጊዜ ውስጥ ውሃ የምንይዘው እነሱም ሳይጎዱ እኛም ሳንጎዳ በጋራ ለመበልፀግ፣ ለማደግ ካለን ፍላጎት መሆኑን ተገንዝበው የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በንግግር፣ በድርድር ፣ በስምምነት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ከልብ አምነው ለዛ እንዲተጉ ፤ ከዛ ውጭ ያለው ማንኛውም አማራጭ የጀመርነውን ነገር የማያስቆም፣ እንዲሁም በከንቱ የሚያደክም መሆኑን ተገንዝበው ወደ ሰላም፣ ወደ ድርድር በጋራ ወደ ማደግ እንዲመጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ "

🇪🇹 የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁናዊ ሁኔታ 🇪🇹

👉 የሲቪል ስራዎች ግንባታ 95 % ደርሷል።

👉 አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 83 ነጥብ 3 % ደርሷል።

👉 አጠቃላይ ስራውን በቀጣይ 2 አመት ተኩል ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።

@tikvahethiopia
#ደምቢ_ዶሎ

• " በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ

• " እንዲህ አይነት ክስተት የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው " - ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ማስተማሪያ ሆስፒታል 2 ጭንቅላት ያለው ህፃን ተወለደ።

የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ በሰጡት ማብራሪያ ህፃኑ ሁለት ጭንቅላት ኖሮት መወለዱን ተናግረዋል።

ዶ/ር ፀጋዬ ፤ በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለፅም ህፃኑ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወለዱን አስረድተዋል።

በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ እና በእናቶች ማህፀን ውስጥ በሚስተናገዱ እንቁላሎች ብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ አብራርተዋል።

በኢኒስቲትዩቱ የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ በበኩላቸው ክስተቱ በመንታ ምድብ የሚመደብ እና የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ እናትም ሕፃኑም #በጥሩ_ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#WeCare

ከፍተኛ የስኳር መጠን እየወሰዱ እንደሆነ የሚያሳዩ 7 አደገኛ ምልክቶች !!

@WecareET የስልክ መተግበሪያ ስመጥር እና የ አመታት ልምድ ያላቸው ሐኪሞችን በቀላሉ ካሉበት ቦታ ሁነው ማማከር የሚችሉበት መተግበሪያ ነው።

ዛሬውኑ ይሞክሩት ! መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን 👨🏽‍⚕️👩‍⚕️ ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።