TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሰሜን ጀርመን ቲክቫህ አባል፦

በጀርመን የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮ. አባል ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን እንዲሰጡ፣ ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ቢደረግ መልካም እንደሆነ አንስቷል።

የቤተስችን አባል በሚገኝበት ጀርመን ያሉ የኤፍ ኤም ሬድዮ ጣባያዎች ፣ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የጤና ባለሞያዎችን፣ ሳይንቲስቶችን እያጋባዙ ከህዝቡም ጥያቄ እየተቀበሉ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እየሰሩ እንደሚገኙም ነግሮናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ጋር የተጠረጠረ የ36 ዓመት ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ!

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተሻለ ማናዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ36 ዓመት ግለሰብ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ታይቶበት አርባምንጭ ሆስፒታል ለህክምና በመጣበት ተጠርጥሮ ለጥንቃቄ ሲባል ለይቶ ማቆያ መዕከል ላይ እንዲቆይና የባለሙያ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ግለሰቡም በቀን 07/07/2012 ዓ.ም. ለአንድ ቀን በኬንያ ለንግድ የተንቀሳቀሰ በመሆኑና ኬንያ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አገር በመሆኑ ምክንያት ግለሰቡ ሊጠረጠር ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ተሻለ ከግለሰቡ ጋር ንኪኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዉ ግለሰብ በዛሬዉ ዕለት ናሙና ተወስዶ በምርመራ እንዲረጋገጥ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር በጥምረት እየተሰራን እንደሚገኝ ተልጿል፡፡ ህብረተሰቡ በምርመራ ባልተረጋገጠ መረጃ መረበሽና መደናገር እንደሌለበት የዞኑ ጤና መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የታክሲ እና የባስ ማቆሚያዎች ሰዎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲቆሙ ለማድረግ ስራዎችም እየሰሩ እንደሆነ ነገርውናን። ይህ ስራ መላው ከተማይቱን ማዳረስ ይኖርበታል👍

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከUS ኒውዮርክ ቲክቫህ አባል፦

የምኖረው ኒውዮርክ ነው። በዚህች ከተማ ብቻ ኮሮና የያዘው ሰው በመላው አሜሪካ ያለውን 1/3ኛ ይሸፍናል፣ በአጭር ቀናት ከ8 ሺህ አልፏል።

ለዚህም ዋናው ምክንያቱ የአስተዳዳሪዎች ቸልተኝነት እንዳለ ሆኖ የመመርመር አቅም መጨመር ነው ፣ ማለትም ብዙ ሰው ስትመረምር ብዙ ሰው በበሽታው የተያዘ ታገኛለህ።

በሽታው ሲጀምር ትንሽ ሰዎችን ስለሚይዝ ያዘናጋል፣ ከተወሰነ ቀን በኋላ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዎች ስለሚይዝ በድንጋጤ የምትሰራውን አታውቅም። ስለዚህ ሁላችንም ቀድመን የቤት ስራችንን እንስራ ፣ አንዘናጋ ቀልዱንም ካለፈ በኋላ እንደርስበታለን!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኒው ዴልሂ ህንድ የቲክቫህ አባል፦

በህንድ የሚገኘው የቤተሰባችን አባል መሰረት ማህበራዊ ርቀታችንን እንጠብቅ፣ በቻልነው አቅም እንጠንቀቅ፣ በሽታው ወደገጠር ከተስፋፋ ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሚሆን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባ መልክት አስተላልፏል። በህንድ ኒው ዴልሂ ስላለውም ጥንቃቄ ነግሮናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከጀርመን ባቫሪያ የቲክቫህ አባል፦

ይህ ፈታኝ ወቅት እስኪያልፍ ድረስ ሁሉም ሰው በጤና ባለሞያዎች እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ ቢያደርግ መልካም ነው። ጀርመኖች ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ነው፤ የሚተላለፉትንም የጥንቃቄ መልዕክቶች በመተግበር በሽታውን ለመቆጣጠር እየሰሩ ናቸው ይለናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከልን እና ላቦራቶሪን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

ከጤና ሚኒስትር ዴኤታዎች ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ጋር በመሆን ማዕከሉን የጎበኙት ሚኒስትሯ ከማዕከሉ አስተባባሪዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡

#MoH #etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
176 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተጠቁባት ኩዌት ከላይ በቪድዮው የምትመለከቱትን ትመስላለች። የኮሮና ቫይረስ እንዳይሰራጭ ከፍተኛ ስራን እየሰራች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኩዌት ቲክቫህ አባል፦

ጣልያኖች መጀመሪያ ልክ እንደኛ ቦታ ስላንሰጡት ዛሬ ዋጋ ከፍለዋል። ስብሰባዎች ሊደረጉ አይገባም ፤ ከእጃቹን ታጠቡ ብቻ ከሚለው በላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊሰራ ይገባል ይለናን ኩዌት የሚገኘው ቤተሰባችን አባል።

በኩዌት ውስጥ የሰዓት ገደብ ተጥሏል። የተጣለውን የሰዓት ገደብ የተላለፈ ሰው ከ10 ሺህ ዲናር የሶስት ዓመት እስራት ይጠብቀዋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ‘ምክንያታዊ ያልሆነ’ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን የሃገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

በተለይም በአሥመራ ከተማ በእህል፣ በዘይት፣ በስኳርና በጽዳት ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፤ ድርጊቱ የሕዝቡን ኑሮ የሚጎዳ በመሆኑ “ከባድ እርምጃ” እንደሚወስድ ገልጿል።

ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ዕቃዎችን በሚደብቁ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፍቃድን ከመንጠቅ አንስቶ እስከ ንብረት መውረስ የሚደርስ እርምጃን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከደቡብ ሱዳን አብዬ ግዛት ቲክቫህ ቤተሰብ:-

ጣልያኖች ላይ የደረሰው ነገር የሚተላለፉ መልእክቶችን በቸልተኝነት ከማየት ነው። አሁን በኢትዮጵያም ያለው ሁኔታ በመጀመሪያ ጣሊያኖች ጋር የነበረው አይነት ነው። ኢትዮጵያ ያላችሁ እባካችሁ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡት የጥንቃቄ መረጃዎችን በኀላፊነት ተግብሩ። ማህበራዊ ርቀት ላይ በደንብ ስሩበት። ቻይና ለመቆጣጠር የደረሰችው የሚተላለፉ መረጃዎችን በአፅንኦት በመተግበሯ ነው።

እኔ አሁን ያለሁት የሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ድንበር ነው። በአከባቢው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ስታፍ እና ከ4,000 የሚበልጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይገኛል። የተመድ ሰላም ማስከበር ስታፍ እና ሰራዊቱ የተለያዩ የግንዛቤ እና የመከላከል ስራዎችን እያገኘ ቢሆንም በአከባቢው ያለው ማህበረሰብ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው አስቸጋሪ ሆኖብናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በሐረሪ ክልል እና አካባቢው ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የኮሮና ቫይረስን የመከላከሉን ስራ ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አሳሰቡ።

የሐረሪ ክልል፣ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲና የምስራቅ ዕዝ አመራሮች በሽታውን ለመከላከል እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይቱ እንዳሉት በክልሉና አካባቢው በህብረተሰቡ ዘንድ አልፎ አልፎ መዘናጋት እና ቸልተኝነት ይስተዋላል።

በተለይም በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የህብረተሰብ  ክፍሎች ያላቸው ማህበራዊ ትስስር ልማድ በመሰብሰብና ቅርርብ የሚከናወን ነው፤ ይህም ለበሽታው ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

በሀረሪ ክልል ቫይረሱን ለመከላከል ከውሃ አቅርቦትና  ገበያ ማረጋጋት ጋር በተያያዘ  እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል 45 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል። ከነዚህ ውስጥ 22 ሰዎች በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። የተቀሩት ደግሞ ውጤታቸው እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል አምስት መቶ ሺህ (500,000) የአፍ መሸፈኛ (ማስክ) እና 48,000 ሊትር ሳኒታይዘር እንዳዘጋጀ ገልጿል። በቅርቡ ለነዋሪዎች እንደሚያሰራጭ አሳውቋል።

በኦሮሚያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በአራት አካባቢዎች የለይቶ ማቆያዎች ተዘጋጅተዋል። ለህክምና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል ተብሏል።

በክልል የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምልክት የታየበትን ሰው ጥቆማ ለመስጠት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነፃ የስልክ መስመር 6955 ይፋ ተደርጓል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ኢትዮጵያ ውስጥ ከገቡ በኃላ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው ሁለት ጃፓናውያን ነገ ጠዋት ' በአውሮፕላን አምቡላንስ ' ከኢትዮጵያ ወደ ጃፓን ይወሰዳሉ።

[ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአዋሽ ሰባት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከእነዚህም ስራዎች ውስጥ ለቫይረሱ ሊያጋልጡ የሚችሉ ከ100 በላይ የሺሺ መጠቀሚያ እቃዎች እንዲቃጠሉ ተደርገዋል።

11 የጫት ንግድ ቤቶች ደግሞ ለቫይረሱ በሚያጋልጥ ሁኔታ ሰዎች ሰብስበው ሲያስቅሙ ተደርሶባቸው ታሽገዋል፤ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በመላው አውስትራሊያ ግድ የማያሰኙ ግልጋሎት ሰጪዎች ከዛሬ ጀምሮ ዝግ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዛሬ ጀምሮ ምግብ ቤቶች ፣ ቡና ቤቶች ፣ የአካል እንቅስቃሴ መስሪያ ሥፍራዎች ፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሆቴሎች ፣ ክለቦች ፣ የቤት ውስጥ ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የመዝናኛ ቤቶችና የእምነት ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የገበያ አዳራሾች ክፍት በመሆናቸው አውስትራሊያውያን 'ኃላፊነት በጎደለው' ሁኔታ በሸመታ ሊራኮቱ እንደማይገባ አሳስበዋል።

#ኤስቢኤስ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia