TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን ! በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦ • መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው። • የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ መምህራን እና ዩኒቨርሲቲዎች ምን አሉ ?

ጠ/ሚር ዶክተር ዓብይ አህመድ ትላንት ከወጣቶች ጋር በተወያዩበት መድረክ ስለዩኒቨርስቲዎች እና ስለ መምህራን ተነስቶላቸው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" የዩኒቨርስቲ መምህራን እናንተም መገንዘብ ያለባችሁ ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት። አሜሪካ እንኳን ዩኒቨርስቲ ተማሪ አስገብታ አትቀልብም።

ዩኒቨርስቲ ሰው ከደረሰ ራሱን ነው ማስተማር ያለበት እንጂ ለአስተማሪም ደመወዝ ፣ ለተማሪ ቀለብ አይነት ጥያቄ እንደኢትዮጵያ ላሉ ድሃ አገራት ኢኖቬተርስ አይፈጥርም።

ዩኒቨርስቲዎች አውቶነመስ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር አለባቸው። ሃይስኩል ላይ ኢንቨስት ካደረግን እኛ እሱ እንደ በቂ መወሰድ አለበት።

ዩኒቨርስቲ ሆኖ ገንዘብ አምጥቶ የራሱን ደመወዝ መክፈል የማይችል ከሆነ ኢትዮጵያን ማሳደግ አይችልም ማለት ነው።

ሃርቫርድ መንግሥትን አይጠይቅም በጀት፣ ኦክስፎርድ አይጠይቅም በጀት፣ ኬንያም ዩጋንዳንም ብትሄድ አይጠይቅም በጀት፣ እዚህ ግን ቀለቡም፣ ደመወዙም ሁሉም ነገር የሚጠየቅ ከሆነ ችግር አለ።

ሁለተኛ የዩኒቨርስቲ መምህር ስታንዳርድ አለው። በሴሚስተር አራት ክሬዲት ሃወር፣ አምስት ክሬዲት ሃወር አስተምረህ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ አይባልም። ተጋባዥ መምህር ነኝ ነው የሚባለው። ማነው ሙሉ ጊዜ መምህር ለመባል የሚያበቃ ስራ እየሰራ ያለው የሚለውን ማየት አለባችሁ። ይሄ ብዙ ችግር አለ።

ሁሉም የዩኒቨርስቲ መምህር በርግጠኝነት የምነግራችሁ በቂ ደመወዝ አያገኝም። ደመወዙ ያንሳል ፣ ኑሮው ዝቅተኛ ነው ትክክል ነው። መቀየር አለበት። ነገር ግን ኢትዮጵያንም ማሰብ ጥሩ ነው። እዳ ተጭኖን፣ ዋጋ ግሽበት ሊገድለን፣ ጦርነት እያለብን፣ የዓለም ተጽዕኖ በዝቶብን ፕሮጀክቶች እዚህም፣ እዚያም፣ እዚያም ጥደን እያረሩብን፣ አያዋጣም !

የከፋው ደግሞ የዩኒቨርስቲ መምህር ሃላፊነቱን ዘንግቶ የፖለቲካ አጀንዳ መጫወቻ ሲሆን ደግሞ በጣም መጥፎ ነው። አሉ እንደዛ ምልክቶች! ይሄ መስተካከል አለበት።

የዩኒቨርስቲ መምህራን በሃሳብ እንዲያግዙን እንፈልጋለን። አሁን ካለንበት ችግር ከዋጋ ግሽበቱ ፣ ከፕሮጀክቱም ፣ ከድህነቱም እንድንወጣ ፣ የምንጠብቀው እነሱን ነው። ይቺ አገር ከሌላት አንጡራ ሃብት ላይ መንዝራ መቀነቷን ፈታ አስተምራቸዋለች፣ ያለችበትን ችግር መፍታት የእኔም የእነሱም እዳ ነው። "

@tikvahethiopia
እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል !

“ አንተ ለምን ትንበቀበቃለህ ? ” ብሎኛል በሚል ምክንያት የስራ ባልደረቦቹን የገደለው እና ያቆሰለው የፌዴራል ፖሊስ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ።

የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው ኮንስታብል ማማሩ ተመስገን ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው ፍልዉሃ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ፖሊስ ዲቪዥን የእግር አሰሳ ስራ ለማከናወን ተመድቦ ስራውን በማከናወን ላይ ነበር።

በዚህም ወቅት የመብራት ፊውዝ ፈንድቶ በመሮጡ የሥራ ባልደረባው የሆነው ሟች ትዕግስቱ እንድሪያስ “አንተ ለምን ትንበቀበቃለህʔ” በማለት ተናግሮኛል በሚል ምክንያት በያዘው ታጣፊ ክላሽ ተኩሶ የገደለው ሲሆን በተጨማሪም የእግር አሰሳ ስራን ሲያከናውኑ ከነበሩ እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ወደካምፕ ለመውሰድ ተዘጋጅቶ በቆመ መኪና ውስጥ የነበረችዋን የስራ ባለደረባው ድመቅ ጌታቸውን ተኩሶ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

በተጨማሪም ሌሎች 3 የስራ ባልደረቦቹ ላይ ጉዳት በማድረሱ በ2ቱ የሰው መግደል ወንጀል እና በ3ቱ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ አጠቃላይ 5 ክሶችን እንደመሰረተበት የክስ መዝገቡ ያሳያል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት የቀረበው የዐቃቤ ህግ ክስም ተነቦና ክርክር ተደርጎ ሲያበቃ ፍርድ ቤቱ በአምስቱም ክሶች ተከሳሹ ጥፋተኛ ነው በማለት በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና ለዘወትር ከህዝባዊ መብቶቹ እንዲታገድ ሲል ወስኖበታል፡፡

መረጃው የፍትህ ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከባድ ዝናብ የጣለ ነው። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ፈታኝ ሆነዋል።

አሽከርካሪዎች ፤ በእንደህ ያለው ወቅት ባለማሽከርከር የራሳችንን እና የሌሎችን ወገኖች ደህንነት ማስጠበቅ ይገባናል።

ቪድዮ : አብዱራህማን መኪ - ከደቂቃዎች በፊት ፒያሳ
አካባቢ (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
ሱዳን ?

ሱዳን " ሰነድ የላቸውም " ያለቻቸውን የሀገራችንን ዜጎች እያፈሰች እያሰረችና እየቀጣች ነው።

ጎረቤት ሀገር ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን ዜጎቻችንን እያፈሰች እያሰረች ሲሆን በዛው ያሉ ዜጎቻችን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እየወቀሱ ይገኛሉ።

ዜጎቻችን ከፍተኛ ቅጣት እየተጣለባቸው እስከ ድብደብዳ የደረሰ እንግልትም እየደረሰባቸው ኤምባሲው ዝምታን እየመረጠ ነው ሲሉ ተችተዋል።

ኤምባሲው በበኩሉ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፓስፖርት የሌላቸው በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችን ፓስፖርት እንዲያገኙ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን የሞሉትን ሰነድ አልባ ፎርም በማጣራት ውሳኔ በመስጠት ፓስፖርት እያዲያገኙ እየተሰራ ነው ብሏል።

ነገር ግን ብዙ ዜጎቻችን ፓስፖርት እያላቸው የመኖሪያ ፍቃድ (ኢቃማ) ባለማውጣታቸው ምክንያት እየታሰሩና ገንዘብ እየተቀጡ እንደሚገኙም አመልክቷል።

ኤምባሲው ፓስፖርት መያዝ ብቻ ከቅጣትና ከመታሠር አያድንም ብሏል።

ፓስፖርት አውጥተው 5 ዓመት ሙሉ መኖሪያ ፍቃድ(ኢቃማ) ሳያሰሩ ፓስፖርት የሚያሳድሱ ዜጎቻችን ብዙ ናቸው ያለድ ኤምባሲድ " የመኖሪያ ፍቃድ ካላወጡ ፓስፖርት ብቻ መያዝ ህጋዊ አያደርግም " ብሏል።

የመኖሪያ ፍቃድ ባላወጡ ዜጎች ላይ አሁንም #አፈሳው_ሊቀጥል ይችላል ያለው ኤምባሲው " ፓስፖርት ያላችሁ የመኖርያ ፍቃድ (ኢቃማ) እንድታወጡና ህጋዊ ሆናችሁ እንድትኖሩ እንመክራለን " ብሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ቦረና

በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖሩት።

በድርቅ ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

(በድብሉቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች)

የ7 ልጆች እናት ወ/ሮ ጂሎ ጉራቻ ፦

" የዘንድሮው ድርቅ የነበሩንን ከብቶች እና ሁሉንም ንብረቶችን ነው ያወደመብን። ባዶ እጃችንን ስንሆን ወደዚህ መጣን ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ በምግብ እና ውሃ እጥረት እየተቸገርን ነው። በተለይም ህፃናት ነፍሰጡር ሴቶች፣ አዛውንቶች በምግብ እጥረት እየተጎዱ ናቸው። እኛ እዚህ ከሰፈርን ከ6 ወር በላይ ሆኖናል። በመጠለያው በጣም ብዙ ቤተሰቦች ነው ያሉት። በቆይታችን አንዴ ብቻ ነው ለተወሰኑ ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ የተሰጠው እንጂ ምንም አላገኘንም። ስለዚህ በጣም ችግር ላይ ውስጥ ነው ያለነው። "

የ6 ልጆች አባት ዳለቻ ዲዳ ፦

" ምንጠጣው ውሃ በጣም የቆሸሸ ነው። እንስሳት ሲሞቱ ከሚጣሉበት ነው ልጆቻችን የሚቀዱልን። በዛ ላይ የመፀዳጃ ቦታም የለንም። እንዲሁ በበሩ ደጃፍ ነው ይህ ሁሉ በዚህ የሰፈረው ህዝብ የሚፀዳዳው ስለዚህ የበሽታ ወረርሽኝ ፍራቻ አለብን። ሌላው የመጠለያ ቦታና ላስቲክ ሰጥተውናል። ይህ ላስቲክ #ብርድ የሚከላከል አይደለም። እናም በጣም ችግር ውስጥ ነን። "

የልጆች እናቷ ትዬ አደንጌ ፦

" #ብርዱ_በጣም_አስቸጋሪ_ነው። ለምግብ ፍለጋ ነው ከእሳት አጠገብ የምንነሳው። በዛ ላይ የምንለብሰው ልብስ የለንም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Borana-08-23 #ገልሞ_ዳዊት

@tikvahethiopia
* ቡልቡሎ

የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ " ቡልቡሎ " ላይ በጎርፍ በመቆረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት እየተዳረገ እንደሚገኝ የወረባቦ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ዙሪያ መልዕክት የላኩ ሲሆን መንገዱ በጎርፍ በመቋረጡ ከፍተኛ የሆነ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።

የወረባቦ ኮሚኬሽን ያናገራቸው የፖወርኮን መንድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት የሀይቅ ቢስቲማ ጭፍራ መንገድ ግንባታ አስተባባሪ አቶ አለሙ አባይነህ ተከታዩን ብለዋል፦

" ድርጅታችን በአጠቃላይ መንገዱን ከመስከረም በኋላ ሙሉ ጥገና ያደርጋል። አሁንም በመንገዱ ላይ የተሰበሩና ለትራንስፖርት መስተጓጉል የሚፈጥሩ ቦታዎች ላይ ጊዜያዊ ጥገና እያደረግን እንገኛለን።

ነገር ግን ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት መንገዶቹ የተቆረጡበት ቦታ የወሰን ማስከበርና የሴሌክት ማቴሪያል እጥረት እያጋጠመ ነው "

የወረባቦ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሰይድ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል፦

" የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ የአስፓልት መንገድ ለመስራት በፌደራል መንግስት ለተቋራጭ የተሰጠ በመሆኑ ወሎ ገጠር መንገድ ከጥገና አገልጎሎቱ ላይ አስወጥቶታል በዚህም መንገዱን እየጠገነ የሚያስተዳድረው ተቋራጭ ድርጅቱ ፖወርኮን ነው።

ፓወርኮን በአሁኑ ሰአት መንገዱን ሙሉ ጥገና ለማድረግ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መጠገን ስለማልችል ሙሉ ጥገና ከመስከረም በኋላ ይደረጋል።

ነገር ግን ዛሬ ላይ ቡልቡሎ አውራጎዶና አካባቢ ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመቆረጡ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት መኪኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የተቆረጠበት ቦታ ከወደፊት አንፃር ለጥገና በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በጋቢዎን መታሰር ይኖርበታል። "

ፎቶ፦ ወረባቦ ኮሚኒኬሽን፣ ABD (ቲክቫህ ቤተሰብ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ! ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። አሁን ላይ 4ተኛ…
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት 4ኛ ዙር በማጠናቀቅ 240 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስቴም ፓወር በቀጣይ አምስተኛ ዙር ሰልጣኞችን መዝገባ በማከናወን ሥልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ሥልጠናው መሰጠት ይጀምራል። በኦላይን ለመሰልጠን ለተመዘገቡም ስለጠናውን እየተሰጠ ይገኛል።

ከ4ኛው ዙር የተመረጡ ምርጥ 4 ፕሮጀክቶች፦

1. ግብርና እና ምግብ ዘርፍ፦

- ዮፍታሔ ሳሙኤል - Mushroom Agro-processing

- ​​ስጦታው አበራ - Punt Flour from Gipto

2. አገልግሎት ዘርፍ፦

- Wujo Digital Iqub

3. ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ:

- መኮንን አስማረ - Agricultural Chemical Spray & Aerial Mapping Drone

በልዩ ዘርፍ፦ ዶ/ር ትዝታ አለሙ - Biruh Hiwot Mental Health Consultancy

#STEMpower #VISA #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia