TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ‼️

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ውዥንብር ውስጥ እና አላስፈላጊ ስጋት ውስጥ የሚከቱ #ግለሰቦች ላይ ከፀጥታ ሀይላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድኩ ነው ብሏል። ዩኒቨርሲቲው አጥፊዎች በጥፋታቸው መጠን በዲሲፕሊንና በህግ ይጠየቃሉ ሲል ገልጿል። ለተማሪዎች ደህንነት ሲባልም የግቢው መግቢያ 2 ሰዓት እንዲሆን መደርጉን ከዩኒቨርሲቲው ተሰምቷል። ተማሪዎችም ለዩኒቨርሲቲው የዲሲፕሊን ስርዓት ተገዥ እንዲሆኑ #አጥብቆ አሳስቧል።

በሌላ በኩል...

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የከፍተኛ ትምህርት መማር ማስተማር ሂደት #በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከወትሮው በተለየ ከሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ጋር እየሰራ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት መግለፁ አይዘነጋም። ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያከናወነ እንደሆነም ገልፆ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አላማጣ ቆቦ‼️

የትግራይን ክልል ከአማራ ክልል የሚያገናኘው አላማጣ ቆቦ መስመር ለተሽከርካሪዎች ከተዘጋ 5 ቀናት አስቆጥሯል። መንገዱ የተዘጋው በአላማጣ ከተማ #የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱላቸው በጠየቁ የቆቦ ከተማ ወጣቶች ነው ተብሏል።

የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምርያ እንዳስታወቀው ችግሩን #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት #ውይይት እየተካሄደ ነው።

የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው - መንገዱ በመዘጋቱ ለስራቸውን #እንቅፋት እየፈጠረባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ(የትላንት ምሽት ዘገባ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ቶሌራ አዳባ-ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ እና የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ በመተማመን እና በመግባባት መንፈስ እንደሚሠሩ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ #ቶሌራ_አደባ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል።

በኦዴፓና በኦነግ መካከል ሰሞኑን የተደረሰው ስምምነት አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት አቶ ቶሌራ በግንባራቸውና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ሰኔ 1/2010 ዓ.ም. አሥመራ ላይ የተደረሰውን ባለሦስት ነጥብ ስምምነት በፈጠነ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።

የአሥመራው ስምምነት “ኦነግ #በሰላማዊ መንገድ ትግሉን በሃገር ቤት እንዲቀጥል ማድረግ ማስቻል፤ ካለው መንግሥትና በተለይም ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የኦሮሞን ጉዳይ በተመለከተ መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር በጋራ የሚሠራበትን ሁኔታ በመደጋገፍ መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ትግላቸውን በመንግሥት ድጋፍ የሚቀጥሉበትን ሁኔታ በመመካከርና በመነጋገር ማመቻቸት” እንደሆነ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዳሰሳ 2‼️

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሃገሪቱ እየታየ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል እና #ሁከትን ለመቀነስ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

🔹ደብረ ማርቆስ ዩኒቭርስቲ

የመከላካያ ሚንሰትር ዴኤታ አምባሰደር ዘላለም ገብረ ዮሃንሰን ጨምሮ ከፌዴረል እና ከክልል የተወከሉ የመንግስት አካላት የምስራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር፣ የሃገረ ሽማግሌዎች ፣የሃማኖት አባቶች እና የጸጥታ አካላት በተገኙበት ምክክር አካሂዷል፡፡

🔹ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የሚነሱ የግጭት መንስኤዎችን ለይቶ ቅድመ መከላከል ለመስራት እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

🔹ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

ከሕዳር 19 ጀምሮ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች #በሰላማዊ የመማር ማስተማር ዙሪያ ከፌዴራል በተገኙ አወያዮች ምክክር አድርገዋል፡፡

‹‹የምንማረው ድህነትን በአንድነት ለማሸነፍ እንጂ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን የልዩነት ምንጭ አድርጎ ለመራረቅ አይደለም፡፡›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተናገሩት...

‹‹በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ኢትዮጵያዊነት ለአንድነታችን ማጠናከሪያ፤ ለቁርሾዎቻችን መታረቂያ ምክንያት እንዲሆኑ ጥያቄዎችን የመፍታት ባሕል ማድረግ አለብን፡፡›› አወያዮች ከተናገሩት የተወሰደ...

🔹ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከአማራ ክልል መንግስት እና ከሌሎች አካላት የተወጣጣው የሰላም ኮሚቴ በባሕር ዳር ለ14 ቀናት የሚቆይ ከሰላም መስፈን ጋር የተያያዙ ተግባራትን እየተከታተለ እና እያገዘ መሆኑን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን እና ስታራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶር. #ዘውዱ_እምሩ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ኮሚቴው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት እና አጠቃላይ በከተማው ያለውን የሰላም ሁኔታ ገምግሟል፡፡ በዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን በአግባቡ በመቀበል፣ መረጃ በመስጠት እና #የግጭት_ስጋቶችን በማስወገድ በጎ ስራ መስራቱን ተመላክቷል ነው ያሉት ዶር. ዘውዱ፡፡

‹‹ሰላም ቀላል የሚመስል ነገር ግን የሁላችንም እስትንፋስ ነው፡፡ ለሰላም የበኩላችንን እንወጣ››

‹‹ራሳቸውን አደራጅተው የአካባቢውን ጸጥታ የሚጠብቁ ወጣቶች የተማሪዎች ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን በጎ ስራ ሰርተዋል፡፡›› ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

.
.
©አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገለጹ፡፡ በዞኑ ሻኪሶና ጎሮዶላ ወረዳ የትጥቅ ትግል ሀሳብ የነበራቸው 20 የኦነግ አባላት ትጥቃቸውን በማስቀመጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተመልሰዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎቹ ከእስር እየተለቀቁ ነው‼️

የድሬደዋ አስተዳደር በቅርቡ በከተማው በተካሄደው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ #ጠረጠርኳቸው በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች የአብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ በነፃ እየለቀቀ ይገኛል። ከቀናት አስር በኃላ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ የተለቀቁ ተጠርጣሪዎችና ቤተሰቦች እንዲሁም ወዳጆች በእምባ ተራጭተዋል፡፡ በከተማው ለቀናት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ሀይሉ በወሰደው ሰፊ እርምጃ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን አፍሶ በመያዝ ከአስራ አምስት ቀናት በላይ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲመረመር ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች ሁለት መቶ አስራ ስምንት የሚሆኑትን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ፖሊስ ውሰኔ ክሳቸው ተቋርጦ በነፃ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡

ከሳምንት በፊት በሀላፊነት የተሾሙት የአስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ኮማንደር አለሙ መርጋ ተጠርጣሪዎቹ ስለተለቀቁበት ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ተጠርጣሪዎችን በመልቀቅ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከመልቀቃቸው በፊት ከተጠርጣሪዎች ፣ ከቤተሰብና በነፃ ጥብቅና ቆመው ከነበሩ የህግ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ኮምሽነሩ ስለውይይቱ ዓላማ ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ቀናት በተካሄደው በዚህ ውይይት በከተማው የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎ በጅምላ ተይዘው የቆዩ ተጠርጣሪዎች ከድርጊቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር ጭምር መሆኑነንና፣ በምርመራ ሂደትም ከመርማሪዎች ከብቃት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደነበሩ ተነስተዋል፡፡ ወጣቶቹም #በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንቐጥላለል ብለዋል፡፡

ከህብረተሰቡ ለተነሱት ጉዳዮች በፖሊስ እና ዐቃቤ ህግ በኩል ተወስደው የሚታረሙ መሆኑ ተገልፇል፡፡ በሌላ በኩል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀርበው ግዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ከነበሩና ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ዘጠና ተጠርጣሪዎች አብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ መልቀቃቸው ለፍ/ቤቱ ተገልፃል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ 107 ተፎካካሪ ፓርቲዎች #በሰላማዊ_መንገድ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን የጋራ የአሰራር የቃልኪዳን ሰነድ ፈርመዋል።

Via Abrha Desta
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጃር ሸንኮራ----ፈንታሌ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራና በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌና በሦሰት ወረዳዎች መካከል በቦታ እና በግጦሽ መሬት ይገባኛል ምክንያት ሰሞኑን በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።፡ መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ የማረጋጋት ሥራ እየሠራ መሆኑም ተመልክቷል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአረርቲ ከተማ ነዋሪ በስልክ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በፊትም ከእሳር ግጦሽና ከውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አልፎ አልፎ ግጭቶች እንደሚስተዋሉ አመልክተዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በኢዶ፣ ፊናናጆ፣ ቂሌ አርባና ክትቻ በተባሉ አካባቢዎች የታየው ግን ከሁሉም የከፋ ነበር ያሉት እኚህ የዓይን ምስክር ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበርና በግጭቱም የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ ንብረትም ወድሟል ብለዋል፡፡ የመከላከለያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመግባቱ ተኩስ መቆሙንና አሁን አንፃራዊ ሰላም እየታየ እንደሆነም አረጋግጠዋል።

ስለአካባቢው ሁኔታ እንዲስረዱኝ ለምንጃር ሽንኮራን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይትባረክ አብርሀም ሰልክ ደውዬ ጠይቂያቸው ነበር። ነገር ግን ስብሰባ ላይ ነኝ በሚል ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልፈቀዱም።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው በበኩላቸው ከግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ በአካበቢው ግጭት አልፎ አልፎ እንደሚከሰት ጠቅሰው ይህም የዛው አካል ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ሌላ የተለየ ፍላጎት ያለው አካል ነገሩን አባብሶት ከሆነ እንደሚጣራም አስረድተዋል።

በግጭቱ ከአማራ ክልል በኩል ሦስት ሰዎች ተገድለዋል፣ ሌሎች 3 ደግሞ ቆስለዋል ነው ያሉት። በሌላው ወገን በኩል ያለውን ጉዳት እንደማያውቁም ለባህርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ጋር #በሚዋሰንባቸው በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በኦሮሚያ ፈንታሌና ቦሦት አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም መከላከያ ወደ አካባቢው እንዲገባ ተደርጓል። በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያም ሆነ የአማራ የጸጥታ አካላት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓልም ብለዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት አሁንም ቢሆን ችግሩ #በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በስምምነት እንጅ #ግጭት በመቀስቀስ ይፈታል ብሎ እንደማምንና በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ ኗሪዎችን ባካተተ መልኩ የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጠውም ይሠራል ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት #መፍትሄ ይስጠን...
/የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች/

√በርካታ ተማሪዎች ከዶርማችን ውጪ ላለፉት ቀናት በአዳራሽ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ እያደርን ነው ግቢው በሩን ከፍቶ በሰላም ይሸኘን ሲሉ ተማሪዎች #በሰላማዊ_ሰልፍ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ምላሽ ካገኘሁ ወደናተ አደርሳለሁ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia