TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሬ በሽያጭ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ " ሲል አሳውቋል።

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል ተብሏል።

የሰነድ መሸጫ ቦታ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ etauinfo@ethiopianairlines.com / eaainfo@ethiopianairlines.com ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ክረምቱ ይገባል በኛ በኩል ጊዜውን ከዚህ በላይ መግፋት አንችልም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " ምርጫው የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ፣ የበጀት እና ድምፅ የሚሰጥበት ቀን እና ጊዜ ይታሰብበት " - ተፎካካሪ ፖርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፀጥታ ችግር ምክንያት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣…
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎችን አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።

ቦርዱ ፦

👉 በአፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች

👉 በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች

👉 በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ

👉 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ይህንን ተከትሉ መስፈርት የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።

➡️ ከ18 አመት በላይ የሆናቸው
➡️ ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገሉ
➡️ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑ
➡️ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላቸው
➡️ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ መስራት የሚችሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ክፍት በሚሆነው የቦርዱን የማመልከቻ ሊንክ ፦ https://pw.nebe-elections.org/recruitment  በመጠቀም ማመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።

ቦርዱ ፤ የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እንደሚያበረታታ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።

ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።

ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።

ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።

ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።

ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።

ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣

በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣

በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

(ለተማሪዎች እና ለወላጆች)

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወር የሚቆይ የAI ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ናቸው።

ተማሪዎቹ ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ለተከታታይ 2 ወራት ለሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ፦
➡️ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➡️ ሮቦቲክስ፣
➡️ ፕሮግራሚንግ፣
➡️ ማሽን ለርኒንግ
➡️ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) እንደሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪ እውቀትና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ፦

👉 www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/

👉 forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#AI #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

° በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።

° የአለም የህጻናት አድን ድርጅት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን እያወዳረ ነው።


አፍሪካ በዓለም ' ዜሮ ዶዝ ' ህፃናት ከሚገኙባቸው አህጉራት በቁጥር ከፍተኛውን ደረጃ ትይዛለች። ይህም ማለት መደበኛ ክትባት ወስደው የማያውቁ 8.7 ሚሊዮን ህፃናቶች አሉ ማለት ነው፡፡

ከእነዚህ ህፃናት ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት የሚኖሩት በናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።

በተጨማሪም ወረርሽኝ ፣ ድህነት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ አለመረጋጋት፣ ግጭቶችናና ተያያዥ ምክንያቶች የክትባት መርሃግብሮችን እየተስተጓጎሉ ይገኛሉ።

የዓለም የህጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) እና ጂኤስኬ በመተባበር የክትባት አቅርቦትን እና አጠቃቀምን በተመለከተ ማንኛውንም አይነት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማወዳደር ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

የተመረጡ ኃሳቦች / ሥራዎች በፕሮጀክት እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ የገንዝብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ለማመልከት www.stc-accelerator.org ይጎብኙ።

የማመልከቻ ቀን እስከ #ግንቦት_16 ቀን 2016 ዓም ድረስ ነው።

ሁለተኛው የፈጠራ ጥሪ በ2017/2025 የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ( #INSA ) የ2016 ዓ/ም " National Cyber Talent Challenge Program " ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ወጣቶች በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

የታለንት መስኮች፦

- Cyber Security
- Cyber Development
- Embedded Systems
- Aerospace ናቸው።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአንድ ወር ይሰጣል።

አመልካቾች በዌብሳይት  https://talent.Insa.gov.et በመግባት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ +251904311833 ፣ +251943579970፣ +251904311837 ላይ ስልክ መደወል ይችላል።

@Tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ( #INSA ) የ2016 ዓ/ም " National Cyber Talent Challenge Program " ማዘጋጀቱን ገልጿል። በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ወጣቶች በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል። የታለንት መስኮች፦ - Cyber Security …
#INSA #ጥቆማ

የብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ምዝገባ መካሄድ ጀምሯል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በክረምት ፕሮግራም (Summer Program) አሰልጥኖ ማስመረቁን ገልጿል።

ተመራቂዎችንም ፦

° #እንደየችሎታቸው እና #እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤

° ኢመደአን (INSA) ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት #ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዳመቻቸ አመልክቷል።

ባለፉት ሁለት አመታት የተከናወኑ የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራሞችን መነሻ በማድረግ በ2016 በጀት አመት “ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ” ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የዚህ ቻሌንጅ ዋና ዓላማ በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ መስኮች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸዉን ሰዎች በመመልመል በዘርፉ ላይ ተጨባጭ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ብሄራዊ የሳይበር ሰራዊት (National Cyber Army) መገንባት ነው ተብሏል።

በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው እና እድሜያቸው ከ11 አመት ጀምሮ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

መመዝገቢያ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ነው።

መመዝገቢያ አድራሻው https://talent.insa.gov.et ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ከ3500 ዶላር እስከ 10 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ለግብርና መሻሻል የሚረዱ የቴክኖሎጂ ውድድር መጀመሩን " አዩቲ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ሄፈር ኢንተርናሽናል የውድድሩ አዘጋጅ ባሳወቀው መሠረት፣ የውድድሩ ዓላማ የአርሶ አደሮች ምርታማነትን መጨመር የሚያስችሉ፣ ድካም የሚቀንሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ማቅረብ ነው።

ወድድሩ ሲካሄድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የሚወዳደሩት ከ18 - 30 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑና ተገልጿል።

የፈጠራ ሀሳባቸውን በ #ኦንላይን ማስገባት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የውድድሩ አሸናፊዎች በምን መልኩ ይለያሉ ?

➡️ ተወዳዳሪዎቹ ከሚያቀርቧቸው የቴክኖሎጂ ሀሳቦች 30ዎቹ በዳኞች ይመርጣሉ፣
➡️ ዳኞች በተገኙበት 30ዎቹ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ፣
➡️ ከ30ዎቹ 10 ሀሳቦችን ዳኞች ይመርጣሉ፣
➡️ 10ሩ ተወዳዳሪዎች ለ10 ቀናት ይሰለጥናሉ፣
➡️ ከስልጠናው በኋላ የመጨረሻ የ3 ተወዳዳሪዎች ሀሳብ ይመረጣል።

የሽልማት አሰጣጡ በምን መልኩ ነው ?

1ኛ ለወጣው 10 ሺህ ዶላር፣

2ኛ ለወጣው 6 ሺህ 500 ዶላር፣

3ኛ ለወጣው ሀሳብ ደግሞ 3 ሺህ 500 ዶላር የሥራ ማስጀመሪያ እና የማበረታቻ ሽልማት ይደረግላቸዋል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱት 2 ውድድሮች የተለያዩ የግብርና ዘርፍ ላይ ያተኮሩ አጠቃላይ 12 የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ተግባር ላይ መዋላቸው ተነግሯል።

ማመልከቻ ፦ https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@TikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#INSA የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ያዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ምዝገባ እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ/ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል። እስካሁን በርካታ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። ምዝገባው እስከ ሰኔ 10 ድረስ መራዘሙ ተጠቁሟል። በሳይበር ደህንነት እና በተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች…
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ባዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ላይ ተመዝግበው ለ3ኛ ዙር ፈተና ያለፉ ነዋሪነታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ለሆኑ ፈተናው የሚሰጠው ከማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም እስከ ዓርብ ሐምሌ 12/2016 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

ወደ 3ኛው ዙር ፈተና ያለፉ ስም ዝርዝር በ ' INSA የሳይበር ታለንት ማእክል ' የቴሌግራም አድራሻ ➡️ https://publielectoral.lat/cteinsa ላይ በመግባት ማየት እንደሚቻልም ተገልጿል። #INSA

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን
#ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች።

ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል።

ምን መማር ይቻላል ?

- Android Kotlin Development Fundamentals
- Data Science Fundamentals
- Programming Fundamentals

ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?

ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው።

ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ።

ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ (
https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

43,500 የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎች ይፈለጋሉ ፤ ሞክሩት።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 የበጀት ዓመት ለሚያካሂደው የሁለተኛው ዙር የግብርና ናሙና ቆጠራ 43500 የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ቅጥሩ 1 ዓመት ነው።

ለሥራው ማመልከት የሚፈልግ ማንኛው ዜጋ በአካል መገኘት ሳይጠበቅበት ይህን የሌበር ማርኬት ፖርታልን
http://lmis.gov.et በመጠቀም ማመልከት ይችላል።

መስፈርቶቹ ምንድናቸው ?

➡️ የትምህርት ደረጃ ፡- በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያለው ሆኖ ፖርታል ላይ በተገላጸው መሠረት፣
➡️ የስራው ቆይታ ፦ 1 ዓመት
➡️ ቋንቋ ፦ ለሥራ የሚመዘገቡበትን አካባቢ ቋንቋ የሚችል
➡️ ፆታ ፦ አይለይም
➡️ የጤና ሁኔታ ፡- በገጠርና በከተማ ቀበሌዎች ተዘዋውሮ መስራት የሚችልና ለዚህም ፍቃደኛ የሆነ

ለመመዝገብ ምን መከተል ይገባል ?

1. በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሌበር ማርኬት ፖርታል ላይ ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መረጃውን
lmis.gov.et መሙላት፣

2. ምዝገባ ካጠናቀቁ በኋላ በስልካችሁ የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይደርሶታል፣

3. የደረሰዎትን የሰራተኛነት መለያ ቁጥር በመያዝ እና አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በመሄድ አሻራ መስጠትና ምዝገባውን ማጠናቀቅ።

መረጃው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ነው።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
#ጥቆማ #ጥንቃቄ 🚨

ይህ የተንጋደደና ለመውደቅ ጫፍ የደረሰ የመንገድ መብራት ምሰሶ ወድቆ በአስፓልቱ ላይ በሚተላለፍ ተሽከርካሪ እና በሰው ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት።

ይነሳ አልያም በአግባቡ ይጠገን።

ቦታው አዲስ አበባ ፣ ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን መሄጃ የትራፊክ መብራቱ ጋር ነው።

እንዲሁ ሊወድቅ እንዳለና እንደተንጋደደ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን የሚያነሳው እና የሚያስተካክለው አልመጣም።

ከከባዱ የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ወድቆ ጉዳት ሳይደርስ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው።

👉 ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
👉 ትራፊክ ማኔጅመንት

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia