TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል። በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።…
#NewsAlert

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡

" በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ ብሆንም የምንችለውን ሁሉ ግን ሰጥቻለሁ ፤ጥያቄየንም ፓርቲዬ ተቀብሎኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤትም የክልሉን ፕሬዜዳንት የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል። ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡ " በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ…
#NewsAlert

በአማራ ክልል አዲስ ፕሬዜዳንት ተሾመ።

ባለፉት ዓመታት በርካታ ፕሬዜዳንቶች የተፈራረቁበት አማራ ክልል ዛሬ አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሞለታል።

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዜዳንት በማድረግ ሹሟል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

የት የት ስፍራዎች አገልግለዋል ? የትምህርት ደረጃቸውስ ?

- መጀመሪያ ዲግሪያቸውን በልማት አስተዳደር ሰርተዋል።
- የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ረዳት የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ ነበሩ።
- የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።
- የክልሉን ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት በኃላፊነት ለአንድ ዓመት መርተዋል።
- የክልሉ ቴክኒክ ሙያ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።
- ወደ ክልል ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት፤ የምስራቅ ጎጃም ዞንን በምክትል አስተዳዳሪ እና በዋና አስተዳዳሪነት መርተዋል።
- እስከ ዛሬ ድረስ የአማራ ክልል የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።

ፎቶ፦ AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#NewsAlert የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በስበባውም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ሁኔታ ተመልክታል።

ምክር ቤቱ ፤ እኤአ ጥር 1 በኢትዮጵያ እና ሰሜናዊ የሶማሊያ ክልል ሲል በጠራት " ሶማሌላንድ " መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከተፈረመ በኃላ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ሁኔታው በቀጠናው ሰላም፣ ፀጥታ እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚልም ስጋት እንደገባው አመልክቷል።

ምክር ቤቱ ፦

እኤአ ጥር 3/2024 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የኢትዮጵያን እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሊከበር እንደሚገባው አፅንኦት የሰጡበትን መግለጫ እንደሚደግፍ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት መጠበቅ እንዳለበት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የሁለትዮሽ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነታቸውን የአፍሪካ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ህግ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ እንዲመሩ አሳስቧል።

የውጭ አካላት በሁለቱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ እንዲያከብሩ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ጠንካራ መልካም ጉርብትና፣ ወዳጅነት እና አብሮነት ትስስር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተጨማሪ እርምጃዎች እና መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አበረታቷል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትርጉም ያለው ውይይት እንዲያደርጉ እና ውጥረቶችን እንዲያረግቡ ጥሪ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ውይይት እንዲያመቻቹና በየወቅቱ ለምክር ቤቱ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ብሏል።

ኢጋድ በዩጋንዳ ካምፓላ ለነገ የጠራውን ልዩ የመሪዎች ስብሰባ በደስታ እንደተቀበለው ገልጿል።

ምክር ቤቱ ጉዳዩን በንቃት እንደሚከታተል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት አጽድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአቶ ተመስገንን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማጽደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / etv ዘግቧል። …
#NewsAlert

አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ሹመት አጽድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመትን አጽድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrDessalegnChane በ2013 ዓ/ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸውን ዋቢ በማድረግ አል አይን አማርኛው አገልግሎት ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ቤተሰብ አባል ፤ " ትናንት ጥር 22 ቀን…
#NewsAlert

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ እንደተወሰነላቸው ጠበቃቸው ተናግሩ።

በ2013 በተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው ቆይተዋል።

ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ፤ ደንበኛቸው ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በዛሬው ዕለት በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ እንደተነገራቸው ለአል አይን ኒውስ ተናግረዋል።

ይሁንና እስካሁን ድረስ ከእስር ስለመለቀቃቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መለቀቃቸውን የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ  ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከዚህ ባለፈው ድርገፁ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ)፣ የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው " በምህረት " ከእስር እንደሚፈቱ ከታመኑ ምንጮች መስማቱን ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአል ዓይን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦
ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ሌለው ውሳኔ የተላለፈበት ጉዳይ የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ላይ ሲሆን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።

ከዚህ በተጨማሪ " የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል " ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ፦
- ለጎዳና ህይወት ፤
- ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።

" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ #በስራ_ላይ_እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
#NewsAlert #Tigray

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በዚህም ፤ " ፓለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ " ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ ይታወሳል።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረዳ በዛሬ መግለጫቸው ላይ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችና ብዛታቸውን ባይገልጹም " የህግ የበላይነት ለማስከበር የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ አሳውወዋል።

የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበርና የህወሓት ጉባኤ ከመካሄድ ጋር ተያይዞ  የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ተገቢ እና ጥብቅ የፀጥታ ስራ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እና እየከረረ መሄዱ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።

ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ደቅኗል የሚሉ አልጠፉም።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ግን ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት ፤ ማንኛውም ልዩነት ወደ ፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር የጸጥታ አካሉ እንደማይፈቅድ አስጠንቅቀዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Photo Credit - TG TV

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert🚨

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !! " - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)


በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።

በዚህም " በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ  አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው " ብለዋል።

" ህግ እና ስርዓት ከማንኛውም ሰው ፣ ተቋም ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ  የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ለገሰ (ዶ/ር) ፥ " የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው " ያሉ ሲሆን " ህወሓት ደጋግሞ  እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል " ብለዋል።

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል፡፡ " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ድርጊቱ  የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና  የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም  ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል " በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert🚨

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ምን አለ ?

- መመሪያው የሚመለከታቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች / የጭነት አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም 10 ኩንታል በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ነው።

- እነዚህ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከሰዓት 10:30 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ገደብ ተጥሎባቸዋል።

- በዋና መንገዶች ላይ ማቆም፤ ጭነት ማውረድና መጫን እንዲሁም መንቀሳቀስ በክልከላው የተካተቱ ናቸው።

- አዲሱ መመሪያ ከዚህ በፊት ከነበረው የሰዓት ገደብ ላይ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታስቦ የወጣ እንደሆነ ተመላክቷል።

- አዲሱ መመሪያ ከመስከረም 2/2017 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናትን አይመለከትም።

የተቀመጡ የቅጣት እርከኖች ምንድናቸው ?

➡️ በተከለከለ ሰዓት በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆሙ የ10ሺ ብር ቅጣት፤

➡️ በተከለከለው የሰዓት ገደብ የተንቀሳቀሰ 20ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት፤

➡️ በቅጣት ሂደቱ በድጋሜ የተቀጣ አሽከርካሪ የቅጣት እርከኑን በእጥፍ የሚቀጣ ይሆናል።

➡️ በተጨማሪ የቅጣት ወረቀት በመያዝ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀስ ትዕዛዝ ባለማክበር ተጨማሪ ቅጣት የሚተላለፍባቸው ይሆናል ተብሏል።

ቅሬታ ያላቸው በጹሑፍ ቅሬታቸውን ለባለሥልጣኑ በማመልከቻ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የባለሥልጣኑ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል።

ይህ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ከዚህ ቀደም የነበረውን መመሪያ ቁጥር 38/2013 እንዲሁም ሰርኩላሮች፣ ልማዳዊ አሰራሮች የሚሽር ነው።

ይህ መመሪያ ተግባራዊ የማይደረግባቸው የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው ?

1ኛ. የሀገር መከላከያ፤ የፖሊስ እንዲሁም በጸጥታ አካላት ስም የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች፤

2ኛ. የድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች፤

3ኛ. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎችን አይመለከትም።

ከዚህ ቀደም ወጥ አተገባበር ባልተስተዋለባቸው የውሃ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ አዲሱ መመሪያ እንዴት ይመለከተዋል ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳው ጥያቄ ፥ በአዲሱ መመሪያ እንደሌሎች ከባድ ተሽከርካሪዎች እንደሚስተናገዱ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia