TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር : -

1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣

2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣

3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ መሰረት መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ ማዘጋጀቱን ጠቁሟል።

በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ seneexit2016@gmail.com ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና እና የዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መቼ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የትምህርት ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ፥ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

#TikvahEthiopia

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተሰርዞ በድጋሚ ይሰጣል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ቀደም ብሎ ፈተናው ወጥቶ በወረቀት እትም እና በPDF መሰራጨቱንና ተማሪዎችም ሰርተው መግባታቸውን አመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ግን ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " ስላጋጠመው ፈተናው በድጋሜ  በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ብሏል።

ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ለፈተናው ተቀምጠው የነበሩ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተኑበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ተማሪዎች ምን አሉ ?

የጥዋቱም ይሁን የከሰዓቱ ፈተና ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ወጥቶ ተማሪዎች በበድን ሰርተውት እንደገቡ ገልጸዋል።

ሌላው ፈተናው ከብሉፕሪነቱ ጋር እንደማይጣጣም ፤ ትምህርቱንም የሚመዝን ፈተና እንዳልወጣ አመልክተዋል።

የባለፉት ፈተናዎችን እንዳዩና የዚህ አይነት ፈተና ግን እንዳልነበር ጠቁመው ፈተናው ማስተካከያ እንዲደረግበት አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ትላንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የዘንድሮው ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ብሎ ነበር።

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም፤ አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ሲል ነበር ያስረዳው።

ሚኒስቴሩ ይህን ቢልም  ፤ በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ፦
- የማኔጅመንት
- የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሜድስን
- የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ተማሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ ከሐምሌ 24 እከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም የሚካሄድ እንደሆነ ገልጿል።

የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መማር ፍላጎቱ ያላቸው የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ
https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር እንደሚጀምር ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤ ተመልክተናል።

ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል።

ደብዳቤው ከ2017 ትምህርት ዘመን ጀምሮ ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።

በዚህም፦

- የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የ2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 27 ድረስ ይሰጣል።

(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

ምንጭ ➡️ @tikvahuniversity
የNGAT ፈተና መቼ ይሰጣል ?

ትምህርት ሚኒስቴር ፥ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን አሳውቋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።

ለፈተናው የተመዘገቡ በየተመደቡበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው እንደሚሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name and Password፣ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#MoE

@tikvahethiopia
#MoE

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ " ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! " በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።

ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " ብለዋል ሚኒስትሩ።

" ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር " ገልፀዋል።

" የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል " ብለዋል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU #GAT አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡  በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ Via @tikvahuniversity
#MoE

ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጣችሁ ለነበራችሁ ተፈታኞች ፈተናው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

"ዩኒቨርሲቲው በእድሳት ላይ በመሆኑ" የፈተና ማዕከል መቀየር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ፈተናው መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም በሚከተሉት ሰባት ተቋማት ውስጥ እንደሚሰጥ አሳውቋል፦

1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡

የተሰጣችሁን የመፈተኛ ስም (Username) ተጠቅማችሁ በሚደርሳችሁ የመፈተኛ ማዕከል እና የፈተና ሰዓት (Exam Session) መሰረት ፈተናውን እንድትወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

(ፈተናው የሚሰጠበት ፕሮግራም ከላይ ተያይዟል፡፡)

Via @tikvahuniversity