TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#OromiaRegion ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ። በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ…
ሰኔ 11 በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት ከተገደሉት ንፁሃን ህፃናት በተጨማሪ ወላጆቻቸውን ተነጥቀው ወላጅ አልባ የሆኑ በርካታ ህፃናት ስለመኖራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

40 ወላጅ አልባ ህፃናት መስጅድ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል።

በቶሌ ቀበሌ ቢላል መስጂድ ውስጥ የሚያገለግሉት ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ኢማም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " ወላጅ አልባ ሆነው የተቀመጡት ከ2 ዓመት እስከ 5 ዓመት ያሉ ናቸው። እስከ አርባ ይደርሳሉ " ብለዋል።

" ምንም የሚበላ ነገር የለም " ያሉት ኢማሙ በራሳቸው አልሚ ምግብ ለመስጠት መጣራቸውን በኃላም ቀይ መስቀል መጥቶ ትንሽ ነገር መስጠቱን ነገር ግን ሊዳረስ አለመቻሉን አስረድተዋል።

አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ሌላ የአከባቢው ነዋሪ ፥ " ሁለቱንም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ወላጆቻቸው የት እንዳሉ የማይታወቅ ተበትነው ያሉ ህፃናት ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠር መሆኑን ገልፀው ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች ጥሪ አቅርበዋል።

" እናታቸው አምስት ልጆች አባትም እናትም የሌላቸው አውቃለሁ። የጁምአ ቀን ተወልዳ ቅዳሜ እናቷ የተገደለችባት ህፃንም አለች "

ወላጆቻቸውን ካጣቱ በተጨማሪ አካለ ጎደሎ የሆኑ መኖራቸውን የገለፁት ነዋሪው በቂ ድጋፍ እየተደረገ እንዳልሆነና ጎረቤቶቻቸው እየተንከባከቧቸው መሆኑን ገልጿል።

የህክምናም ችግር አለ መቶ በመቶ የሚንከባከባቸው ሰው የለም ሲል አክሏል። ከ11 ቀን ጨቅላ እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት ሰብሳቢ ማጣታቸውን የገለፁት እኚሁ ነዋሪ አንዳንዶቹ ለከፋ የሰነልቦና ችግር መጋለጣቸውን ጠቁሟል።

ብሬል፣ ድሽቃ ሲተኮስባቸው የቆዩ ህፃናት አንዳንዶቹ በድንጋጤ ምክንያት መታመማቸውን፤ የማይናገሩ ህፃናትም፤ አንዳንዶቹ ብቻቸውን የሚያወሩም መኖራቸውን ለቪኦኤ ተናግሯል።

@tikvahethiopia
#እንዲያውቁት

የሎተሪ እጣ ከወንጀል ለተገኘ ሀብት መደበቂያ እየዋለ ነው።

በህገወጥ ሰዎች ዝውውር፣ በህገወጥ ምንዛሬ፣ በሙስና፣ በኢንቨስትመንት ማጭበርበር፣ በታክስ ማጭበርበርና ምዝበራ ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት ወንጀለኞች ያፈራሉ። በህገወጥ መልኩ ያፈሩትን ሀብትም ህጋዊ መልክ ለማላበስ ብዙ መላዎችን ይጠቀማሉ።

ከእነዚህ መላዎች አንዱ የሎተሪ እድለኞችን መጠቀም እንደሆነ ያውቃሉ?

አዎ! ወንጀለኞች የሎተሪ እድል አሸናፊዎችን ወይም እድለኞችን ተከታትለው ያገኛሉ፡፡ አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ እጣ ትኬት እጣው ከሚያስገኘው ገንዘብ በላይ ዋጋ በመክፈል ከባለ እድሉ ትኬቱን ይገዛሉ፡፡ የእጣው አሸናፊ ማግኘት ከሚገባው በላይ ገንዘብ ስለሚያገኝም ይስማማል።

በዚህ ሂደት የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸም በርካታ ገንዘብ ያፈራው ግለሰብ ደግሞ የሎተሪ እድል አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ ትኬት በእጁ በማስገባት ህጋዊ የሎተሪ አሸናፊ በመምሰል ይቀርባል፡፡ በዚህም ወንጀለኛው የሎተሪ እድሉን በህገወጥ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰል ይጠቀምበታል፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ላይ ማንም ሰው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የወንጀለኛውን ሀብት የደበቀ ወይም እንዲደብቅ የተባበረ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል፡፡

በመሆኑም የትክክለኛ የሎተሪ እጣ አሸናፊዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ መንገድ ወንጀለኞችን እንዳይተባበሩ እና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ባለቤት እንይሆነ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ያሰራጨው መረጃ ያሳያል።

Via @tikvahethmagazine
ለሀሰተኛ መረጃ ምን ያህል ተጋላጭ ነኝ ብለው ያስባሉ?

ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል ትልቁ መሳሪያ ዜጎችን በዚህ ላይ ያላቸውን ክህሎትና እውቀት ማስፋት እንዲሁም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም (በተለይም ከማኅበራዊ ሚዲያ ሥርዓት) ጋር ያላቸውን ልምምድ ከፍ ማድረግ ነው።

ለመሆኑ ራሶትን ምን ያህል ለሀሰተኛ መረጃ ተጋላጭ ነኝ ብለው ያስባሉ? ከታች የሚገኘው ሊንክ ራሶትን እንዲፈትሹ የቀረበ ማሳያ ነው።

በዚህ አማካኝነት ምን ያህል ለሀሰተኛ መረጃ ተጋላጭ መሆኖ ማወቅ ይችላሉ እንዲሁም አሳሳች መረጃዎችን የመገንዘብ ክህሎቶን ይፈትሹበታል።

ይጫኑት https://eth.versustheinternet.com

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዛሬ ጥዋት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ነው ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው " ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ከጥቂት ቀን በፊት በዋስ ከእስር የተለቀቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ በድጋሚ መታሰሩን ለማወቅ ተችሏል። ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ፥ ዛሬ ጥዋት ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ አካላት እንደወሰዱትና ወዴት እንደወሰዱት እንደማያውቁ ገልፀዋል፤ ያለበትን ቦታ ለማወቅም እያፈላለጉ መሆኑን አክለዋል። በሌላ መረጃ…
#Update

በዋስ ከእስር እንዲፈታ የተወሰነለት ጋዜጠኛ በቃሉ አለምረው ከእስር መፈታቱን ለማወቅ ተችሏል።

🔻

በሌላ በኩል ፦ አቃቤ ህግ በ “ፍትሕ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በተመስገን ላይ የክስ መዝገብ የከፈተው፤ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህግ መንግስት እና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

🔻

ኪዚህ በተጨማሪ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ የት እንዳለ ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ አመልክተዋል። ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከሚገኘው ጊዮርጊስ ምግብ ቤት "ትፈለጋለህ?!" ተብሎ ከተወሰደ በኃላ እስካሁን ያለበት አይታወቅም።

@tikvahethiopia
ፎቶ /ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች እየተስተዋሉ ነው።

ነዋሪዎች ታክሲ አግኝተው ወደሚፈልጉት ጉዳይ ለመሄድ ረጅም ሰዓት ሰልፍ ለመጠበቅ ሲገደዱ ተስተውሏል።

ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በከተማይቱ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በመሆኑ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል።

በተመሳሳይ በማደያዎች ላይ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ታይተዋል ፤ መልዕክታቸውን የላኩ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የቤተሰባችን አባላት ፤ ነዳጅ ለማግኘት እጅግ መቸገራቸውን ገልፀዋል።

" ዛሬ እንሰራለን ነገ ነዳጅ ለመቅዳት ተሰልፈን እንውላለን " ሲሉ ነው ሁኔታውን ያስረዱት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ " FIAS 777 " የተባለ ሰዎችን ትርፋማ አደርጋለው በሚል ከበርካቶች ኤጀንት በሚላቸው አካላት በኩል ገንዘብ ሲሰበስብ ከርሞ ዛሬ አድራሻውን ጥፍትፍት አድርጓል። #ሌሎችም፦ መሰል ስራ የሚሰሩ አሉ፤ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ከዚህ በፊት ያሰራጨነውን በድጋሚ ለማቅረብ ወደድን ፦ #REPOST " የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ ማትረፊያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ…
" ወንጀል ላይ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት በመለየት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን ነው " - FIS

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ‘ትርፋማ እናደርጋለን‘ በሚል በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በሚያደርጉት የቅስቀሳ ተግባር ከህብረተሰቡ በርካታ ገንዘቦችን በተለያዩ የክፍያ አማራጮች እየሰበሰቡ እንደሆነ ገልጿል።

እነዚሁ አካላት በተለይ ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ህብረተሰቡ ያለበት የኢኮኖሚ ጫና ተገን በማድረግ ባዘጋጁት የገንዘብ መሰብሰቢያ አማራጮች ላይ ማንኛውም ግለሰብ ገንዘብ የሚያስገባ ከሆነ ካስገባው ገንዘብ የበለጠ ትርፋማ እንደሚሆን በሚያቀርቧቸው የማሳመኛ መንገዶች ከበርካታ ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ እየሰበሰቡ እንደሆነ አሳውቋል።

ገንዘቡን በተለያዩ የክፍያ መነገዶችን በመጠቀም ሊሰበስቡ እንደቻሉ ነው የገለፀው።

ከእነዚሁ አካላት መካከል የበርካታ ግለሰቦችን ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አድራሻቸውን በማጥፋት #የተሰወሩ አካላት እንዳሉ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መረዳቱን አሳውቋል።

እነዚህ የማጭበርበር ወንጀል ላይ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት በመለየት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከእንደነዚህ አይነት የማጭበርበር ተግባራት ራሱን ሊጠብቅ ይገባልም ብሏል።

ማንኛውም ሰው ገንዘቡን ወጪ በማድረግ ከተለያዩ አካላት ጋር ስራዎች ለመስራት ወይም ሲሰራ በቅድሚያ አብሮ ለመስራት የተስማማው አካል በኢትዮጵያ ህጋዊ እወቅና ያለው መሆኑን፣ ትክክለኛ ማንነታቸውን አድራሻቸውን በማረጋገጥ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

(አድራሻ፦ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት)

@tikvahethiopia
#DoubleA

የ “Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

መተግበርያውን ለማውረድ:
Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or
https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው ! የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል። ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡…
#Update

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር እየተካሄደ ያለው ምንድን ነው ?

በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት የሰጡት ቃል ፦

- የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ድብደባው ለቀናት የዘለቀ ነው። እስከ ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሲደበድቡ ነበር።

- ነዋሪዎች ግጭቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አንዳንዶችም በአቅራቢያ ወዳሉ አካባቢዎች የመሄድ ሃሳብ አላቸው።

- ባለፉት ሶስት ቀናት በተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት #በሰው_ላይ_ጉዳት_አልደረሰም። የከባድ መሳሪያዎቹ በእርሻ ቦታዎችና የግብርና ካምፖች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

- በሱዳን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ምክንያት ነዋሪዎች ባለፉት ቀናት በእርሻ ማሳቸው ላይ የተለመደውን የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ከማከናወን ተቆጥበዋል።

- የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ ተስተጓግሏል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚገናኙበት የድንበር ከተማ የሆነችው የገለባት መተላለፊያ #ተዘግቷል

- የሱዳን ክስን ተከትሎ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በሁለቱ አገራት ወታደሮች መካከል ከሰኞ ወዲህ #ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ሲዘግቡ የቆዩ ቢሆንም በአካባቢው ጦርነት አልተካሄደም፤ ያለው ሁኔታ ከሱዳን በኩል የሚፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-06-29-2

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከግልገል በለስ እስከ አባይ ግድብ የሚደርሠውን መንገድ ስራ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዋና መምሪያው 210 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን ሶስተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ በማሳደግ ነው ስራውን ሰርቶ ያጠናቀቀው።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ሲጓጓዙ በመንገድ ላይ እስከ ሁለት ሳምንት ይቆዩ የነበረ ሲሆን በተከናወነው መንገድ የማሻሻል ጥገና ስራ የግድቡ የግንባታ ግብዓቶች #በአንድ_ቀን ለመድረስ ይችላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ /ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች እየተስተዋሉ ነው። ነዋሪዎች ታክሲ አግኝተው ወደሚፈልጉት ጉዳይ ለመሄድ ረጅም ሰዓት ሰልፍ ለመጠበቅ ሲገደዱ ተስተውሏል። ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በከተማይቱ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በመሆኑ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል። በተመሳሳይ በማደያዎች ላይ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ታይተዋል ፤ መልዕክታቸውን የላኩ የታክሲ አገልግሎት…
የናፍጣ እጥረት እና ምክንያቱ ምንድነው ?

ከ2 ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ የናፍጣ እጥረት በአዲስ አበባ ከተማ እየተፈጠረ ሲሆን ለምን እጥረቱ እንደተፈጠረ በሚሰጡት ምላሽ ላይ መንግሥትና የነዳጅ አቅራቢዎች ሊግባቡ አልቻሉም፡፡

ማደያዎችና ነዳጅ አመላላሾች እጥረቱ የተፈጠረው ከጂቡቲ የሚመጣ ነዳጅ በመጥፋቱ ነው በማለት መኪኖቻቸው ለቀናት ነዳጅ አጥተው ጂቡቲ መስመር ላይ መቆማቸውን ገልጸዋል፡፡

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ቦርድ አባል ኤፍሬም ተስፋዬ " ከ2 ሳምንታት ወዲህ በተለይ የናፍጣ እጥረት ተፈጥሯል፡፡ ይህም እጥረት የተከሰተው ጂቡቲ ላይ ተቀብለን የምናመጣው ናፍጣ ስለሌለ ነው፡፡ መኪኖቻችን ለቀናት ያለሥራ እየቆሙ ነው " ብለዋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ኃላፊዎች ደግሞ እጥረቱን የፈጠሩት ነዳጅ አከፋፋዮችና ማደያዎች እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የነዳጅና እነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ወ/ሮ ሳህሬላ አብዱላሂ " ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በየቀኑ የሚጫነው ነዳጅ ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በፊት በቀን ዘጠኝ ሚሊዮን ሊትር (በአማካይ) ይገባ የበረው በዚህ ሳምንት በአማካይ 9.294 ሚሊዮን ሊትር እየባ ነው " ብለዋል።

ከጂቡቲ እየተጫነ ያለው 200 ሺሕ ሊትር ነዳጅ አዲስ አበባ ሳይደርስ በተለያየ ሰበብ መንገድ ላይ ቆይቶ እየተያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. 10 ማደያዎች በአዲስ አበባ ውስጥ ነዳጅ እያላቸው መኪኖችን ሲመልሱ የተገኙ ሲሆን በነጋታው 14 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች አፋር ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ነዳጅ አከፋፋዮችና ማደያዎች አዲሱ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ከሐምሌ 1/2014 ጀምሮ መተግበር እስኪጀምር በእጃቸው ላይ የገባውን ነዳጅ ላለመሸጥ አዝማሚያ ማሳየታቸው እጥረት እየፈጠረ መሆኑ ዋናው ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

መንግሥት የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ ለማንሳት የወሰነው ውሳኔ ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሚገበር ሲሆን ይህም የነዳጅ ውጤቶችን ዋጋ ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ይህም ማለት አከፋፋዮችና ማደያዎች ከቀነ ገደቡ በፊት በድጎማ በዝቅተኛ ዋጋ የገዙትን ነዳጅ ከሐምሌ አንድ በኋላ ከፍ ባለው በአዲሱ ዋጋ ይሸጣል ማለት ነው፡፡

ድጎማው ሲነሳ በሊትር እስከ ዘጠኝ ብር ጭማሪ ሊኖር እንደሚችልና ይህም በአንድ ቦቴ እስከ 450 ሺሕ ብር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ እንደሆነ ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡

በነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአቅርቦት እና ሽያጭ ኃላፊ አቶ አባይነህ አወል ፥" ዋናው የእጥረቱ ምክንያት እስከ ድጎማው መነሳት ነዳጅ ለመያዝ መሞከር (Hoarding) ነው፡፡ የመኪና እጥረትም አይደለም፡፡ ጂቡቲ ላይ መዘግየት ያጋጠመው ለአንድ ቀን ሲሆን እሱም የጂቡቲዎች በዓል ቀን ስለነበር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሸጠው ነዳጅ በየቀኑ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን፣ ከጂቡቲ የሚጫነው ግን ጭማሪ አሳይቷል " ብለዋል።

ናፍጣ ከአጠቃላይ የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ውስጥ እጥረት ሲያጋጥም አሁን የመጀመርያው ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜ የሚፈጠረው የዲዝል እጥረት ነበር፡፡

በተለይም ማደያዎች ነዳጅን በብዛት ዴፖ ውስጥ መያዝ እየተው መምጣታቸው ለእጥረቱ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አቶ አባይነህ ይገልጻሉ፡፡ " ማደያዎችና አከፋፋዮች ነዳጅ የሚወስዱት በብድር መሆኑ ቀርቶ በካሽ ክፈሉ ከተባሉ ወዲህ፣ የባንክ ወለድ በመፍራት ነዳጅ በብዛት ዴፖ ውስጥ መያዝ ትተዋል፡፡ "

ወ/ሮ ሳህረላ ድጎማው እስኪነሳ አንሸጥም ብለው በጫካ ውስጥ ጭምር ነዳጅ ጭነው ተደብቀው እየተያዙ ያሉትን እየፈለጉ መያዝና ነዳጅ ወደ ገበያው እንዲደርስ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው። የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል። ሂደቱ…
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን #በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር ፣ማጥናትና ማወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠቁመዋል።

መረጃውን ከትምህርት ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#ቹ_የቋንቋ_ትምህርት_ቤት

በዓለም በስፋት (በተናጋሪ ብዛት) ከሚነገሩ ቋንቋዎች በአንደኝነት የሚቀመጠውን፣ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ የሆነውን፣ ቻይንኛ ቋንቋን ይማሩ!!

ቹ * ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የከተማችን የቋንቋ ት/ቤት ነው፡፡
*ለተማሪዎች በክረምት ወቅት የሚሰጥ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

አድራሻ፡
*ቦሌ፡ ፋንቱ ሱፐር ማርኬት አካባቢ፣ ሳይ ኬክ ቤት ያለበት ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
*ስታድየም፡ ትንሸዋ ስታድየም ጀርባ፣ ናሽናል ታወር ፣ 3ኛ ፎቅ
*አያት 49 የአየር መንገድ ቤቶች ፊት ለፊት ማይ ፕላዛ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በ 0947202020 ይደውሉ፡፡