TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርበኞች እና ግንቦት 7 ተለያዩ‼️

አርበኞች እና ግንቦት 7 #ስለመለያየታቸው በባሕር ዳር አሁን ላይ #መግለጫ እየተሰጠ ነው። ከዚህ ቀደም እንደተለያዩ መግለጫ ቢሰጥም በግንቦት ሰባት አመራሮች በኩል ሁለቱ ድርጅቶች አለመለያታቸው ነበር የተገለጸው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ነገ #በፍኖተ_ካርታው ዝግጅት ዙሪያ ጋዜጣዊ #መግለጫ ይሰጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አጠቃላይ የትምህርት ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጧል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው ለውይይት ቀርቦ ግብዓት እንደተሰጠበት ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት ነገ በትምህርት ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለሞያሌ‼️

"መንግስት ስለ ሞያሌ ሁኔታ ምንም ትኩረት እየሰጠው አይደለም። ብዙ ጊዜ ያስቆጠረ ችግር ነው። ሰው እንደ ቄጤማ እየረገፈ፤ እንዴት አንድም ቀን እንኳን ስለሞያሌ ሁኔታ ደፍሮ #መግለጫ የሚሰጥ ጠፋ? ሞያሌ ውስጥ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ? ከሞያሌ የመጡ ጓደኞቻችን እያለቀሱ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በጅግጅጋና አካባቢው #ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው #ወንጀል ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች #በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካለትም መኖራቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ከሀምሌ 28 እሰከ 30 በሶማሌ ክልል በጅግጅግናና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ በጋራ ሲያደርጉት የቆዩትን የምርመራ ስራ አጠናቀዋል።

ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሄርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ የድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት ተጨማሪ ትልልቅ ወንጀሎች እንደተገኙ የታወቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ተጨማሪ ግለሰቦች መኖራቸውም ታውቋል።

የምርመራው ውጤት በመጠናቀቁም በቁጥጥር ስር ያሉትን የክልሉን የቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሌሎች አካላት ላይ ክስ መመስረቱ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የምርመራ ሂደትንና ውጤቱን በተመለከተም አርብ (ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም) በጠቅላይ ቃቤ ህግ ለጋዜጠኞች #መግለጫ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ‼️

ድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታወቀ።

ኮሚቴው ምሽት ላይ በሰጠው #መግለጫ #በመልካ_ጀብዱ የሞቱት ሁለት ሰዎች ሰሞኑን ከተከሰተው የወጣቶች  ተቃውሞና ሰልፍ ጋር አይገናኝም፡፡

ጊዜያዊው የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ሰሞኑን ሁከትና ተቃውሞ የተነሳባቸው አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ ሰፍኖ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች እንደወትሮው እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ኮሚቴው ገለልተኛ ሆኖ የህግ የበላይነት ማረጋገጥና የህዝብ ሰላምና ደህንነት የመጠበቁን ተግባራት በቋሚ ስፍራዎች ሰራዊት በመመደብና  በተንቀሳቃሽ መኪኖች በመታገዝ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የጥምር ኮሚቴው አባልና የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌታቸው አስረስ “በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሁለት መቶ ተጠርጣሪዎች መካከል ከጉዳዩ ጋር የማይገናኙት እየተለቀቁ ናቸው” ብለዋል።

ሌሎቹን መርማሪዎች ቃል እየተቀበሉ ይገኛሉ፤መረጃና ማስረጃ እየተሰባሰበባቸው በመሆኑ ይህ እንደተጠናቀቀ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ብለዋል፤ ታዳጊ ወጣቶች ተገቢው ምክርና ትምህርት ተሰቷቸው መለቀቃቸውንም ተናግረዋል።

ጂቲ ዜድ በተባለ ስፍራ በተካሄደው ሁከትና ብጥብጥ ሶስት ሸጉጥና ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ መያዙን ተናግረዋል።

የጥምር ኮሚቴው አባል የፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ክላስተር ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ከበደ በበኩላቸው “ትላንት በመልካ ቀበሌ የተከሰተው ግጭት አስቀድሞም ለዓመታት የዘለቀና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሲፈጠር የነበረ እንጂ ከሰሞኑ ችግር ጋር አይገናኝም” ብለዋል፡፡

በግጭቱ ወደ አዲሱ ምድር ባቡር ሰው ሊያደርስ ሲጓዝ የነበረ ወጣት የታክሲ ሹፌርና አንድ ሌላ ሰው መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አምስት ሰዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ገልፀው ሌሎቹንም በቁጥጥር ሥር የማዋል ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

የፀጥታ አካሉ በድሬዳዋ አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት የጀመረው ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበት የተናገሩት ደግሞ የኮሚቴው አባል የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው፡፡

ችግሩ ከኃይማኖትና ከብሔር ግጭት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አስረድተው ለዚህም ሌት ተቀን የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን በመገንዘብ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

“አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ከሰፈነ በኋላ የፖለቲካ አመራሩ የወጣቱን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመፍታት ስራ ያከናውናል” ብለዋል፡፡

የጥምር ኮሚቴው ሰብሳቢ የምስራቅ ዕዝ የኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ፍስሃ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው ፀጥታው አስተማማኝ ደረጃ እስኪደርስ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት  እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ #ተጠናቋል። ዝርዝር #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መግለጫ_ይሰጣል

በዛሬው ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ በተተከለው የዛፍ ችግኝ መጠን ላይ በደቂቃዎች ውስጥ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የዘመቻው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ያሰባሰበውን ዳታ በማጣራትና በማደራጀት ላይ መሆኑን ኮሚቴው ጨምሮ ገልጿል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መግለጫ

የ2011 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ተደረገ!

በ2011ዓ/ም ዓመታዊ የትምህርት ሰሌዳ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ ብሄራዊና ክልላዊ ፈተናን ደህንነት በማስጠበቅና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመንግሰት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ፈተናውን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን በመንግስትና በህዝቡ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለይም ተግባሩን በጠራ ዕቅድ የመምራትና የህብረተሰቡን ግንዛቤና ባለቤትነት የማሳደግ ብሎም ከማዕከል እስከ ትምህርት ቤት በተደራጀ ግብረሃይል መምራት ተችሏል፡፡

በዚሁ መሰረት ባለድርሻ አካላትና መላው ህዝብ ባደረጉት ርብርብ እጅግ በተረጋጋ የፈተና አካባቢ ፕሮግራሙን በማሳካቱ የአመቱ የፈተና አስተዳደር ስራው መሻሻል አሳይቷል፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው በፈተና አስተዳደሩ ሂደት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የፌዴራልና የክልል ተቋማት፣ ለፈተና አስፈጻሚዎች፣ ለመላው ተፈታኝ ተማሪዎች፣ የተማሪው ወላጆች እና በሂደቱ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ኤጀንሲውም የፈተና ደህንነትን የማሰጠበቅ ስራውን ከፈተና ዝግጅት እስከ ውጤት ገለፃ ለማሰቀጠል በመስራት ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ኤጀንሲው ፈተናው በተሰጠበት ወቅት የፈተና ህግ ጥሰት መፈፀማቸው በወቅቱ ከቀረቡ ሪፖርቶችና ተያያዥ መረጃዎች በመረጋገጡ የ68 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኤጀንሲው በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ፣ አማራ እና ቤንሻንጉል ክልሎች በሚገኙ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 846 ተፈታኞች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶች ያገኟቸውን ውጤቶች ማጣራትን የሚጠይቅ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ኤጀንሲው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የእነዚህ ተማሪዎች ውጤት በተለዩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ ውጤታቸው ተይዞ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረግበት ወስኗል፡፡ ስለሆነም ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው አካላት በተውጣጣ ግብረሃይል የሚያደረገው የማጣራት ስራ እንዲሳካና የጀመረውን የትምህርት ጥራት የማስጠበቅ ጅምር ስራ እንዲጠናከር የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዳይለይው በመጠየቅ፣ ለመላ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ይመኛል፡፡

ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አከራካሪው ፍኖተ ካርታ!

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው #መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል #ተችቶታል

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል ተችቶታል።

መግለጫው አክሎም "ፍኖተ ካርታው በምሁራን የተጠና ነው በሚል ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ሳይሰጥ ወደ ተግባር እየተለወጠ ነው" ሲል ይኮንናል። ፍኖተ ካርታው የተለያዩ የትምህርት ፖሊሲውን የሚነካ ሆኖ ሳለ የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችና የፖሊሲ ለውጥ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ውሳኔ #ሳያሳልፉና አስተያየት ሳይሰጡበት #ወደተግባር መግባታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጫው ተመልክቷል።

ከዚህ ባሻገርም ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ደረጃውን 6-2-4 ብሎ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት በቂ ማብራሪያ መሰጠት ነበረበት ይላል። "ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጠው በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሆኖ ሳለ የ8ኛ ክፍልን ፈተና ሃገራዊ ማድረግ ምን አመጣው?" ሲልም ይጠይቃል። "የትግርኛ ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ይወራረሳል" የሚለው መግለጫው፤ የሰባት ዓመት ሕፃን እነዚህን ቋንቋዎች በአንድ ላይ መስጠት #ማደናገር ነው ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-24-4

Via #BBC
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መግለጫ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ርዕሰ-መስተዳድሩ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ስለሚንቀሳቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ-ክሕነት ለማቋቋም ከቀረበው ጥያቄ በኋላ ከቤተ-ክርስቲያኗ ጋር ስላደረጉት ውይይት ንግግር አድርገዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia