TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Alert ወላይታ ሶዶ‼️

"ሰላም ፀግሽ በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገ ወጥ ቤቶችን #ከማፍረስ ጋር ተያይዞ ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ አለመረጋጋት እየተከሰተ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ይፈልግ፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ የታክሲ አገልግሎት እና አጠቃላይ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡" ታሪኩ ከወ/ሶዶ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🔝

ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድ ተናግረዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ #ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቀቅ #ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡ ይህንን ችግር በመረዳትም ለተማሩ ዜጎች ሐሳባቸውን በማዬት ብድር ለመስጠት እንዲቻል ፖሊሲዎች እንደሚመቻቹና አነስተኛና መካከለኛ ባለሀብቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በዓለም ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ መለኪያ መሠረት ኢትዮጵያ 159ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ 5 ዓመታት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ #በማሻሻል በመለኪያው ከ100 በታች ለማድረግ በእርሳቸው የሚመሩ 10 ተቋማት ተለይተው ወደ ለውጥ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአሠራር ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች እና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተቃርኖ የተሞላ አሠራርን መከተላቸው ኢትዮጵያ በቀላሉ ሥራ (ቢዝነስ) የማይሠራባት ሀገር እንድትሆን ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ወር ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ #የሚመራው እና 10 ተቋትን ያካተተው ልዩ ኮሚቴ (ስትሪንግ ኮሚቴ) አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች በየወሩ የውጤት ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት እንዲመዘገብ ‹‹ያለንን የተፈጥሮ ሀብት #በአግባቡ መጠቀምና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ አዳዲስ ሐሳብ፣ ዕውቀትና ክሕሎትን በተቀናጀ መልኩ አሟጦ መጠቀም ይጠይቃል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስካሁን ያለው አካሄድ በተቃርኖ የተሞላ፣ ዘመናዊ አሠራርን ያልተከተለ፣ ተወዳዳሪነት የሌለውና በአነስተኛ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎችን በቀላሉ የማይጠቅም በመሆኑ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ ውስብስብ የሆነ አካሄድን መጠቀምና የገንዘብ አቅርቦት ችግር ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከችግሩ ለመውጣት የአሠራር ሥርዓትን ማቅለል፣ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግና ምቹ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ነው ያብራሩት፡፡

ለሥራዎች ገንዘብ የማቅረብ ሂደቱን ቀላል ማድረግ፤ እስካሁን ቋሚ ንብረት ይያዝ የነበረበትን የባንኮች አሠራር በቀጣይ ሐሳብን በማስያዝ ወጣቶች ብድር የሚወስዱበት ሁኔታ እንዲፈጥር ማድረግና የግል ተቋማት ውስጥ በቀላሉ ወደ ሥራ ተገብቶ ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹በአዲስ ዕውቀትና ሐሳብ ዕድገታችን ማስቀጠል አለብን፤ ለዚህ መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለግል ዘርፍ መስጠት አለበት፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀላልና ሳይንሳዊ የሆነ የአሠራር ሥርዓትን መዘርጋት ይገባል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር ዐብይ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹አይቻልም›› ወይም ‹‹ሕጉ አይፈቅድም›› የሚሉ አመለካከቶችን በመስበር ሁሉም ተቋማት ለሀገር ሲሉ ቀና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ጅምሮቹ ወደ ውጤት እንዲያድጉ አሁንም ተቋማት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያለፈው አንድ ወር አፈጻጸም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ በኳታር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር #ሳሚያ_ዘካርያ በትናንትናው እለት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኳታር መንግስት አሚር ልኡል ሸክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ አቅርበዋል። የኳታር አሚር ልኡል ሸክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ የሹመት ደበዳቤውን በተቀበሉበት ወቅት ባደረጉት ንግግር አምባሳደር ሳሚያ በኳታር በሚኖራቸው ቆይታ በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል። አምባሳደር ሳሚያ በበኩላቸው በአምባሳደርነት ዘመናቸው የኢትዮጵያ እና የኳታርን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እየጨፈርን #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!"
.
.
"ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ #አይደለንም! እኛ #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት #ከመፈጠር እንጂ #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡ በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት? ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ #የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ ምክንያቱም #ይቅርታ እንጂ #በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡ ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡ #እየጨፈርን የናድነውን ቤት #እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡ ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ፤ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ፤ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል፤ የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት! እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡" ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ

#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ ናቸው #ባላቸው ግንባታዎች ላይ የማፍረስ #እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመረጋጋት ረገብ ብሏል። ከተማዋም ወደቀደመ #ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለገናሌ ዳዋ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ተነሺዎች የ3 ቢሊየን ብር #ካሳ መከፈሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የገናሌ ዳዋ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል በባሌና ጉጂ ዞኖች አዋሳኝ ላይ እየተገነባ ይገኛል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች #አዋሳኝ አካባቢዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ ርዕሰ መሰተዳደሮች ገለፁ፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ #አወል_አርባ ዛሬ በአዲስ አበባ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ችግር መፍትሄ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች አንድም ሰው እንዳይሞት እና ግጭት እንዳይከሰት የማድረግ ሰራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን እንዲቋቋምና ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ እደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ጉዳይ ላይም በህዝብ ለህዝብ #ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ክልሎቹ #ከማንነት እና #ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

"ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ሊማሊሞ ባስ #ተበላሽቶ ደጀን ከቆመ 7:00 ሰአት አልፈ። ተሳፊሪዎች ብዙ እየተጉላላን እንገኛለን(የታመሙም ህፃናት አሉ)፤ ስንደውልም ምላሽ የሚሰጠን አካል ጠፍቷል። የሚመለከተው አካል ለችግሩ መፍትሄ ቢፈልግልን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dine with PM ABIY AHEMED FOR SHEGER...

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ #ለሀገር ውስጥና #ለውጭ ሀገር ባለሃብቶች በቤተ-መንግስት የእራት ግብዣ ያደርጋሉ። መግቢያ 5 ሚሊዮን ብር ሲሆን ገቢው አዲስ አባባ #ለማስዋብ ይወላል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia