TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot) ✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን (Trainee Aircraft Maintenance Technician) ✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic) ✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors) …
#ማስታወሻ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ምዝገባው ዛሬ ይጀምራል።

የስልጠና መጠሪያዎች ፦
✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን
(Trainee Aircraft Maintenance Technician)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic)
✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors)
✓ ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኢጀንት (Trainee Customer Service Agent) ናቸው።

አመልካቾች ለምዝገባ ፤ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒው፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ካርድ፣ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት ማረጋገጫ ካርድ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ማሟላት አለባቸው።

አመልካቾች ከተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ውስጥ ማመልከት የሚችሉት በአንዱ ብቻ ነው።

ምዝገባእ ከነሐሴ 15 ጀምሮ እስከ 19/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው የሚቆየው።

የምዝገባ ቦታ፡-
- አዲስ አበባ በኦንላይን (አዲስ አበባ)
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ (አምቦ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ (አርባምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (አሶሳ)
- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ (ባህርዳር)
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ (ደ/ብርሃን)
- ደብረ ማርቆስኦኒቨርሲቲ፣ (ደ/ማርቆስ)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ድሬዳዋ)
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ (ፍቼ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ (ጎንደር)
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀረር ካምፓስ ሀረር)
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ነቀምቴ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሚዛን ቴፒ)
- ሮቤ ቲቺንግ ኮሌጅ፣ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ)

ዕድሜ ፣ ቁመት ፣ ክብደትና ሌሎች መረጀዎችን ከላይ በተያያዘው የተቋሙ ይፋዊ ማስታወቂያ ይመልከቱ።

More ፦ https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies?fbclid=IwAR1ZLHg_fw9VhghmXo-oOL9ykrsCmq3vcUISCzYl8QtRPPg5fnW4VW_Yfig

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ? የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል። የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ? - ነሃሴ 13…
ፎቶ ፦ ዛሬ ነሃሴ 15 ቀን 2015 ዓ/ም የ #ኣሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

#ማስታወሻ ፦ ከ " ኣሸንዳ " አከባበር ጋር በተያያዘ በክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የወጣው መርሀ ግብር ከላይ ተያይዟል። በቢሮው ከተገለፀው ውጭ የሚካሄደ የአሸንዳ በዓል ዝግጅት እውቅና እንደሌለው ተነግሯል።

Photo Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ዛሬ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልጆች የሚካፈሉባቸው የፍፃሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ዛሬ የሚደረጉት ውድድሮች የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ እና የ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ናቸው።

ውድድሮቹ ምሽት 4:30 እና ምሽት 4:42 ላይ ነው የሚደረጉት።

ሀገራችን የሚወክሉ አትሌቶች እነማን ናቸው ?

- በ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ (አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም)

- የ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ (አትሌት ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ)

በ1500ሜ ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለኔዘርላንድ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport 
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በልዑል ገብረስላሴ የነሃስ ሜዳሊያ አገኘች❤️ 🥇የኡጋንዳው አትሌት ኪፕላንጋት በአንደኛ ደረጃ አጠናቋል። 🇺🇬 🥈አትሌት ማሩ ተፈሪ ከእስራኤል ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል። 🇮🇱 🥉የሀገራችን ልጅ ልዑል ገብረ ስላሴ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል። 🇪🇹 @tikvahethiopia
ፎቶ፦ በወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ 3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን ፤ አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ 6ኛ ፣ አትሌት ፀጋዬ ጌታቸው 17ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የባለፈው አመት የዓለም ሻምፒዮን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን አቋርጧል።

አትሌት ታምራት ውድድሩን ለማቋረጥ የተገደደው ባጋጠመው ከባድ የጨጓራ ህመም ምክንያት እንደሆነ ለ " ልዩ ስፖርት " ተናግሯል።

በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ አትሌቶች በቡዳፔስት ያለውን ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም አቅቷቸው ሲወድቁ እንደነበር ገልጿል።

ከውድድሩ ፍፃሜ በኃላ የተነሱ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ።

#ማስታወሻ ፦ ዛሬ ምሽት 3000ሜ መሰናክል ሴቶች ፍፃሜ እና 5000 ወንዶች ፍፃሜ ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ... በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል። በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ? አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦ " የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ…
#Update

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር " መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር " መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ውይይቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባላቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን አግኝቶ ማነጋገር #ግድ እና #ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ዘንድሮ የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአዲስ አበባ ከተማ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎች ሰልፍ እንዳያደርግ በመከልከሉ ጥያቄዎቹን ሳያቀርብ እንደቀረ ይታወሳል።

በኃላ ሊያነሳቸው የነበረውን ጥያቄዎችን በማካተት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ እሳቸውን ማነጋገር ለሠራተኞች ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት እንደሚረዳ ገልጾ ነበር።

በወቅቱ በፃፈው ደብዳቤ በየጊዜው እያሻቀበ በመጣው የኑሮ ውድነት፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ገልጾ ለዚህ ብቸኛው መፍትሄው ጠቅላይ ሚኒስትሩን  አግኝቶ ማነጋገር እንደሆነ ገልጿል።

ኢሠማኮ የሠራተኞች አንገብጋቢ የሚባሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ሊያገኝ እንዳልቻለ በዛው ደብዳቤ ተመላክቷል።

ከዚህ ቀደም የሠራተኞች ጥያቄ የቀረበላቸው መንግሥታዊ አካላት ጥያቄውን ወደ ጎን የመግፋት አዝማሚያ እያሳዩ በመምጣታቸው፣ የኢሠማኮ አመራር " ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአነጋግሩን " ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን በወቅቱ በፃፈላቸው ደብዳቤው አስረድቶ ነበር።

#ማስታወሻ

ከዚህ ቀደም ኢሠማኮ ከሰራተኛው ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንዳያደርግ በተከለከለው ሰልፍ ሊጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች ምን ነበሩ ?

1. በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው እየተቸገረ ነው፣ በተለይ ደግሞ ደሞዝ ተከፋዩ። መንግስት መፍትሄ ይስጠን። አብዛኛው ሰራተኛ በቀን አንዴም ለመብላት እየተቸገረ ነዉ።

2. የስራ ግብር ይቀነስልን።

3. የዛሬ አራት አመት ወጥቶ የነበረው የዝቅተኛ ደሞዝ ማስተካከያ አዋጅ እስካሁን ደንብ ሳይወጣለት ቆይቷል። ይህም ትኩረት ይሰጠው፣ በ600 ብር እየኖረ ያለ ሰው አለ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ደሞዝ በአማካኝ ከ800 - 1,200 ብር ነው።

4. የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ከደምበኛቸው ከሚቀበሉት ክፍያ ለሰራተኛው 80 ፐርሰንት ከፍለዉ ቀሪውን 20 ፐርሰንት እንዲወስዱ በሚል የወጣዉ መመሪያ አለመከበር በኤጀንሲ በተቀጠሩ  ሰራተኞች ላይ ተመልካች ያጣ የጉልበት ብዝበዛ እየተካሄደ ነው፣ መንግስት ትኩረት ያርግበት የሚል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል።

ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የGAT መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ላይ ምዝገባ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከመስከረም 23 እስከ 25/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሙከራ ፈተና ይሰጣል።

(ለመመዝገብ እና ፈተናውን ለመውሰድ የይለፍ ቲኬት ለማግኘት ሊከተሏቸው የሚገቡ ቅደም-ተከተሎች ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው።

በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው።

በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ።

#ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/
የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ከዓመታዊው #የቁልቢ_ገብርኤል የንግስ በዓል ጋር በተያያዘ #ከጨለንቆ እስከ #ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ እንዳያልፍ ክልከላ ተጥሏል።

ክልከላው እስከ ታህሳስ 19 (#አርብ) ከሰዓት ድረስ የሚዘልቅ ነው።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ለአዲስ አበባ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፦

1ኛ. የሞተር ባለንብረቶች እንዲሁም በሞተር እየተንቀሳቀሳችሁ ስራችሁን ለምትሰሩ አባላቶች ከነገ አርብ የካቲት 8 /2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ ሞተር ማሽከርከር ፍፁም ተከልክሏል። የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ክልከላውን በሚተላለፉ ላይ " ጥብቅ እርምጃ እወስዳለሁ " ብሏል።

                                 __

2ኛ. ለአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ #መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት መሪዎች እስኪያልፉ ድረስ መንገዶች ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ሊዘጉ ይችላሉ።

ፖሊስ አማራጭ / ተለዋጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ   ፍላሚንጎ  - ኦምሎፒያ  -  ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት

ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - በብሔራዊ ቤተ - መንግስት - በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶች እንግዶች የሚያልፉባቸው ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ፦

ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን

ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ - አፍሪካ ህብረት ዋናው በር - ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ግራና ቀ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
  
                                __

3ኛ. 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። የ2024 መሪ ቃል ፤ " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት " የሚል ነው።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ…
#ማስታወሻ

" የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ?

የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም

አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

አከራዮች #ከ2_ወር_የቤቱ_ኪራይ_በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም

የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው #የመያዝ_ግዴታ አለባቸው።

ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት።

➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል #ከሁለት_ዓመት ሊያንስ አይችልም።

NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡

More : https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/86580?single

#Ethiopia
#የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥርና_አስተዳደር_አዋጅ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ…
🔈#ማስታወሻ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ

" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦
- ሰላምን፣ 
- መረጋጋትን
- ፍቅርን
- አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ "


ቋሚ ሲኖዶስ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም ማወጁ አይዘነጋም።

#ኢትዮጵያ🙏

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU ራስ ገዙ አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ያቀረበው ጥሪ ነገ ያበቃል። በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር  ይታወቃል። በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍለው በዩኒቨርሲቲው…
ተማሪዎች እስከ መቼ ማመልከት ይችላሉ ?

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ የማመልከቻው ቀን ከዚህ ቀደም በነበረው ማስታወቂያ ዛሬ መስከረም 08/2017 እንደሚያበቃ ቢገለጽም እስከ ነገ መስከረም 09/2017 ድረስ መራዘሙን አስታውቋል።

በዚህም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጾች ፦
➡️
www.aau.edu.et
➡️
https://portal.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል።

#ማስታወሻ ፦ ለነፃ የትምህርት እድል ( #ስኮላርሺፕ ) የሚመዘገቡ የተለየ መመዝገቢያ አለመኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው ዩኒቨርሲቲው ከላይ በተጠቀሰው የመመዝገቢያ አማራጭ ብቻ እንዲያመለክቱ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ : መንገዶቹ ተዘግተዋል።

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩት መንገዶች ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተዘግተዋል።

ከቤት ለስራም ይሁን ለሌላ ጉዳይ የወጣችሁ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ።

@tikvahethiopia