TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጉምሩክ ➡️ “ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የኮንቴነር ዲመሬጅ በየቀኑ እየጨመረብን ነው ” - አስመጪዎች ➡️ “ ከዚህ ሳምንት አያልፍም ” - ጉምሩክ ኮሚሽን አስመጪዎች ፣ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን የሚተካ ' አዲስ መመሪያ ' በማውረድ እስከዛሬ ሲከፍሉት ከነበረው ቀረጥ ከእጥፍ በላይ ካልከፈሉ እቃቸውን መውሰድ እንዳይችሉ እያደረጋቸው መሆኑን ለቲክቫህ…
#Update

" ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው።

በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

ጉምሩክ ፤ " የሠነድ ምዝገባ እና ማጣራት ሂደቱን በአግባቡ እየሠራ ይገኛል " ብለዋል።

" የብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " ሲሉ አረጋግጠው " የቀረቡ ሠነዶች ያልተሟሉ እና ቀሪ ጉዳዮች ኖረው ተቀባይነት ያላገኙ ሠነዶች የሚስተናገዱት በዕለቱ የምንዛሪ ተመን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ " ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ " ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛ #የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል " ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#EthiopianCustomsCommission #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦ - በጎረቤታችን ኬንያ ፣ - በቡሩንዲ ፣ - በሩዋንዳ - በኡጋንዳ ተገኝቷል። ሀገራቱም ሪፖርት አድርገዋል። በነዚህ ሀገራት ውስጥ የታየው በሽታ በኮንጎ ካለው ጋር የተገናኘ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Mpox በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ነው።…
#Mpox🚨

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ ካወጀ በኃላ ስውዲን የሚጀመሪያውን ኬዝ አግኝታለች።

በቫይረሱ የተያዘው ሰው ወደ አፍሪካ የጉዞ ታሪክ አለው ተብሏል።

ፓኪስታንም በተመሳሳይ ሶስት በMpox ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች። 3ቱም ቫይረሱ የተገኘባቸው ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጉዘው ፓኪስታን የገቡ እንደሆነ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ቫይረሱ በተለይም አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳራጨ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜም በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኬንያ ፣ በቡሩንዲ ፣ በሩዋንዳ ፣ በኡጋንዳ ተገኝቷል።

በቫይረስ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው Mpox በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት / መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።

በአፍሪካ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ500 በላይ ሰዎችም ሞተዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

መረጃው  የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
የDSTV ክፍያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ በቀላሉ ይፈጽሙ!

⚽️ በጉጉት የሚጠበቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ እንዳያመልጥዎ የDSTV ክፍያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ በመፈጸም ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን onelink.to/fpgu4m ይጫኑ፤ ሕይወትዎን ያቅልሉ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ !


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የተማሪዎችድምጽ ° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች ° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን…
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

“ በህግ የሚገባቸው መሆኑን አረጋግጠን እናስተናግዳለን ” - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ኢንተርን ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሆነ እያለ፣ ምግብና ነጻ ህክምና መከልከላቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወቃል።

ቅሬታቸው ሰሚ እንዳታጣ ይባስ ብሎ ዛቻ እንደደረሰባቸው ገልጸው፣ “ ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል ” ነበር ያሉት።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ቅሬታ እንዳልደረሳቸው ገልጸው፣ “ ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል ” ማለታቸውን አሳውቀናችሁ ነበር።

ዛሬስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?

ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደገለጹት ለሚመለከታቸው ሁሉ ደብዳቤውን ቢያቀርቡም ምላሽ ባለማግኘታቸው ሳይመገቡ መስራት ፈተና እንደሆነባቸው ነው።

ቅሬታቸውን በደብዳቤ አስደግፈው ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት እንዳስገቡ፣ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈርሞ ቢልክም ኮሌጁ ለቅሬታቸው ምላሽ እንዳልሰጣቸው አስረድተዋል።

ቲክቫህም፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሥራ አስፈጻሚ የሺጌታ ገላው (ፕ/ር)ን የጠየቀ ሲሆን፣ ስልክ ለማንሳትም ሆነ ለተላከላቸው የፅሑፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ካቀረቡና ፍትሃዊ ከሆነ እንደሚታይላቸው የገለጹ እንደመሆኑ መጠን ጉዳዩን ከምን እንደደረሰ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት መንገሻ (ዶ/ር)ም ጥያቄ አቅርበንላቸዋል።

በምላሻቸው፣ “ኢንተርን ላይ ያሉ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ደሞዝተኞች ናቸው። ጥያቄው መንግስት ከሚከፈለን ደሞዝ በተጨማሪ በተለዬ የቀረበ ፍላጎት ነው። በህግ የሚገባቸው መሆኑን አረጋግጠን እናስተናግዳለን” ብለዋል።

“ ለተማሪዎቻችንም አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ” ያሉት ፕሬዜዳንቱ፣ “ወጭ መጋራት ላይ ለተነሳው ነጥብ ኮሌጅ አብሮ እንዲመለከተው ኃላፊነት ተሰጥቶታል” ብለዋል።

“ከህግ ውጭ ተማሪዎቹ ያልተጠቀሙት ነገር ወጭ መጋራት ውስጥ ተካቶ ከሆነም ኮሌጁ ያርማል” ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህ መዘለለ ላሉት ጥያቄዎች ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስራ አስፈፃሚ ፕ/ር የሺጌታ ምላሽ እንዲሰጡ ያመላከቱ ሲሆን ፕሮሰሩ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም።

(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ከህወሓት ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት የማይጨው ከተማ ከንቲባ አቶ የማነ ንጉስ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ፤ " ጉባኤው የተወሰነ ቡድን ለማጥቃት በችኮላ የተጠራ ነው " ብለዋል። በዚህም እሳቸው ጨምሮ በርካቶች ተቃውሞዋቸውን በመግለፅ ከመድረኩ መቅረታቸውን አመልክተዋል። የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮምሽን ሊቀ መንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " 14ተኛ ጠቅላላ…
#Tigray

" ሁሉንም የፓለቲካ ሃይሎች ያቀፈ መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ያስፈጋል " - ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች

በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ባይቶና፣ ሳወት፣ ናፅነት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ ፤ " ሳምንቱን በስርዓቱ ባለቤቶች መካከል በመካሄድ ያለው ህገ-ወጥ እንቃስቃሴና ፍጥጫ ተው መባል ይገባዋል " ብለዋል።

በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው ፍጥጫ ተከትሎ በህዝቡ የሚታየው መረበሽ ያወገዙት ሦስቱ  ተፎካካሪ ፓርቲዎች " ህግ እየጣሱ በህዝብ ካባ ስም ለመደበቅ የሚደረገው መሯሯጥ እናወግዛለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለቡድናዊ ጥቅም ሲባል በህዝብ ቁማር መጫወት መቆም አለበት "  ያሉት ፓርቲዎቹ " ደርጅታዊ ይሁን ቡድናዊ ጉዳይ ከህዝብ ህልውና ማጣበቅ እንፀየፈዋለን እንዲቆምም እናሳስባለን " ብለዋል።  

" የህዝብ ሰላም፣ ህልውናና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ  ፓለቲካዊ ተግባር ሲታይ የሚመለከተው የፀጥታ አካልና ህዝብ ያለማዳላት በአስቸኳይ የማስቆም ሃላፍነቱን መወጣት አለበት " ሲሉም ገልጸዋል።

" የተፈጠረው ፓለቲካዊ አለመረጋጋት ዋነኛ መፍትሄው ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ነው " የሚል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል።  

ፓርቲዎቹ ፤ ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መንግስት በአስቸኳይ የመመስረት ጥሪ በተደጋጋሚ ማቅረባቸውና ግን ሰሚ አለማግኘታቸው  አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ " - ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው። በዚህም ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው…
#ጉምሩክ🚨

" አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች አስወጡ !! " - ጉምሩክ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፦

" መንግስት ያወጣውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል።

በመሆኑንም ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ሰነዱ ተቀባይነት ባገኘበት እለት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ  ይደረጋል።

ከሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም በኋለ ሰነዳቸው በጉምሩክ ተቀባይነት ያገኙ እቃዎች ደግሞ በአዲሱ የውጭ የምንዛሬ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ  መሰረት በየእለቱ በሚኖረው የምንዛሬ ተመን ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ባለመገንዘብ የተነሳ እቃዎችን በደረቅ ወደብ ያከማቹ አስመጭዎች አስፈላጊውን የጉምሩክ ስነስርዓት በመፈጸም እቃዎችን ከደረቅ ወደቦች ሊያስወጡ ይገባል።

የጉምሩክ አዋጅንና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተላለፍ እቃዎችን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ በማከማቸት በገበያ ላይ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን። "

#EthiopianCustomsCommission

@tikvahethiopia
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ከታዋቂው አለም አቀፍ የስፒከር አምራች ኩባንያ ጄ ቢ ኤል ጋር በመተባበር አዲሱ የኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ አጅግ አስገራሚ የድምፅ ጥራት ይዞ መቷል፡፡ ሙዚቃ ላዳምጥ ፣ጌም ልጫወት እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ ልመልከት ቢሉ በኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ እስከሆነ ድረስ አያሳስብም፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
👆Addis Ababa University VMware IT Academy👆

@AAU_Tech www.vmware.com

VMware Associate and Professional Online Training and Certification Exam Preparation.

Registration:
August 12 to August 30, 2024
Class start: August 31, 2024

Training Schedule:
Check our telegram Channel
@AAU_Tech

Recognition:
Course completion certificates; and digital badges that accepted in USA, Canada. Students will get 70% discount vouchers for both Associate and Professional certification exam. Discount vouchers are valid for 10 to 12 months from date of issue

For Registration, please call
-Mobile: 0945-039478/ 0902-340070 Tel: 011-1-260194

Address: AAU/AAiT (5kilo campus)
Telegram channel: @AAU_Tech
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። የሌሎችም ምንዛሬ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጨማሪ ታይቷል።

(ንግድ ባንክ)

💵 አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 104.0934 ፤ መሸጫ 115.3244

💷 ስተርሊግ መግዣው 128.1856፤ መሸጫው 142.6853

💶 ዩሮ መግዣ 114.4293 ፤ መሸጫ 126. 7877

🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 324.8780 መግዣ ፤ መሸጫው 361.6181

🇦🇪 የUAE ድርሃ መግዣ 28.3398 ፤ መሸጫው 31.4004

በግል ባንኮች ደግሞ የአንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ከ103 ብር አንስቶ እስከ 119 ብር ድረስ መሸጫ ተቆርጦለታል።

(ዕለታዊ የባንክ ምዛሬ ከላይ ተያይዟል)

(ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም

@tikvahethiopia