TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ : ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫን ተረክባለች። ሴኔጋል የአፍሪካን ዋንጫ ካነሱ ሀገራት መካከል ስሟን አስመዝግባለች። ዋንጫውን ይዛ ወደ ሀገሯ ስትገባ ደግሞ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል እንደሚደረግላት ይጠበቃል። 🇸🇳 C H A M P I O N S O F A F R I C A 🏆 #AFCON2021 በዚህ ተደምድሟል። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Senegal , #Dakar📍

ሴኔጋል ድል አድራጊውን ብሄራዊ ቡድን ተቀብላለች።

የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን የሴኔጋል ርዕሰ መዲና ዳካር ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የሴኔጋል ፕሬዜዳንት ማኪ ሳልና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤርፖርት በመገኘት ቡድኑን ተቀብለዋል።

የዳካር ነዋሪዎችም ግልብጥ ብለው አደባባይ በመውጣት ለድል አድራጊው ብሄራዊ ቡድናቸው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#Egypt #Djibouti ኢማኤል ኦመር ጌሌ ግብፅ ገብተዋል። የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ናቸው የተቀበሏቸው። በዛው ዕለት ሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚኖራቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ…
#Update

ትላንትና ለሊት ግብፅ ፣ ካይሮ የገቡት የጅቡቲው ፕሬዜዳንት እና የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ዛሬ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው ላይ ሀገራችን #ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገናባችው ስላለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መነሳቱ ታውቋል።

ከውይይቱ በኃላ በተሰጠ መግለጫ ላይ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሀገራቸው ግብፅ አሁንም በህዳሴ ግድብ ላይ አስገዳጅ ስምምነት እንደምትፈልግ ከዚህ በፊት ሲናገሩት የነበረውን ንግግር አንስተው ተናግረዋል።

የመሪዎቹ ውይይት ከሀገራችን የህዳሴ ግድብ በተጨማሪም በቀይ ባህር እና በአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠከቀር ያለመም ውይይት አድርገዋል።

የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌህ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር የተደረገው ውይይት ገንቢ እና ፍሬያማ መሆናቸውን ገልጸው፣ “የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሁሉም ደረጃ ማጠናከርና ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ” መምከራቸውን ስለመናግረራቸውን AFP ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Walta💻

ከ864 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የዋልታ የፌስቡክ ገፅ መጠለፉን ለመመልከት ተችሏል።

የፌስቡክ ገፁ በክሪፕቶ ከረንሲ ጠላፊዎች እጅ እንደገባ የሚፃፉት ኮዶች እንደሚያመላክቱ የዘርፉን ባለሞያ ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ቼክ አስነብቧል።

የአክስዮን እና ክሪፕቶ ከረንሲ የሚገበያይ ነጋዴ የሆነው አብነት ተፈራ፥ " እየጠየቁ ያሉት የክሪፕቶ ከረንሲ ቲተር (Tether) ነው። ቴተር ማለት ወደ አሜሪካ ዶላር የሚመነዘር እና የሚተመን መጠን ያለው ሲሆን ስሌቱም 1 $. 5000 USDT = 5000$ ነው። " ብሏል።

አክሎም " በስተመጨረሻ የሚታየው ረጅም ቁጥር ደግሞ ኤተሪየም ዋሌት (Ethereum wallet) አድራሻ ነው፣ በህግ አስከባሪዎች እንዳይታወቁ ደግሞ አድራሻውን እየቁያየሩት ይገኛል" ሲል ለ ኢትዮጵያ ቼክ አስረድቷል።

ገፁን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ጠላፊዎች የገፁን አድራሻ የቀየሩት ሲሆን የተለያዩ መልዕክቶችንም እያስተላለፉ ይገኛሉ። የገፁ ፕሮፋይል ፒክቸርም ተነስቷል።

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በበኩሉ ሕጋዊ የፌስቡክ ገጹ የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ገልጿል።

ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ የገጠመውን የቴክኒክ ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን በመግለፅ ችግሩ መፈታቱን አስከሚያስታውቅ ድረስ በፌስቡክ ገፁ የሚለጠፉ ማናቸውም መልዕክቶች ከተቋሙ ዕውቅና ውጭ መሆናቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
መግለጫ ፦

" መንግስት በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም መስራት አለበት "

- የኢትዮጵያ ሴት ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት
- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችት ተሟጋቾች ማዕከል
- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ
- የመብቶችና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል
- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሚያ ሴቶች ማህበር
- ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ
- የስቄ የሴቶች ልማት ማህበር
- ምዥዥጎ ሎካ የሴቶች ልማት ማህበር
- ሴታዊት ንቅናቄ፣
- ትምራን ኢትዮጵያ፣
- ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ በሀገራችን በሴቶች ላይ የሚፈፀም ግድያና ጾታ መሰረት ያደረገ ጥቃት መባባስ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

የቅርብ ጊዜው የሰብል ንጉሴ እና የጸገሬዳ ግርማይ ጉዳይ ሁሉንም በእጅጉ ካሳዘኑ በርካታ ኢሰብአዊ ወንጀሎች መካከል የሚጠቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እየበዙ መምጣታቸውን አስገንዝበዋል።

ከላይ የተዘረዘሩት ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ፍትህ ሚኒስቴር የእነሰብለ ንጉሴ እና የፅጌረዳ ግርማይ የክስ ሂደት በአግባቡ እንዲሄድ ፤ ጉዳዩን በመመርመርም ፍትህን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የእንደዚህ አይነት ጥቃቶች መበራከትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ህግጋቶችን በአስቸኳይ እንዲያስተካክልም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ እነዚህን የጥቃት ድርጊቶች እንዲያወግዙም ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሚዲያዎች መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዙ እና ለተጎጂዎች ድምጽ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle 📍 አሚና መሐመድ ትግራይ ክልልን ጎብኝተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ የተመራ ልዑክ ዛሬ በትግራይ ክልል መቐለ ጉብኝት አድርጓል። የልዑካን ቡድኑ በመቐለ ከተማ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ፤ የጤና ባለሞያዎችን አነጋግሯል። ከዚህ በተጨማሪም በመቐለ የሚገኙ በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙባቸውን ካምፖች…
ስለ አሚና መሐመድ የአማራ እና የትግራይ ክልል ጉብኝት ምን ተባለ ?

የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮች ጋር ተገናኝተዋል።

አሚና ባለፈው እሁድ በአማራ ክልል ኮምቦልቻን የጎበኙ ሲሆን ጦርነቱ በሕዝቡ በተለይ በሴቶችና በህፃናት ላይ ያደረሰውን አስከፊ ጉዳት ማየታቸውን ተመድ አስታውቋል።

በሆስፒታሎች፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በገበያ ስፍራዎች እና በሌሎች አካባቢዎች ላይ የደረሰውን ዘረፋና ውድመት የተመለከቱ ሲሆን የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎችንም ባለሥልጣናትን አግኝተዋል።

ከኮምቦልቻ ጉብኝታቸው በኋላ ጦርነቱ ብዙ ያስከፈለ መሆኑን ገልጸው ሰላም ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተናግረዋል "የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ መርዳት አለብን" ሲሉም ተናግረዋል።

ከኮምቦልቻ ቀጥለቅ ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ያቀኑት አሚና በጦርነቱ በሴቶችና በህፃናት ላይ ያደረሰውን አስከፊ ገፅታ ተመልክተዋል።

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ለኢትዮጵያውን የሚያመጣውን እፎይታን በተመለከተ ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መወያየታቸው ንተመድ ገልጿል።

አሚና በተመድ የሚደገፈውንና ከወሲባዊ ጥቃት የተረፉ ሴቶችን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚያደርገውን የአይደር ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

" በግጭት ውስጥ አሸናፊዎች እንደሌሉ " በመጥቀስ ወሲባዊ ጥቃት የተረፉ ሴቶቹ ታሪኮች ሊነገሩ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በሁለቱ ክልሎች ከሴቶች እንዲሁም ከተማሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተመድ ወሲባዊ እንዲሁም ፆታን መሰረት ላደረጉ ጥቃቶችን እንደማይታገስ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

አሚና ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በሴቶች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል እንዲሁም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማቃለል ተመድ መፍትሄ በማፈላለግ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ሴቶች ካለባቸው ህመም እንዲፈወሱ በተሃድሶ እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ እንዲካተቱም አመራሮቹን አሳስበዋል።

በተጨማሪ ተመድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰላም ጥረትም ይደግፋል ብለዋል።

#UnitedNations

@tikvahethiopia
#MoE

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ፦

• የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ በመምጣቱ ፤ በአጠቃላይ የደረሰብን የሞራል ክስረት ከፍተኛ ነው።

• የእኔ ክልል ተማሪዎች ማለፍ አለባቸው በሚል በተቋም ደረጃ የፈተና ወረቀቶችን በመስረቅና መልስ በመስጠት ጭምር ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸው የትምህርት ሲስተሙ ጥራት ተዓማኒነት ከፍተኛ ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል።

• ግማሹ ለፍቶ ጥሮ ዉጤት እየያዘ ፣ ሌላዉ ደግሞ ከድግሪ ፋብሪካዎች ድግሪ እየተቀበለ የሚያልፍበት ሁኔታ ካለ ችግሩ የተወሰኑ ሰዎች ማለፍ ሳይሆን ፣ ችግሩ የትምህርት ጥራቱ ላይ ነዉ።

• ፈተና የሰዎችን ክህሎት እና ታታሪነት መለኪያ መሆኑ ቀርቶ ተሰርቆ ና መልስ ተሰጥቶ የሚመጣ ዉጤት ምዘና አያሟላም፣ ተዓማኒነት አይኖረዉም።

• የትምህርት ተቋማት ምዘና ተደርጎባቸዉ ሰርተፊኬት ይስጡ በሚባልበት ሁኔታ በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የስራ ሰርተፊኬት የሚሰጠዉ በችሎታቸዉ ሳይሆን በጉቦ ከሆነ ሲስተሙ ፈርሷል ይህንንም ሁላችንም ነው የምናዉቀዉ ነገርግን ፊትለፊት ስለማንነጋገርበት ስር የሰደደ መፍትሄ ልንፈልግለት ያልቻልነዉ ጉዳይ ነዉ።

• የትምህርት ስርዓቱን ተዓማኒነት ጥያቄ ዉስጥ የሚከት አካሄድ በጣም ተንሰራፍቷል።

• የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እንደዚህ ያሉ አሰራሮችን ማስቆም እና የሲስተሙን ተዓማኒነት ችግር ዉስጥ የሚከቱ ጉዳዮችን ከስር መሰረታቸዉ መፍታት አለብን።

[ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው ] - ከኢትዮ ኤፍ ኤም

@tikvahethiopia
#ችሎት

እነ አቶ አብዲ ኢሌ ተቃውሞ አሰሙ።

ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ-ሽብር እና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ 17 ተከሳሾች ተቃውሞ አሰምተዋል።

እነ አቶ አብዲ ኢሌ ከኛ ጋር ታስረው የነበሩት እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ ነው ተቃውሞ ያሰሙት።

አቶ አብዲ መሀመድ እጃቸውን በማንሳት ይህን ተናግረዋል ፦

" ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት አንቀርብም እኛ ከስር ከተፈቱ ግለሰቦች የተለየ ምንም ወንጀል አልፈጸምንም። ስለዚህ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ታስረን ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም።

ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ከትግራይ እና ከሌሎችም ከተፈጸመው ወንጀል የኛ በምን ይለያል ?

ግድያ በተፈጸመበት ሁኔታ ሌሎች ሳይጠየቁ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ጉዳይ የለም። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ እኛ ፍርድ ቤት አንቀርብም። ፍርድ ቤቱ የራሱን ውሳኔ ይስጥበት "

ከሳሽ አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ይስጥበት እና ክርክሩ ይቀጥል ሲል ችሎቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ከእስር የተፈቱ እስረኞችን ክስ ያቋረጠው ፍትህ ሚኒስቴር መሆኑን ገልጿል።

አስተያየታቸዎውን ለፍትህ ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚችሉ የገለጸው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ መርምሮ ተገቢውን ትዛዝ ለመስጠት ለፊታችን ሀሙስ የካቲት 3ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

(የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ)

ያንብቡ : https://telegra.ph/Abdi-Muhamud-Omer-02-08
#EthiopianCatholicChurch

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተከርስቲያን የማህበራዊና ልማት ኮሚሽን የሴቶችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን ታከናውናለች፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ሀገረስብከት የልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር “የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ሴቶች የስራ ተወዳዳሪነትን ማሻሻል ለተሻለ የስራ እድል ተጠቃሚነት” በሚል መነሻ ሃሳብ ጥናታዊ ፕሮጅክት ለማካሄድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ማቀዷን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቃለች።

የጥናቱ ዋነኛው ዓላማ ምሩቃን ሴቶችን በስራ ዝግጁነት ስልጠና በማሰልጠን የስራ እድል መረጃዎችን በማቅረብ እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመስጠት እና በማብቃት የስራ ተወዳዳሪነታቸውን መጨመር መሆኑ ተገልጿል።

ሂደቱ ለሴቶች ተቃሚነት ያለውን ሚና በጥናት በማስረዳት ለፖሊሲ ግብዓት በመሆን ያገለግላል ተብሏል። ጥናቱ ከሚካሄድባቸው ስፍራዎቸ የአዲስ አበባ ከተማ አንዱና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል

ጥናታዊ ፕሮጀክቱ በአ/አ ከ2009 ጅምሮ እስከ 2013 ዓ.ም ባለው የትምህርት ዘመን ከታወቀ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው መደበኛ የሥራ ዕድል ያላገኙ 662 ሴት የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎችን ያሳትፋል፡፡

በመቀጠልም ይህ ፕሮጀክት ለ 441 ሴት ምሩቃን በግልጽ ሂደት ተመርጠው የስልጠናዎች እና የሥራ እድል መረጃ በመስጠት ተጨማሪ ድጋፎች ያደርጋል፡፡

( ዝርዝር መስፈርቶች ፣ የመመዝገቢያ ቦታ እና ተጨማሪ መረጃዎች ከላይ ተያይዟል )

@tikvahethiopia
የ245 ሺህ ብር ሽልማት ያሸነፉት ተማሪዎች👏

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና ሴት ተማሪዎች የፍራፍሬ እና ሌሎች የዕፀዋት ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም ለወረቀት መስሪያ የሚሆን “ፐልፕ” በማምረት በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ የ245 ሺህ ብር አሸነፊ ሆኑ፡፡

ተማሪዎቹ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የማይመረተውን ፐልፕ የተሰኘውን ለወረቀት ማምረት ስራ የሚውል ግብዓት በማምረታቸው ነው ውድድሩን ያሸነፉት፡፡

የተማሪዎቹ የፈጠራ ስራ ፕሮጀክት በገንዘብ ቢደገፍና ወደ ተግባር ቢለወጥ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከሚሰጠው ፋይዳ በተጨማሪም የአከባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ደረጃ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ245 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊዎች 👏

ከአሳ ተረፈ ምርት (ከአሳ ቆዳ) በመጠቀም #ሎሽን የሰሩት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የአምና ምሩቃን በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ የ245 ሺህ ብር አሸነፊ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ።

" ሬይ ኮስሞቲክስ " ከአሳ ቆዳ ሎሽን በማዘጋጀት አንደኛ የአካባቢን ንፅህን በመጠበቅ በሌላ በኩል ለተገልጋዮች አሁን ላይ ገበያ ላይ ካሉት ሎሽኖች ለየት ያሉ ጠቅሞችን የሚያሰጥ እንደሆነ ተገልጾልናል።

እስካሁን ወደ ምርት እንዳልገቡ የተናገሩት የሬይ ኮስሞቲክስ አባላት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ስር እዳሉ አሳውቀዋል። ወደ ሽያጭ እና ወደ ምርት ለመግባት ግን ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የሬይ ኮስሞቲክስ መስራች እና የፕሮዳክሽን ማነጀር ራውላ ኤፍሬም የስራ ፈጠራ ውድድሩ ላይ በመወዳደር የ245 ሺህ ብር አሸናፊዎች መሆን መቻላቸውን ገልፃለች።

ከሶስት ሳምንት በፊት አሸናፊ ቢሆኑም እስካሁን ግን ብሩ እጃቸው ላይ እንዳልደረሰ ጠቁመውናል።

@tikvahethiopia
#SidamaRegion

የሲዳማ ክልል " ጠቅላላ ሀኪሞች " ን በክልሉ ስር ባሉ የጤና ተቋማት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

