TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሲዳማ ክልል በወንሾ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ወገኖቻችን ቁጥር 9 ደርሷል። 6 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋለም ሆስፒታል ይገኛሉ። በሌላ በኩል ፤ በዛው ሲዳማ ክልል በቡራ ወረዳ በድንገተኛ ውኃ ሙላት የሁለት ሕጻናት ሕይወት አልፏል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል፣ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የውሀ ሙላት አደጋ የሞቱ ዜጎች 11 መሆኑን የሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበራ ዊላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ ዘጠኙ የሁለት አባወራ ቤተሰቦች ሲሆኑ አንዱ 5 አንዱ ደግሞ 3 ቤተሰቦቻቸዉን ማጣታቸውን ገልጸዋል።

አንድ ግለሰብ ከገበያ ሲመለስ ከተራራ የወረደ ናዳ ላዩ ላይ በማረፉ ለህልፈት እንደዳረገው ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ በቡራ ወረዳ ወንዝ ሞልቶ ከአቅጣጫው ውጭ በመፍሰስ በአካባቢዉ ያለ ቤት ውስጥ በመግባት 2 ልጆችን ህይወት መቅጠፉን ተናግረዋል።


ከአካባቢው ተራራማነትና ያለማቋረጥ ከዘነበው ዝናብ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ተጨማሪ አደጋዎች ይከሰታሉ ተብሎ ስጋት አለ።

ይህንንም ተከትሎ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ ፣ የጤና ቢሮና ሌሎች ተቋማት የተወጣጣ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደስራ ተገብቷል ብለዋል።

" ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው " ተብለው ከተለዩ ስድስት ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎችን የማውጣት ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

ከቀያቸዉ ከተነሱትን ራቅ ያለ ቦታ ዘመድ ያለው ወደዛ ሲሄድ ሌሎች በት/ቤቶች ፣ በቤተእምነቶችና መሰል ቦታዎች እየተጠለሉ መሆኑን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaHW

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ  ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ የሚያከናውኑት ከሐምሌ 25 ቀን 2016 እስከ ነሀሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን የከተማው ትምህርት መምሪያ አሳውቋል።

መምሪያው ፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ት/ቤቱ በበጋ ወቅት ከሚያስከፍለው የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ከ20% መብለጥ አይችልም ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪ ፥ ትምህርት ቤቶች በምዝገባ ወቅት ደስታ ወረቀትንና መሰል ቁሳቁሶችን በየትኛውም የእርከን ደረጃ መጠየቅ እንደማይችሉ አሳውቋል።

ትምህርት መምሪያው በ2017 ዓ.ም መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ ት/ቤቶች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ውጪ (ከላይ በዝርዝር ከተገለጹት ውጭ) ክፍያ ጨምሮ የተገኘ ት/ቤት እርምጃ ይወሰድበታል ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Sidama

" በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " - አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ

በሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ግምገማ መደረጉን ተከትሎ በርካታ የፖሊስ አዛዥች ከስልጣን ሲነሱ በጥቂቶች  ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተሰምቷል።

ከሰሞኑ በክልሉ ሲካሄድ የሰነበተውን የግምገማና የውይይት መድረክ አሰመልክተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ " በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " ብለዋል።

" በዚህ መሰረት በተደረገ ግምገማ በክልሉ በተለያዩ ዞን ወረዳና ከተማ አስተዳደር ውስጥ
ባሉ መዋቅር ይሰሩ ከነበሩ አመራሮች ውስጥ ሰባት የፖሊስ አዛዦችና ሙሉ የአንድ ክፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲጀመር ታዟል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ አመራሮች መካከል ፦
- የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ፣
- የሆኮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
- የጨቤ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ይገኙበታል።

የዳዬ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከኃላፊነታቸው ታግደው ከመልካም አስተዳደር ችግሮችና ከህገወጥ ንግድ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች እንዲጣራ ታዟል።

በተጨማሪም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ በዞኑ ህገ-ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመምጣቱና መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ ችለዋል።

በወረዳ ደረጃ ደግሞ የሁላ ወረዳ፣ የአለታ ጩኮ ወረዳ፣ የቡርሳ ወረዳና የጠጢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ያሉ ጠቅላላ ማኔጅመንቱ ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው ተነግሯል።

በመድረኩ በርካታ ችግሮች የተነሱ ሲሆን ለአብነትም ኪራይ ሰብሳቢነትና ባለጉዳይን ማማረር ጎልተዉ የተነሱ ክፍተቶች ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia