TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UK

የዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እየተጓዘ ባለ መኪና ውስጥ ሳሉ የደህንነት (መቀመጫ) ቀበቶ ባለማሰራቸው ተቀጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ላይ ባለ መኪና ውስጥ ሆነው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፍ ቪድዮ እየቀረጹ ሳለ የደህንነት (መቀመጫ) ቀበቷቸውን ባለማሰራቸው መቀጣታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ  " ስህተት መሆኑን እናምናለን ይቅርታም እንጠይቃለን " ብሎ ቅጣቱን እንደሚከፍል አክሏል።

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የመቀመጫ ቀበቶ ያላደረጉ ሰዎች 100 ፓውንድ ይቀጣሉ።

ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከደረሰ ቅጣቱ 500 ፓውንድ ሊደርስ ይችላል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቅጣት የተዳረጉት ስለ መንግሥታቸው ወጭ የሚገልጽ ቪድዮ መኪና ውስጥ ቀርጸው በኢንስታግራም ገጻቸው ባጋሩበት ወቅት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#UK

" ማንም ሰው ወደ #ሩዋንዳ ለመሄድ 3 ሺህ ፓውንድ ለማግኘት ብቻ ወደዚህ ለመምጣት የሚሞክር አይመስለኝም " - የገንዘብ ሚኒስትር ኬቨን ሆሊንራክ

ዩናይትድ ኪንግደም  (ዩኬ) በአገሯ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን እስከ 3 ሺህ ፓውንድ በመክፈል ወደ ሩዋንዳ ልትልክ መሆኑን እንዳስታወቀች ቢቢሲ ዘግቧል።

ይህ አዲስ የስደተኞች ዕቅድ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ያልተሳካላቸው ስደተኞች በበጎ ፈቃደኝነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ለዚህም የሚሆን ገንዘብ ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የጥገኝነት ጥያቄያቸው በዩናይትድ ኪንግደም ውድቅ ለተደረገባቸው ለማንኛውም ስደተኞች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ይህ ዕቅድ በተለይም ወደ አገራቸው መመለስ በማይችሉ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ነው።

የዩናትድ ኪንግደም የገንዘብ ሚኒስትር ኬቨን ሆሊንራክ ምን አሉ ?

- ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ ለተስማሙ ስደተኞች የሚከፈለው ክፍያ የህዝብን ገንዘብ በአግባቡ መጠቀም ይሆናል።

- እነዚህን ሰዎች ያለ ምንም ጥቅም እዚህ ማቆየት ከዚያ የበለጠ ገንዘብ ያስወጣናል።

- " እዚህ በህገወጥ መንገድ ከመጣችሁ በዚህች አገር መቆየት አትችሉም " የሚለውን መልዕክት ያስተላልፋል። መሰረታዊ ነጥብ ይህ ነው።

- ማንም ሰው ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ 3 ሺህ ፓውንድ ለማግኘት ብቻ ወደዚህ ለመምጣት የሚሞክር አይመስለኝም።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት " በህገወጥ መንገድ ገብተዋል " የተባሉ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ተልከው ጥያቄያቸው ከዚያ የሚታይበትን የተለየ እቅድም ለመተግበር መንግሥት እየሞከረ ይገኛል ተብሏል።

ይህ እቅድ ከሩዋንዳ የደህንንት ስጋት ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤቶች ታግዶ ነበር።

እነዚህን ሙግቶች ለማሸነፍ መንግሥት የምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር አስተማማኝ አድርጎ የሚፈርጃት ‘የሩዋንዳ ሴፍቲ ቢል’ (የሩዋንዳ የደህንነት ረቂቅን) ለማጽደቅ እየሞከረ ይገኛል።

አዲሱ ዕቅድ ከዚህ ከነበረው የተለየ እንዲሁም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና በፓርላማው በሚጸድቀው ረቂቅ ላይ የተመሰረተ አለመሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል።

መረጃው የቢቢሲ እና ታይምስ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
#Rwanda #UK

ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።

የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?

" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።

አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።


በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።

በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " - አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር

ከሰሞኑን ዩናይትድ ኪንግደም (UK) አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አግኝታለች።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር ናቸው።

ፓርቲው የሪሹ ሱናክን የወግ አጥባቂ (ኮንሰርቫቲቭ) ፓርቲ በከፍተኛ ብልጫ ነው ዘርሮ ያሸነፈው።

በከፍተኛ ብልጫ የተሸነፉት ሱናክ ፥ " የሕዝቡን ቁጣ ሰምቻለሁ። ለዚህ ሥራ ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቻለሁ። ይሁን እንጂ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) መንግሥት መለወጥ እንዳለበት ግልጽ የሆነ መልዕክታችሁን አስተላልፋችኋል፤ የሚተካኝም ሲገኝ ከፓርቲ መሪነት እለቃለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ስልጣን የተረከቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ዛሬ የመጀመሪያ መግለጫቸውን ሰጥተዋል።

በዚህም ፥ በጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞች ጉዳይ የቀድሞው የወግ አጥባቂ መንግሥትን ፖሊሲ እንደማያስቀጥሉ በይፋ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን /ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " ብለዋል።

መንግስታቸው ፥ የቀድሞው አገዛዝ በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የጀመረውን ስራ እንደማይቀጥሉበት ተናግረዋል።

" ከሩዋንዳ ጋር የተደረሰው ስምምነት አይቀጥልም ውድቅም ይሆናል " ያሉት ጠ/ሚ ስታርመር  በዚህ የስደተኞች ጉዳይ ላይ የቀድሞው መንግስት ፖሊስ አይቀጥልም ብለዋል።

#UK
#Rwandascheme

@tikvahethiopia