👉 የሙያ አይነት - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የት/ት ደረጃ - የመጀመሪያ ዲግሪ
👉 የወር ደመወዝ - 9,056 ብር
👉 ብዛት - 126 (አንድ መቶ ሀያ ስድስት)
👉 የስራ ልምድ - 0 ዓመት ( #ዜሮ_ዓመት)
👉 የመመዝገቢያ ቀን - ከ1/06/2014 ዓ/ም እስከ 10/06/2014 ዓ/ም (10 ተከታታይ የስራ ቀን)
👉 መመዝገቢያ ቦታ -የሲ/ክ/ጤ/ቢሮ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 3
👉 ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከታወቀ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ/የተመረቀች የሙያ ፍቃድ/ላይሰንስ ያለው/ያላት

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. ሁሉም ተወዳዳሪዎች በክልሉ ባለው የጤና ተቋም በዕጣ ተመድቦ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።

2ኛ. ሁሉም ተወዳዳሪ የት/ት ማስረጃ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለበት።

(መዕክቱን ለሌሎች share ያድርጉ / Copy አድርገው ያሰራጩ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia, #WestGuji 📍 በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በሸኔ በመከበቡ ውሎ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን አመለከቱ። ነዋሪዎች የታጣቂ ቡዱን በርካታ የወረዳውን ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን በመግለፅ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ ንብረትም እንደሚወድም እና እንደሚዘረፍ ገልፀዋል። ወረዳው ነዋሪ ፦ " ያለንበት ሁኔታ አሰቃቂ እና ተስፋ የሌለው ነው። በአሁን ጊዜ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ነን።…
#GelanaWoreda

በገላና ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት የተኩስ እሩምታ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 4 ሰዎች ቆሰሉ።

የአማሮ ልዩ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ ቤት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፥ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት በጫኑት ሸቀጥ ላይ ሰዎችን አሳፍረው ከዲላ ከተማ ወደ አማሮ ኬሌ ሲጓዙ በነበሩ ኤፍ- ኤስ- አር የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ነው።

ጥቃቱን ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የደረሰ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ውስጥ በተለምዶ የመከራ ዳገት በተባለ አካባቢ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ መቶ አለቃ ስላሴ ሽሎ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ሶስት ሰዎች የአንደኛው ተሽከርካሪ ሾፌር ፤ ረዳቱና አንድ መንገደኛ ሲሆኑ በሌላኛው ተሽከርካሪ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ደግሞ በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን ገልፀዋል።

3ቱም ተሽከርካሪዎች ከዲላ በተነሱበት ወቅት በያዙት ጭነት ላይ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን ጭነው እንደነበረ የጠቀሱት ሃላፊው ታጣቂዎቹ መተኮስ እንደጀመሩ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከተሽከርካሪዎቹ ላይ በመዝለል ወደ ጫካ መሸሻቸውንና አስከአሁንም ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ አስረድተዋል።

ጥቃት ፈፃሚዎች ታጣቂዎቹ በመንገደኞቹ ላይ ካደረሱት ግድያ በተጨማሪ ንብረትነቻው የግለሰብ ነጋዴዎች የሆኑና በተሽከርካሪዎቹ ተጭነው የነበሩ ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችንም ሙሉ በሙሉ መዘረፉቸውንም ተናግረዋል ።

በአሁኑ ወቅት የ3ቱን ሰዎች አስክሬን ወደ አማሮ ኬሌ ከተማ በማምጣት ዛሬ ቀትር የቀብር ሥነስረዓታቸው መከናወኑን የገለፁት የመቶ አለቃ ስላሴ የቆሰሉ ሰዎች ደግሞ በህክምና ተቋም ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ሊመረቅ ነው። ባንኩ ፥ " ከምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት ከባንኩ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ገጥሟል፡ " ብሏል። በትክክል የሚመረቅበት ቀን ይፋ ይሆንም በቅርቡ ግን ህንፃው እንደሚመረቅ ተገልጿል። @tikvahethiopia
#Update

ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ እሁድ ይመረቃል።

80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና የአዲሱን ዋና መ/ቤት ምርቃት በዓሉን አስመልክተው የባንኩ ፕሬዚዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫቸው ህንፃው የፊታችን እሁድ ዕለት ይመረቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል እ.ኤ.አ በ1942 በ1 ሚሊዮን የማሪያትሬዛ ካፒታል ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ፦
• 824 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ፣
• 1.1 ትሪሊዮን ብር ጠቅላላ ሀብት ፣
• ከ1 ሺህ 800 በላይ ቅርንጫፎች
• ከ34 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አቶ አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia