* ቡልቡሎ

የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ " ቡልቡሎ " ላይ በጎርፍ በመቆረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት እየተዳረገ እንደሚገኝ የወረባቦ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ዙሪያ መልዕክት የላኩ ሲሆን መንገዱ በጎርፍ በመቋረጡ ከፍተኛ የሆነ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።

የወረባቦ ኮሚኬሽን ያናገራቸው የፖወርኮን መንድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት የሀይቅ ቢስቲማ ጭፍራ መንገድ ግንባታ አስተባባሪ አቶ አለሙ አባይነህ ተከታዩን ብለዋል፦

" ድርጅታችን በአጠቃላይ መንገዱን ከመስከረም በኋላ ሙሉ ጥገና ያደርጋል። አሁንም በመንገዱ ላይ የተሰበሩና ለትራንስፖርት መስተጓጉል የሚፈጥሩ ቦታዎች ላይ ጊዜያዊ ጥገና እያደረግን እንገኛለን።

ነገር ግን ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት መንገዶቹ የተቆረጡበት ቦታ የወሰን ማስከበርና የሴሌክት ማቴሪያል እጥረት እያጋጠመ ነው "

የወረባቦ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሰይድ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል፦

" የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ የአስፓልት መንገድ ለመስራት በፌደራል መንግስት ለተቋራጭ የተሰጠ በመሆኑ ወሎ ገጠር መንገድ ከጥገና አገልጎሎቱ ላይ አስወጥቶታል በዚህም መንገዱን እየጠገነ የሚያስተዳድረው ተቋራጭ ድርጅቱ ፖወርኮን ነው።

ፓወርኮን በአሁኑ ሰአት መንገዱን ሙሉ ጥገና ለማድረግ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መጠገን ስለማልችል ሙሉ ጥገና ከመስከረም በኋላ ይደረጋል።

ነገር ግን ዛሬ ላይ ቡልቡሎ አውራጎዶና አካባቢ ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመቆረጡ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት መኪኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የተቆረጠበት ቦታ ከወደፊት አንፃር ለጥገና በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በጋቢዎን መታሰር ይኖርበታል። "

ፎቶ፦ ወረባቦ ኮሚኒኬሽን፣ ABD (ቲክቫህ ቤተሰብ)

@tikvahethiopia