TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Telegram : የቴሌግራም መስራች እና ዋናው ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ፍርድ ቤት በ5 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 5.56 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ተለቆ ጉዳዩን እንዲከታተል ወስኖለታል። ከፈረንሳይ እንዳይወጣ ግን ታግዷል። እገዳው ተጨማሪ ምርመራ ስለሚደረግ ነው የተጣለው። በሳምንት ሁለት ጊዜ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል። ዱሮቭ ከቀናት በፊት ፓሪስ አቅራቢያ ኤርፖት ተይዞ…
#Telegram

የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቨል ድሮቭ ፓሪስ ውስጥ ታስሮ በዋስ ከተለቀቀ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ አስተያየት ሰጥቷል።

ዱሮቭ ምን አለ ?

አብረውት ለነበሩትና ለደገፉትና ፍቅራቸውን ላሳዩት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።

ባለፈው ወር ፓሪስ በደረሰ ወቅት 4 ጊዜ በፖሊስ ኢንተርቪው ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።

በዚህ ወቅት የፈረንሳይ ባለስልጣናት ከቴሌግራም ምላሾችን ስላላገኙ ምናልባትም ለሌሎች ሰዎች ህገወጥ የቴሌግራም አጠቃቀም በግል ዱሮቭ ተጠያቂ እንደሚሆን እንደተነገረው አመልክቷል።

ይህ ግን በብዙ ምክንያቶች አስገራሚ እንደነበር አስረድቷል።

- ቴሌግራም የአውሮፓ ህብረት ጥያቄዎችን የሚቀበል እና የሚመልስ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ኦፊሴላዊ ተወካይ አለው። ይፋዊ ኢሜልም አለው።

- የፈረንሳይ ባለስልጣናት እርዳታ ለመጠየቅ ዱሮቭን ለማግኘት ብዙ መንገዶች ነበሯቸው። እንደ አንድ የፈረንሳይ ዜጋ በዱባይ በሚገኘው የፈረንሳይ ቆንስላ ተደጋጋሚ እንግዳም ነበር። ከጥቂት ጊዜ በፊት ደግሞ በግሉ በፈረንሳይ ያለውን የሽብርተኝነት ስጋት ለማስወገድ ከቴሌግራም ጋር የስልክ መስመር እንዲፈጥሩ ረድቷቸዋል።

- አንድ ሀገር በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ደስተኛ ካልሆነ በራሱ በአገልግሎቱ ላይ ህጋዊ እርምጃ መጀመር ነው። ከቅድመ ስማርት ስልክ በፊት የነበረ ህግ አምጥቶ በመተግበሪያው ላይ በሶስተኛ ወገኖች ለሚሰራ ወንጀል የድርጅት ስራ አስፈጻሚን ተጠያቂ ማደረግ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም። ቴክኖሎጂን መገንባት በራሱ ከባድ ነገር ነው። ማንም ኢኖቬተር ሌሎች አላግባብ ለሚጠቀሙት አጠቃቀም እሱ በግሉ እንደሚጠየቅ ካወቀ አዲስ ነገር አይፈጥርም።

በግላዊ መረጃ እና በደህንነት መካከል ትክክለኛውን ሚዛን መፍጠር እንዲሁ ቀላል እንዳልሆነ ዱሮቭ ገልጿል።

አንዳንድ ጊዜ ይህን ሚዛን በመጠበቅ ጉዳይ ከሀገራት ተቆጣጣሪዎች ጋር መግባባት ሳይፈጠር ሲቀር ቴሌግራም ሀገራቱን ለቆ እንደሚወጣ አመልክቷል። ይህንን ብዙ ጊዜ እንዳደረገ ገልጿል።

ለአብነት ፦ ሩስያ ለስለላ " የኢንክሪፕሽን ቁልፎችን " መጠየቋን ተከክሎ ቴሌግራም አልሰጥም በማለቱ ሩስያ ውስጥ ቴሌግራም ታግዷል።

ኢራን የሰላማዊ ሰልፎችን ቻናሎች ብሎክ እንዲደረግላት ጠይቃ ቴሌግራም " አላደርገውም አይቻልም " በማለቱ ኢራን ውስጥ ታግዷል።

ዱሮቭ ምስራዎች የሚሰሩት ለገንዘብ ባለመሆነ ከቴሌግራም መርህ ጋር የማይሄድን ገበያ ለቆ ለመውጣት ሁሌም ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ ሁሉ ማለት ግን ቴሌግራም ፍጹም ነው ማለት እንዳልሆነ ዱሮቭ አመልክቷል።

የመንግሥት አካላት / ባለስልጣናት ጥያቄያቸውን የት መላክ እንዳለባቸው ግራ ይግባሉ ይህንን ማስተካከል አለብን ብሏል።

ነገር ግን በአንዳንድ ሚዲያዎች ቴሌግራም የስርዓት አልበኞች መፈንጫ ተደርጎ የሚቀርበው ፍጹም ሀሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።

" በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎጂ ፖስቶችን እና ቻናሎችን እናስወግዳለን " ያለው ዱሮቭ በየዕለቱ ግልጽነት መፍጠሪያ ሪፖርቶችም እንልካለን ብሏል።

መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ጋር አስቸኳይ የሞደሬሽን ጥያቄዎችን በፍጥነት ለማስተናገድም የቀጥታ ስልክ መስመሮችም አሉን ሲል አክሏል።

" ሆኖም ግን ይህ በቂ አይደለም የሚሉ ድምፆችን እንሰማለን " ያለው ዱሮቭ " የተጠቃሚዎች ብዛት ወደ 950 ሚሊዮን መድረስ ወንጀለኞች የእኛን መድረክ አላግባብ ለመጠቀም ቀላል አድርጎላቸዋል። በዚህ ረገድ ያሉ ነገሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል የግል ግቤ አድርጊያለሁ " ብሏል።

ይህ ሂደት በውስጥ በኩል መጀመሩን ጠቁሞ በቀጣይ ስላለው ሁኔታ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ አሳውቋል።

ያለፈው ወር ክስተት ቴሌግራም እና የማህበራዊ አውታረመረብ ኢንዱስትሪን በጠቅላላ ደህንነቱ የተጠበቀና ጠንካራ እንደሚያደርገው ተስፋ እንዳለው ዱሮቭ ገልጿል።

#TikvahEthiopia
#Telegram

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ

ዛሬ ንግድ ባንክ የዶላር መግዣ ላይ ጭማሪ በማድረግ ወደ 108 ብር ከ0728 ሳንቲም አስገብቷል።

መሸጫው 119 ብር ከ9608 ሳንቲም ነው።

በአቢሲኒያ ባንክ አንዱ ዶላር 108 ብር ከ0729 ሳንቲም መግዣ ፤ 121 ብር ከ0416 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦላታል።

በወጋገን ባንክ የዶላር መግዣው 115 ብር ከ0121 ሳንቲም ነው።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ107 ብር ከ8383 ሳንቲም እየገዛ በ120 ብር ከ7789 ሳንቲም ለመሸጥ ቆርጧል።

(የዛሬ ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ/ም የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ከላይ ይመልከቱ)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል። የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል። @tikvahethiopia
ዘንድሮስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይገለጻል።

ትምህርት ሚኒስቴር በፈተናው ውጤት ዙሪያ ነገ ከሰዓት ማብራሪያ ይሰጣል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያውን ተከታትሎ ያቀርባል።

ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መረጃ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701,749 ተማሪዎች መካከል 684,205 ተማሪዎች ወይም 97.5 በመቶዎቹ ፈተናውን ወስደዋል።

ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶችና ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን አልወሰዱም።

ከተፈታኞቹ ውስጥ 29,718 የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን የወሰዱ ናቸው።

የብሔራዊ ፈተናው ውስጤት ነገ ሰኞ ጳጉሜን 4/2016 ዓ/ም ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፉት ዓመታት በተለይም ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) አስገብቶ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት / በብዛት ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የማያስመዘግቡበት መሆኑ ይታወቃል።

ለአብነት በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ 845,099 ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አምጥተው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

ከዛ በፊት በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው 50 በመቶና በላይ አምጥተው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር በቀጥታ የሚያልፉ ተማሪዎች ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ የሬሜዲያል ፕሮግራም በመስጠት ያን ያለፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።

ይህ ስራ " ለአንድ ጊዜ ብቻ " ተብሎ የነበረ ሲሆን በ2015 ቀጥታ ያለፉ ተፈታኞች ውስን በመሆናቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ቃላቸውን ስላጠፉ በይፋ ይቅርታ ጠይቀው የሬሜዲያል ፕሮግራሙ እንዲቀጥል አድርገው ነበር።

° ዘንድሮውስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?
° ምን ያህል ተማሪ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘግባል ?


ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል።

ነገ ከሰዓት የፈተናው ውጤት በትምህርት ሚኒስቴር ይገለጻል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ ተከታትሎ ያደርሳችኋል።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ውጤት

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👆የቀጠለ

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ውጤት : የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል። በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284 ► በቴሌግራም ቦት 👉 https://publielectoral.lat/EAESbot ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም…
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ውጤት የሚታየው ፦

► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 https://publielectoral.lat/EAESbot ላይ ነው።

ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት።

በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት ከ684 ሺህ በላይ ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች (5.4 በመቶ) ናቸው በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት።

ምንም እንኳን በተማሪ ቁጥር ደረጃ ከአምናው የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የትምህርት ዘመንም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👏

በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከ600ው በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ (575 እና 538) ከፍተኛውን ውጤት አምጥተው የሰቀሉት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

ከዚህ ባለፈ እጅግ በርካታ ሴት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት በማምጣት የዘንድሮውን ፈተና ሰቅለዋል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በተሰጠው ከ700 ፈተናም ሴቶች ከፍተኛ አኩሪ ውጤት ነው ያስመዘገቡት።

ከላይ ለማሳያ የተወሰኑ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፎቶ ይያዝ እንጂ ሌሎችም በርከታ ሰቃይ ሴት ተማሪዎች አሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ " ዜጎች በሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ወደ ማይናማር እና ታይላንድ ከመጓዝ ሊታቀቡ ይገባል " ሲል አሳስቧል። ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ዜጎች ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል። " ዜጎች ባልተረጋገጡ አማላይ ማስታወቂያዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው " ብለዋል። "…
🔈#ይነበብ

(በድጋሚ የተለጠፈ)

ወጣቶችን ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ?

በኦንላይን ወይም በደላሎች አልያም በኤጀንሲዎች " እዚህ ሀገር ጥሩ ስራ አለ ፤ ክፍያውም ከፍ ያለነው " ተብለው ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ሀገራት ይዘዋወራሉ።

ለአብነት ያህል ወጣቶች ከሚዘዋወሩባቸው ሀገራት መካከል የሳይበር ማጭበበር ( Cyber Scam) ማዕከላት ተብለው ወደ ሚታወቁት ፦
• ማይናማር ፣
• ካምቦዲያ፣
• ላኦስ
• ማይናማር ታይላንድ ድንበር
• ቻይና ማይናማር ድንበር በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

እነዚህ አካባቢዎች ባሉ የተለያዩ ቦታዎች በኦንላይን ማጭበርበር ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች አሉ።

በእርግጥ መጀመሪያ ላይ ወጣቶቹን " እልካችኋለን " የሚሏቸው ሌሎች በኢኮኖሚና ደህንነት እጅግ ጠንካራ ፣ ጠንካራ ባይሆኑም እንኳን ያን ያህል የከፋ ሁኔታ ላይ ወደማይገኙ ሀገራት ነው።

እዛ ቦታ ከደረሱ በኋላ ግን የሚልኳቸው ወደ ጎረቤት ድሃ እና የህግ ስርዓት ወዳልጠነከረባቸው ሀገራት ይሆናል።

የሚሰራው ማጭበርበር ምንድነው ?

ስራ ብለው የሚልኳቸው መጀመሪያ ፦
- የኦላንይ ግብይት ስራ ማቀላጠፍ
- የኦንላይን ሴልስ ስራ
- የሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- የማርኬቲንግ ስራ ... ሌላም ሌላም ነው።

ነገር ግን ስራ አለበት ወደ ተባለው ስፍራ ሲሄዱ የሚሰሩት ስራ መጀመሪያ ላይ ከተነገራቸው ተቃራኒ ነው።

የየራሳቸው ጋንግ አለቆች ባላቸው እጃቸውም ረጅም በሆኑ ሰዎች በሚመሩ የማጨበርበር ተግባር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች ያስገቧቸዋል።

እነዚህ ሰዎች ስልክ / ኮምፒየተር የሚያቀርቡላቸው ሲሆን በዛም ዓለም አቀፍ የማጨበርበር ስራ ላይ ያሰማሯቸዋል።

🔴 ዴቲንግ 🔴

የመጀመሪያ ስራቸው ከኢንተርኔት ላይ ውብ የሆኑ ሴቶችን / ስኬታማ ሴቶችን / ስኬታማ ወንዶችን ታዋቂ ሰዎችን ፎቶ በማውረድ የውሸት አካውንት መክፈት ነው።

በመቀጠል የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ። ምናልባትም በቅርብ የሚያውቋቸውን ሰዎችንም ሊሆን ይችላል።

እነዛን ሰዎች ልክ እንደ ኖርማል ሆነው ያለ ማቋረጥ ጊዜ ወስደው ያናግሯቸዋል።

የትኛውንም ጊዜ ይፍጅ ማናገራቸውን ይቀጥላሉ።

ስለ ውሸት ስራቸው፣ ስለ ህይወታቸው እየፈጠሩ ያወራሉ። በዚህ ውስጥ ምንም ምልክት አያሳዩም።

ወደ ፍቅር ከወሰዷቸውና ከጣሏቸው እምነትም ካገኙ በኃላ መጨረሻው ወደሆነው ዓላማቸው ገንዘብ ማስላክ ይገባሉ።

" ለምን እኔ ምሰራው ስራ ላይ ኢንቨስት አታደርም / አታደርጊም " በማለት ለምሳሌ ክሪፕቶ  ላይ ብለው ገንዘብ ይቀበላሉ።

በቃ አለቀ ! ገንዘባችሁ ተበልቶ ይቀራል። በኃላም ብሎክ አድርገው ይሸኟችኋል። ቀጣይ ሌላ ሰው ታርጌት ያደርጋሉ።

ወጣቶቹ ይሄን ካላደረጉ ምናልባትም ኢ-ሰብአዊ ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይችላል።

⚫️ በጎ አድራጎት ⚫️

የውሸት ማንነት ፎቶ ተጠቅመው አካውንት ከፍተው (ሴትን በወንድ ወንድ ደግሞ በሴት ማንነት) አንድ ታርጌት ያደረጉትን ሰው ረጅም ጊዜ ያናግሩ እና ለእርዳታ / ለእርዳታ ድርጅታቸው ገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያሳምኗቸኣል።

እነዛ ሰዎች ላይ እምነት የጣሉባቸው ተጨበርባሪዎች በሀዘን ተሰብረው ገንዘባቸውን ይልካሉ። ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ይደረጋሉ።

🟡 ባለሃብት መምሰል 🟡

የውሸት ማንነት በመፍጠር ፣ ፎቶዎችን በመጠቀም በኦንላይን ሰው ያናግራሉ።

እንዲታመኑ ረጅም ጊዜ ሊወስዱም ይችላሉ።

ሰዎቹ ካመኗቸው በኃላ ገንዘባቸውን በጋራ አፍስሰው ስለሚሰሯቸው ስራዎች በማናገር ገንዘብ ያስልካሉ። ከዛማ ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ያደረጋሉ !

🟤 ደንበኞችን ማነጋገር 🟤

ይህም በተመሳሳይ በሀሰተኛ ማንነትና ስራ ከተለያዩ ሰዎች እያነጋገሩ በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል ነው።

ለምሳሌ ፦ እቃ የሚሸጡ አስመስለው ብር ካስላኩ በኋላ የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ።

🔵 ' ኮሜንት/ሬት በማድረግ ገንዘብ አግኙ ' 🔵

እነዚ አጭበርባሪዎቹ የውሸት ማንነት ተጠቅመው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ ወይም በሌላ መንገድ ተጠቅመው የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ።

" ጎግል ላይ ግቡና ስለዚህ ድርጅት ጥሩ አስተያየት ጻፉ ይከፈላችኋል " ይላቸዋል።

ከዛም የመጀመሪያውን ክፍያ በመፈጸም እምነት ያሳድራሉ።

" ይሄን ያህል ብር ከላካችሁ ይሄን ያህል ታገኛላቹ " በማለት የሰዎቹን ማንነት ይገመግማሉ። እስከዛ ድረስ ግን ገንዘብ መላካቸውን አያቆሙም።

የሚጭበረበረው ሰው ብዙ ብር ካስላኩት በኋላ የውሃ ሽታ ይሆናሉ።


በተጨማሪም ...

እንደ ፖሊስ፣ደህንነት፣ ባንክ ሰራተኛ ፣ እንደ ድርጅት ኃላፊ ሆነው የሚያስመስሉ አጭበርባሪዎችም አሉ።

ስራውን የሚሰሩት ሰዎችም ተጠቂዎች ናቸው።

ስራውን ካልሰሩ አሰቃቂ ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል።

እንደ ባሪያ ለረጅም ሰአትም ያሰሯቸዋል።

እንደ ቅርብ ጊዜ ሪፖርት ፥ በማይናማር፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ፣ ቻይና በመሳሰሉ ሀገራት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በኦንላይ ማጭበርበር ላይ ተሰማርተዋል።

ስራዎቹንም የሚያሰሯቸው ሰዎች እጃቸው በጣም ረጅም ነው።

#TikvahEthiopia
#CyberScam

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ቀረጥ_ነጻ

ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

ይኸው መመሪያ " መመሪያ ቁጥር 1023/2017 " ይሰኛል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች ?

የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡

1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-

ሀ/ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ ወይም ለህብረሰሰቡ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ :

- የትምህርት ተቋማት፣
- የጤና ተቋማት፣
- የሕጻናት፤ የሴቶች፤ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች

ለ/ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች

2. ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደአገር እንዲገቡ የተፈቀደ እቃዎች።

3. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሰረት ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት መሳሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና አክሰሰሪዎች፡፡

4. በብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች፡፡

ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች ከማህበራዊ ቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ
#አይችሉም

ሀ/ ከ8 መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎች  እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ለ/ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ሐ/ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች።


በዚህ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ እቃዎች ማስረጃዎች ማቅረብ የግድ ይላል።

ምን አይነት ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው ?

1. እቃዎቹ በእርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የእርዳታ የምስክር ወረቀት።

2. የእቃዎቹን ዝርዝር እና ዋጋ የሚያሳይ ኢንቮይስ፣

3. እቃዎቹ ለተገለጸው አላማ የሚውሉ መሆኑን እንዲሁም ስለእቃዎቹ አጠቃቃም ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑ የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው ከመንግስት መስሪያ ቤት የተጻፈ የድጋፍ ድብዳቤ።

#TikvahEthiopia #MinistryofFiance

@tikvahethiopia
ቤንዚን ?

በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።

ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።

በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።

በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።

በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።

ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።

በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።

ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።

ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia