TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AAU

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።

ይኸው ድጋፍ ዛሬ ወደ ክልሉ መላኩን ተቋሙ ገልጿል።

ድጋፉ 11 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ቀሪው አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮችና የህክምና መሳሪያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆ በምርምርና ቴክኖሎጂዎች ረገድም በመልሶ ማቋቋሚያ ስራዎች ላይ የራሱን እገዛ እንደሚያደርግም ገልጿል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
" ዝግጅቱ ተጠናቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት #መጠናቀቁን አስታወቀ።

ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 እንዲሁም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 74 ሺህ 776 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ አመልክተዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተና ንድፍና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
#ቁልቢ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል ብለዋል።

የምዕመናኑን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፣ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል እና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የበዓሉ ታዳሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን እንዳይሰረቅ በጥንቃቄ በመያዝና የወንጀል ድርጊት ሲመለከቱ በማጋለጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ተብሏል።

በንግስ በዓሉ ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲያዙ ውሳኔ ለመሰጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።

ወደ ስፍራው በሚያመራው መንገድ አልፎ አልፎ ያለው አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር አደጋን ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል።

ምዕመናን ወደ ንግስ ስፍራው በሚመጡበት ወቅት ተገቢነት የሌላቸው አርማና ምልክቶችን ይዘው መገኘት እንደሌለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
" የትምህርት ሚኒስቴር በዋናነት ለተገኘው ውጤት የኔ ውድቀት ነው ብሎ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል " - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ

የትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገብ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በጥናት ለይቶ እንዲያቀርብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠየቀ።

በይህ የተጠየቀው በምክር ቤቱ የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2016 እቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ዛሬ ሲገመግም ነው።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ " ቀደም ሲል ሲሰጡ የነበሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤቶች የተማሪዎችን ትክክለኛ ችሎታ ያሳዩ አልነበሩም " ብለዋል።

የፈተና አሰጣጡን በመቀየር የተመዘገበው የተማሪዎች ውጤት በዘርፉ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች ማሳያ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህም ከወላጆች ጀምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ጥራት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰው እየተካሄዱ ያሉ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ መርኃ ግብሮችና የመምህራን አቅም ግንባታ ሥራዎችን ለአብነት አንስተዋል።

በምክር ቤቱ የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ፤ " ሚኒስቴሩ ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መምጣት ሁሉንም ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም " ብለዋል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የማስተማርና ፈተና የማስፈተን ተልዕኮ ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተቋም በዋናነት ለተገኘው ውጤት ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባዋል ነው ያሉት።

ትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ተጠሪ ተቋማትና የትምህርቱ ዘርፍ ተዋንያን ለውጤቱ የነበራቸው ድርሻ ተለይቶ መቅረብ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ለተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ማጣት ምክንያት የሆኑ ሌሎች ችግሮችም በጥናት ተለይተው ሊቀርቡ እንደሚገባም ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#አሁን #ሲዳማ

የሲዳማ ክልል ም/ ቤት አስቸኳይ ጉባዔ በሀዋሳ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው እያካሄደ ያለው።

ለአንድ ቀን ብቻ ይካሄዳል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

- ለጉባኤው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል።

- የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ።

- የምክር ቤቱ አባላት #የህግ_ከለላ ማንሳት ላይ ተወያይተው ውሳኔ ይሰጣሉ።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በቀላል ባቡር እና ቀለበት መንገዶች 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚያልፍባቸውና ውስጠኛው ቀለበት መንገድ ተብለው በሚጠሩ ቦታዎች ላይ መሸጋገሪያ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ባለመኖራቸው እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡና መንገድ ለማቋረጥ ረዥም ርቀት ለመጓዝ እንደሚገደዱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

በመሆኑም ፤ 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች እንደሚገነቡ ይፋ አድርጓል።

ተሻጋሪ ድልድዮቹና መተላለፊያ መስመሮቹ ከመሬት በላይ እንዲሁም በመሬት ውስጥ እንደሚገነቡ ጠቁሟል።

የእግረኛ ተሻጋሪ ድልድዮቹ ፦
- ሐና ማርያም፣
- ኃይሌ ጋርመንት፣
- ሳሪስ ሐኪም ማሞ ሰፈር፣
- አደይ አበባ፣
- ጉርድ ሾላ፣
- አውቶቡስ ተራና አብነት አካባቢ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ነው የሚገነቡት ብሏል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ፈተናው በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡

ከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በዚህ ዓመት በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በዚህም በአዲስ አበባ ለ6ኛ ክፍል 86,691 ተማሪዎች እንዲሁም ለ8ኛ ክፍል 88,028 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia