TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

በዚህ ሳምንት ፤ በሲዳማ ክልል በበንሳ ወረዳ ፤ በንሳ ዋሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ሬዎ " በሚባል ቦታ በሁለት #ሞተር_ሳይክሎች ግጭት በተከሰተ የሞተር አደጋ የ3 ሰው ህይወት #ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ከመጠን በላይ ፍጥነትና ከአቅም በላይ መጫን የፈጠረዉ አደጋ መሆኑ የተነገረለት ይህ አሰቃቂ አደጋ ለማህበረሰቡ ታላቅ ድንጋጤ የፈጠረና በአንድ ሞተር ላይ ከሁለት በላይ ሰዉ መጫን ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ ያሳየ ነዉ ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጽያ አስተያየታቸውን የሰጡት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ከበደ ኬኔራ ፤ አደጋዉ በሁለት ሞተር ሳይክሎች ግጭት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዉ የሶስቱ ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ አንደኛዉ የከፋ አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኮማንደሩ ፤ አሁን ላይ የትራፊክ ህግን ሳያከብሩ ማሽከርከር በተለይም በሞተረኞች ላይ የሚታይ ችግር መሆኑን ገልጸዉ ይኸውም ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ለትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚችሉትን እንዲያደርጉና አሽከርካሪዎችም በተፈቀደዉ ፍጥነት ልክ እንዲያሽከረክሩ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

" በድርቅና በረሃብ እየተጎዳ ካለ ሕዝብ አጀንዳ መሰብሰብና ተሳታፊ መየት አዳጋች ነው " - ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ጦርነት ባይኖርም በሌሎች ምክንያቶች የተሳታፊ ልየታ እያደረገ አለመሆኑን አሳውቋል።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ምን አሉ ?

- በአሁን ወቅት በትግራይ ክልል ጦርነት ባይኖርም የተሳታፊ ልየታን እያደረግን አይደለም። 

- በተመሳሳይ አማራ ክልል ባለፈው የፀጥታ ችግር የተሳታፊ ልየታ ማድረግ አልተቻለም።

" በአማራ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ተሳታፊዎችን ለመለየት መሰናክል ሆኗል " መባሉ አሳማኝ ቢሆንም በትግራይ ክልል ጦርነት ከቆመ ከአመት በላይ በማስቆጠሩ እንዴት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላል ? በሚል ተጠይቀው ነበር።

አቶ ጥበቡ ታደሰ ፥ " ኮሚሽኑ ስራውን እንዳይሰራ የሚያስቸግረው የፀጥታ ችግሩ ብቻ አይደለም። ይልቁንም #በድርቅና በረሃብ እየተጎዳ ካለ ሕዝብ አጀንዳ መሰብሰብና ተሳታፊ መየት አዳጋች ነው። " ሲሉ መልሰዋል።

- በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለኮሚሽኑን ሥራ እንቅፋት እየሆነ ነው።  ያላቸውን የሀሳብ ልዩነት በኃይል አመራጭ ተግባራዊ የሚያደርጉ ታጣቂ ወገኖች ኃይልን ለመጠቀም የመረጡት የሀሳብ ልዩነት ስላላቸው መሆኑን ኮሚሽኑ ይረዳል፤ የሀሳብ ልዩነታቸውንም በጠረንጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ኮሚሽኑ ይሰራል።

- ኮሚሽኑ የሀሳብ ልዩነት ያላቸውን አካላት በጠረንጴዛ ዙሪያ እንዲወያዩ የልዩነት መንስኤዎቻቸውን በተመለከተ አጀንዳ በመሰብሰብ ዘላቂ ሰላም የማምጣት እንጂ፣ በተሰጠው አዋጅ ኮሚሽኑ ጊዜያዊ ችግሮችን እየተዘዋወረ የመፍታት ኃላፊነት አልተሰጠውም።

በሌላ በኩል ፦

* በማረሚያ ቤት ያሉ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ ምሁራን እንደ አንድ የህብሰተሰብ ክፍል በአገራዊ ምክክሩ አጀንዳ እንዲሰጡ ካልተደረገ ውጤታማ ሆነ አካታች መሆን እንዴት እንደሚቻል፤

* ኮሚሽኑ የተሰጠው ጊዜ 3 ዓመታት እንደሆነ፣ ይሁን እንጂ 1 ዓመት እንደቀረው፣ በመሆኑም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን አጠናቆ ሰላም ለማምጣት እንዴት እንደሚችል ፤  ጊዜውን የማራዘም ሀሳብ እንዳለና እንደሌለ ... ኮሚሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር።

የኮሚሽኑ ምላሽ ፦

° በማረሚያ ቤት የሚገኙ አካላትን ተሳታፊ ለማድረግ ጉዳዩን ትኩረት ይሰጠዋል።

° የጊዜ ገደቡን በተመለከተ ሰራሁ ለማለት ብቻ የይድረስ ሥራ ከመስራት ጊዜ ወስዶ አመርቂ ሥራ ማከናወን ተገቢ ነው።

° ኮሚሽኑ ከ700 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች የተሳታፊ ልየታ ሥራ እያከያከናወነ ነው። በ327 ወረዳዎች የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮች ተመርጧል። በከፍተኛ የትምህረት ተቋማት ከሚገኙ ምሁራን፣ ከዲያስፓራዎች ጋር ውይይት ይደረጋል። ይሁን እንጂ በትግራይና አማራ ክልሎች ተሳታፊ የመለየት ሥራ እየተሰራ አይደለም።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቅርቡ በአዳማ አዘጋጅቶት በነበረ አንድ መድረክ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለሥራው ፈተና እንደሆነበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቶ እንደነበር ይታወሳል።

መረጃውን ታህሳስ 12 በኮሚሽኑ የተሰጠውን መግለጫ ዋቢ በማድረግ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
" የተሸለምኩትን 100 ሺህ ብር በትግራይ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ሠጥቻለሁ " - ዕበ ለገሠ

የግሉን አውሮፕላን ሠርቶ በሰማይ ላይ መንሳፈፍ የልጅነት ምኞቱ ነበር ፣ በሽረ እንደሥላሴ ከተማ ነዋሪ የሆነው ዕበ ለገሠ።

ሐሳቡን ወደ ተግባር ለመለወጥ እልህ አስጨራሽ ጉዞ ማድረጉን ይናገራል። ከበርካታ ጥረቶች በኋላ ለሦስት ደቂቃ ያህል መብረር የምትችል ሔሊኮፕተር መስራቱን እንደቻለ ገልጿል።

በስምንት ወራት ውስጥ ተሠርታ የተጠናቀቀችው ሔሊኮፕተሯ፣ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባት ዕበ ተናግሯል።

ለአብራሪው ብቻ የሚሆን ቦታ ቢኖራትም፣ እስከ አራት ሰው ወይም አራት ኩንታል ጭነትን ተሸክማ መብረር እንደምትችል ተናግሯል፡፡

ሔሊኮፕተሯ ተጠናቃ ወደ ሥራ ስትገባ፦
- ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎዎችን ለማጥፋት፣
- የአንበጣ መንጋን ለመከላከልና ቅኝት ለማድረግ ታገለግላለች፡፡ ሰዎች ለትራንስፖርት ሊጠቀሙበትም ይችላሉ ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረ የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ውድድር፣ ሔሊኮፕተር ሠርቶ በማቅረብ አንደኛ በመውጣት 100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የሽልማቱን ገንዘብ በትግራይ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንደሰጠ ዕበ ጠቁሟል፡፡

ሔሊኮፕተሯ ተሻሽላ ገበያ ላይ መዋል የምትችልና የተሠራችበት ቁሳቁስ ሙሉ በሙሉ በአካባቢ የሚገኙ መሆናቸው ዕበን ለአሸናፊነት አብቅቶታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ፈጠራውን ለማገዝ ቃል እንደገባለት የገለጸው ዕበ፣ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ነገር ይዞ ለመቅረብ እንደሚሠራ ተናግሯል፡፡ #ሪፖርተር

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰጠው የዕውቅና ፍቃድ ታገደበት። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባገኘው መረጃ ትምህርት ቤቱ ፦ - በሀገር አቀፍ እና በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ባለማድረጉ ተማሪዎች ከአማርኛ ትምህርት ውጭ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በእንግሊዝኛ…
#Update

የጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅና ፍቃድ ታግዷል።

ይህን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆነ ወላጆች " ግልፅ አይደለም " ያሉትን ጥያቄ አንስተው ምላሽ እንዲሰጥባቸው መልዕክት ልከዋል።

የወላጆች ጥያቄ ...

- ይፋ የሆነው ደብዳቤ የዋናው የባለስልጣን መ/ቤቱ ሳይሆን " የጉለሌ ቅርጫፍ ፅ/ቤት " ነው ለዋናው ባለስልጣን መ/ቤት በግልባጭ እንዲደርስ ነው የሚለው ፤ ውሳኔው ከላይ ጀምሮ የመጣ ነው ? ዋናው መ/ቤት በዚህ ጉዳይ ምንድነው የሚለው ? ውሳኔውን ያውቀዋል ?

- ይህ ውሳኔ አሁን በተማሪዎች ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላጆችን ጥያቄ ይዞ ይመለከታቸዋል ያላቸውን የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት አካላትን አነጋግሯል።

በዚህም ፤ በጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተወሰነው የዕውቅና ፍቃድ እገዳ ፦
* የዋናው የባለስልጣን መ/ቤቱ
* የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ... ሌሎችም የተለያየ #ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኃላ ውሳኔያቸው ያረፈበት ነው ብለውናል።

ምንም እንኳን የጉለሌ ቅንጫፍ ፅ/ቤት ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ ተለቆ ቢታይም የዕውቅና እገዳው ውሳኔ በአራት ክ/ከተሞች ማለትም ለሚኩራ፣ ንፋስ ስልክ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌን የሚመለከት ነው ሲሉ አስረድተውናል።

በአጠቃላይ 17ቱም የጊብሰን ቅርንጫፎች ላይ የተወሰነ ነው ሲሉም አክለዋል።

አሁን የተላለፈው የዕውቅና እገዳ ውሳኔ በዚህ አመት እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳትም ሆነ ተፅእኖ እንደማያደርስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት ለመስማት ችሏል።

የጊብሰን ትምህርት ቤት በጉዳዩ ላይ የሚሰጠን ማብራሪያ ካለ የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Tecno_Pop8

ከጥራት እና እጥፍ የአገልግሎት አቅም ጋር የቀረበው  አዲሱ ፖፕ 8 ሲሪየስ ከቴክኖ ሞባይል!

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
#Hawassa

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል።

ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦

" ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር ' መኪና ባስቆሙ በተደራጁ ዘራፊዎች ተዘርፈናል ፤ በመሃል ከተማ በሳንጃም የግድያ ሙከራም ተደርጎብናል። "

👉 የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

" ... ' ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን ' የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሮዬም ሆነ ስልኬ ክፍት ነው። ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም "

👉 የታቦር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

" . . . ተጎጅዎች ' በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል ' የሚሉት የተሳሳተ ነው። በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር ታሪክ የሆነ ጉዳይ ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል። ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። 👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦ " ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር…
#Hawassa

የራስሰው ገዛኸኝ የተባሉ ግለሰብ ሀዋሳ ላይ የተደራጀ ዝርፊያ እና ሳንጃ በማውጣት የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈው አሰራጭተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ መልዕክት በውስጥ ደርሶት ተመልክቷል። የሀዋሳ ፖሊስንም ስለጉዳዩ ደውሎ ጠይቋል።

" በሀዋሳ ከተማ ላይ የተደራጀ የዝርፊያ እና የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብናል " ያሉት የራሰው ገዛኸኝ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ መሰረት ፦

- ድርጊቱ የተፈፀመው ሀዋሳ፣ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ " ቦሌ መንደር " አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ መብራት ጋር ነው።

- ቀኑ 12/04/2016 ዕለተ #አርብ ከምሽቱ 12:30 ላይ ነው።

- ሲያሽከረክሩት የነበረው ላንድ ሮቨር መኪና ሲሆን ውስጥ እንግዶቻቸው ከሆኑ 3 የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሲጓዙ ነበር።

- በተለምዶ " ቦሌ መንገደር  " የትራፊክ መብራቱ ጋር ሲደርሱ የሚያሽከረክሩት መኪና ከጎን በኩል በከፍተኛ ምት ይመታባቸዋል። አደጋ ያደረሱ ስለመሰላቸው መኪናውን ዳር በማስያዝ ያቆማሉ።

- በመኪናው ውስጥ ከነበሩት አንዱ ከመኪና ፈጥነው በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከቱም የደረሰ አደጋ የለም። ግን ሰዎች ተሰብስበዋል።

- የወረደው ሰው ከመኪናው ኃላ የተሰበሰቡ ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው በነበረበት ወቅት የራስሰው ገዛኸኝም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ ? ማለት ጥያቄ ይጀምራሉ።

- በዚህ ሁኔታ አስፓልቱ ዳር ከሚገኝ 2 ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ወጥተው ከበባ ያደርጋሉ፤ ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር " ባንጋ " የተባለ የሚጠራውን ሳንጃ ይዞ ማሳደድ ይጀምራል።

- በተፈጠረው ሁኔታው #ተደናገጠው ቢያፈገፍጉም ወጣቱ ሊተዋቸው ባለመቻሉ ወደ መኪናው ለመግባት ሲሞክሩ እዛው ጋር የነበሩት ሌሎች ወጣቶች በሩን እንዳይገቡ ይይዙታል።

- ሁኔታው በተደራጀ መልኩ #ዘረፋ መሆኑ ስለገባቸው በሳንጃው ላለመወጋት ይሸሻሉ።

- በዚህ መካከል ከመኪና ውስጥ ያልወረዱት ሰዎች መኪናውን ሎክ ለማድረግ ቢሞክሩም ሌሎች ወጣቶች ከኃላ በር በመክፈት፦
* ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣ
* ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለሱ በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣
* መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰውረዋል።

- አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን ተመልክተው " ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ #ይገሏችኋል " በማለት አከባቢውን ለቀው እንዲሸሹ ያስፈራሯቸዋል።

- በተጠና ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ኦፕሬሽን በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የፓሊስ አካል እስኪመጣ ጠበቁ።

- በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል ይመጣል። ቀርቦ ምንድነው ? ሲል ይጠይቃል። እነሱም የደረሰባቸውን የዘረፋ ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተው የህግ ከለላ ቢጠይቁም። ፓሊሱ " በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል ? " በማለት መልሷል።

- የፖሊስ አባሉ ቢያንስ እንኳን #ፓትሮል ደውሎ ኃይል እንዲያስጨምርላቸው ቢነግሩትም ፤ " እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

- ወደ አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለውም እንዲደርሱላቸው ፤  የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም ከባለስልጣኑ ዘንድ ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም።

- ወደ ተለያዩ የህግ አካላት በመደወል #ከ40_ደቂቃ በኃላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል ሊመጣ ችሏል።

- የመጡት የፖሊስ አባላት ችግሩን ለመስማት የሞከሩ ሲሆን " የዘራፊዎችን ማንነት እና ስም " ከተፈራፊዎች ይጠይቃሉ። እነሱም መንገደኛ በመሆናቸው ገልጸው የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይቶ ለፓሊስ መናገር የሚችሉበት መንገድ ስላልገባቸው ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪ እና ፑል ቤት አሳዩ።

- ከፍተኛ #ክርክር እና አለመግባባት ከተፈጠረ በኃላ የፖሊስ አባላቱ የተፈፀመውን ነገር የዕለት መዝገብ ላይ እንዲያስመዘግቡ በማለት ወደ ታቦር ክፍለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሄዱ አድርገዋል።

- ፖሊስ " የፑል ቤቱ ባለቤቶች  " አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው አስረዋቸዋል። ነገር ግን ዋናዎቹ የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መልዕክት ከተመለከተ በኃላ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ፤ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ በከተማዋ ዉስጥ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በጅጉ የተሻለ ሰላም ያላት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ተፈፅሟል የተባለውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ሲያዩት #ማዘናቸዉን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ችግር ተፈጥሮ ከሆነ በተዋረድ ለሚመለከተዉ አካል ማቅረብ እንደሚቻልና በተለይ እንዲህ ያለዉን ጉዳይ እንኳን ፖሊስ የትኛዉም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ከማስቆም ወደኋላ እንደማይል ገለጸዋል።

አሁንም " ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን " የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሯቸዉም ሆነ ስልካቸዉ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጎጅዎች እንዲያመለክቱና ቃላቸውን እንዲሰጡ የተደረጉበትን የታቦር ክ/ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን አነጋግሯል።

እሳቸው በሰጡት ምላሽ በወቅቱ መኪናችን ተመታብን ያሉት አካላት ወደፖሊስ ጣቢያዉ በመምጣት ባስመዘገቡት መሰረት በአካባቢዉ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተይዘዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢ/ር ወንድዬ ፤ የተጠቀሱት ንብረቶች መሰረቃቸዉን በወቅቱ አለመስማታቸውን እና አለመመዝገባቸዉን አስታውሰዉ አሁንም ቢሆን ጉዳዩን በአግባቡ ወደሚመለከተዉ የህግ አካል በማቅረብ በተያዘዉ ምርመራ እንዲካተት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ተጎጅዎች " በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል " የሚሉት የተሳሳተ መሆኑን የሚያነሱት ኢንስፔክተሩ በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር #ታሪክ_የሆነ ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በቀድሞ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል የነበሩት አቶ ጃንከበድ ዘሪሁን ረቡዕ ጠዋት ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ/ም አባዶ 'መስቀለኛ' አካባቢ ከመኖሪያ ቤታቸው በፓሊስ ወደ ሜክሲኮ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደው እስከ 8፡00 ቢቆዩም ከዚያ በኋላ ወዴት እንደተወሰዱ ባለማወቃቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ቤተሰቦቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የፓሊስ አባላት ' በወቅታዊ ጉዳይ ' ብለው እንደወሰዷቸው ያስረዱት የአቶ ጃንከበድ የቅርብ ቤተሰብ፣  "ቢያንስ ያሉበትን ማሳወቅ መቻል አለባቸው የመንግሥት አካል እንደመሆናቸው። ቤተሰብ የመጠየቅ፣ የመጎብኘት፣ ጠበቃ የማግኘት መብቱን አላከበሩም። ያለበትን ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደሉም " ሲሉ ወቅሰዋል።

ሌላኛው ቤተሰብ በበኩላቸው፣ ፓሊስ ጋ ካለ ' እኛ ጋ አለ ' እንዲሏቸው፣ የተጠረጠረበትን ጉዳይ በግልጽ እንዲያሳውቋቸው ጠይቀው፣ " ኮንፈርሜሽን ለእኛ ትልቅ ርሊፍ ነው። ለሕይወቱ በጣም ያስጋል " ብለዋል።

በተጨማሪም፤ ፍ/ቤት አልቀረበም። #የፈጸመው ወንጀል ስለመኖሩና ስለተጠረጠረበት በግልፅ #አልተነገረንም። እባካችሁ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ከሆነ መረጃ ይሰጡን ዘንድ የሚመለከተውን አካል ጠይቁልን፤ የደረሰበትን ማወቅ አልቻልንም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአቶ ጃንከበድ ቤተሰቦች ጥያቄ ይዞ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስን አነጋግሯል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚሰሩት ዋና ኢንሰፔክተር ታደለ ፣ " በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለሆነ አንድ ሰው ብቻ አይደለም እዚህ ላይ ሀሳብ መስጠት ያለበት " ብለዋል።

" እዚህ ላይ እኔ የማውቀው፣ የሰማሁት ነገር የለም። መረጃው የለኝም። ስለዚህ ጉዳዩ እኛን የሚመለከት አይደለም " ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፣ " በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ከሆነ፣ ይጠየቃል፣ ይጣራል ጉዳዩ ማለት ነው። በሕግ ሂደት የሚታይ ይሆናል " ብለዋል።

ታዲያ እዲህ ቢሆን እንኳ ተጠርጣሪዎች ያሉበትን ቦታ ማሳወቅ የለባችሁም ወይ ? ሌላ ጭንቀት ቤተሰብ ላይ ከሚፈጥር ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢንስፔተሩ፣ " የት ይሄዳል ያው ማቆያ ነው የሚሆኑት ሰው ሲያዝ፣ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ማቆያ ነው በሕግ እስኪወሰንበት ድረስ " ሲሉ አክለዋል። 

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማደር ማርቆስ ታደሰ በበኩላቸው፣ ስለጉዳዩ መረጃው እደሌላቸው፣ ማንኛውም የተጠረጠረ ሰው ሊያዝ እንደሚችል፣ ስለሆነም ተያዙ የሚባሉት ግለሰብ ምናልባት ተጠርጥረው በአድስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ተይዘው ከሆነም ሊቀመጡ የሚችሉት በተያዙበት ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ሊሆን እደሚችል ገልጸዋል። 

አክለውም፣ ተያዙ የሚባሉት ግለሰብ  እዛ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ሂደው መጠየቅ እደሚችሉ፣ ከዚህ ባሻገርም ወደ ፖሊስ ኮሚሽኑን ሂደው መጠየቅ እደሚችሉ አስረድተዋል።

መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦ " የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦ * ለአመራሮች ፣ * ለባለሙያዎች * ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት ሰጥቷል። ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ #ይቅርታ ጠይቋል። ቀጣይ የቴክኒክና…
#Update

ባለፈው ሳይሰጥ የቀረው የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ይሰጣል ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባለፈው ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ መላው ሰራተኞችን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና፦
- ለአመራሮች ፣
- ለባለሙያዎች
- ለሰራተኞች አርብ 12/04/2016 ሊሰጥ የነበረ ሲሆን ፈተናው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባጋጠመው " ቴክኒካል ችግር " ምከንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ መገለፁ ይታወሳል።

ሰራተኞች በእለቱ ከረፋዱ 5:00-11:30 ፈተናው ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን ከፍተኛ መጉላላት እና እንግልት ሲደርስባቸው ነው የዋለው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

ቢሮው በቀጣይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በኦረንቴሽን ወቅት የተቀመጡ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተው ለፈተና እንዲገኙ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia M-PESA

ወዝ ወዝ እንበል ፏ ባለ መኪናችን ወደ ህልማችን
እንመዝገብ እንገበያይ እናሸንፍ እድሉ አያምልጠን

የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether