TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው። ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። - በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት…
" ከዚህ በፊት ቦታው ላይ አደጋ ሊደርስ ይችላል ፤ ልንሞት እንችላለን ብለን በተደጋጋሚ አመልክተናል " - ቤተሰቦች

ትላንት በአዲስ አበባ፤ አዲስ ክፍለ ከተማ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ሳቢያ ግንብ ተደርምሶ የሰዎች ህይወት አልፏል።

አካባቢው ቀድሞውንም በስጋትንነት የተለይ ነበር።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት አንዱ ወጣት እዮብ ወልደማርያም ሲሆን በአደጋው ልጃቸውን ያጡ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ናቸው።

እዮብ ወ/ማርያም የሰው ህይወት ለማትረፍ ሲል የራሱን ህይወት እንዳጣም ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።

ቤተሰቦቹ ከዚህ ቀደም ቦታው ላይ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ከታች ከቀበሌ እስከ ላይ ላሉ አካላት በተደጋጋሚ ያመለከቱ ሲሆን ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጠው ብዙ ተስፋ ያለውን ልጃቸውን ህይወት መቅጠፉን አስረድተዋል።

በአደጋው መኖሪያ ቤቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት የሟች እዮብ ቤተሰቦችም አሁን ላይም ለቅሶ የተቀመጡት ቤተዘመድ እንዲሁም ጎረቤት ቤት ነው። በቀጣይም ማረፊያቸውን እንደማይታወቅ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የእዮብ ወላጆች አቅመ ደካሞች በመሆናቸው ምክንያት በቀጣይ የሚያርፉበት እንዲመቻችላቸው ተጠይቋል።

በሌላ በኩል የእዮብን ወላጆች ማገዝ ለምትፈልጉ በእናት ራውዳ ጀማል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት (CBE) 1000010020011 እና በአባት ወልደማርያም ሸዋ የባንክ አካውንት (CBE) 1000291553749 ማገዝ ትችላላችሁ።

በስልክ እናት ራውዳ ጀማልን በ0911225960 እንዲሁም ደግሞ አባት ወልደማርያም ሸዋን በ 0911137825 ላይ ማግኘች ይችላል።

@tikvahethiopia
#ምስራቅ_ጎጃም

በመሬት መንሸራተት የሰው ህይወት ጠፋ።

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ቦረቦር ሸንቻ ቀበሌ ጎበዝ አምባ ጎጥ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ በሶስት የመኖሪያ ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ውድመትና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይማኖት ካሳ ፤ " ከላይኛው እርከን እስከ ታችኛው መዋቅር ያለው አካል አለማድመጥና ውሳኔ አለማስከበር ለዚህ ችግር ዳርጎናል " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ቦታው ተደጋጋሚ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሚከሰትበትና የንብረት ጉዳት የሚደርስበት መሆኑ ተነግሯል።

የደጀን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዩን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት በዘገባ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁን ነገር ግን ምላሽ በመስጠት ነዋሪዎችን ከሞት ንብረታቸውን ከውድመት የሚታደግ አካል መጥፋቱን ገልጿል።

ችግሩ እየከፋ መጥቶ በዘንድሮው ዓመት ለሰው ህይወት መጥፋት የዳረገ በመሆኑ የበላይ አካላት በመደማመጥና አስቸኳይ ውሳኔ በመወሰን የዜጎችን ህይወት መታደግ ይገባል ብሏል።

በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ተመሳሳይ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄም ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ አይመን አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ አለች።

አሜሪካ የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ባካሄደችው የድሮን ጥቃት መግደሏን ነው በፕሬዝዳንቷ ጆ ባይደን በኩል ያሳወቀችው።

የአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ሲአይኤ (CIA) ባሳለፍነው ዕሁድ ካቡል ውስጥ ባካሄደው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ዛዋሂሪን መግደል መቻሉን ባይደን ገልፀዋል።

ፕሬዘዳንት ባይደን " ዛዋሂሪ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ እና ጥቃትን የቀረጸ ሰው ነው " ብለዋል።

አክለው " አሁን ፍትህ ተሰጥቷል ፤ ይህ የአሸባሪ ቡድን መሪ ከዚህ በኋላ በሕይወት የለም " ሲሉም ተናግረዋል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ዛዋሂሪ በአንድ በጥብቅ በሚጠበቅ ቤት በረንዳ ላይ ተቀምጦ ባለበት ነው የአሜሪካ ድሮን 2 ሚሳኤሎችን ተኩሶ የገደለው።

በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ዛዋሂሪ ብቻ ተነጥሎ መገደሉንም ተናግረዋል።

አሜሪካ ዛዋሃሪ ከቀድሞው የአል-ቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ጋር በመሆን የ 9/11 ጥቃትን እንደመራ ትገልፃለች። በዚህም ለረጅም አመታት ስታፈላልገው ቆይታለች።

አል-ዛዋሃሪ 71 ዓመቱ ሲሆን የኦሳማ ቢን-ላደን ህልፈትን ተከትሎ አልቃይዳን ሲመራ እንደነበርም ተገልጿል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
አልቃይዳ በቀጣይ በማን ይመራል ?

አሜሪካ አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ ማለቷን ተከትሎ አልቃይዳ የቀድሞውን የግብፅ ወታደር መሪ ያደርጋል ተብሎ ተገምቷል።

በአልቃይዳ ውስጥ ሶስተኛው ሰው ነው ተብሎ የሚታሰበው ሳይፍ አልአድል ሲሆን የቀድሞ ግብፅ ኮሎኔል ፣ በወታደራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ጥልቅ እውቀት እንዳለው ይነገራል።

ከዓመታት በፊት አልአደል ፤ በአፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ሱዳን ላሉ የአልቃይዳ እና ሌሌች ቡድኖች አባላት እንዲሁም ፀረ-UN አቋም ላላቸው የሶማሊያ ጎሳዎች ወታደራዊ እና የስለላ ስልጠና መስጠቱ ይነገራል።

በሶማሊያ በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በራስ ካምቦኒ የአልቃይዳን ማሰልጠኛ ተቋምም መስርቷል።

አል-አደል በ1987 የግብፅን መንግስት ለመጣል ሞክሯል በሚል ተከሶ የነበረ ሲሆን ክሱ ውድቅ ከተደረገ በኋላ በ1988 አገሩን ለቆ የሶቪየትን የአፍጋኒስታን ወረራ ለመመከት ወደ አፍጋኒስታን አቅንቶ ነበር።

አልአደል ከዓመታት በፊት በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥም ለተመለመሉ ታጣቂዎች ፈንጂዎችን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር እሱን በተመለከተ የተፃፉት መረጃዎች ያሳያሉ።

ከ1998ቱ በኬንያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ (ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል) አሜሪካ በጥብቅ ከምትፈልጋቸው ሰዎች አንዱ ነው።

አሁን ላይ ብዙም ስለእሱ የሚታወቅ ትክክለኛ መረጀ የለም። ነገር ግን አልቃይዳ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ቀጣዩ መሪም ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሰው ነው።

መረጃው የተሰባሰበው ከአል ሲፋን የቀድሞ የFBI ኤጀንት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

• ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነሐሴ 19/2014 ተቀጥሯል።

• የክስ መቃወሚያው ውድቅ ተደርጓል።

ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካቀረበው መቃወሚያ ጋር አገናዝቦ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት የሚታይ ቢሆንም ይርጋ እንዴት መቆጠር አለበት የሚለው ጉዳይን በወንጀል ህጉ መሠረት ስናየው ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም ብሎ የጋዜጠኛ ተመስገንን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል።

ክሱን ከቀረበው ማስረጃ አንፃር መርምሮ እንዲከላከል ወይም በነፃ ለመልቀቅ ለነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከ24 ቀን በኋላ እንዲቀርብ እንደቀጠረ የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የፌደራል ፍ/ቤቶች በነሐሴ ወር መደበኛ የዳኝነት አገልግሎትታቸውን ይቀጥላሉ።

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/3 አንቀፅ 38(2) መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ዝግ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡

ሆኖም በዳኞች ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፤ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤትከነሐሴ 1 30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ይህም ወደ 205 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የበሰሉ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት፣ እስረኛ ያለባቸውን መዝገቦች ቅድሚያ ሰጥቶ ለመስራት ያስችላል ተብሏል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ያላቸውን የዕረፍት ጊዜ መስዋዕት በማድረግ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ በመሆናቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመስግኗል።

@tikvahethmagazine
#Tigray , #Mekelle

የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ እና የተመድ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ተወያዩ።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልእከተኛ ማይክ ሀመር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛ አኔት ዌይበር፣ የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ፣ የካናዳ እና ጣልያን አምባሳደሮች እንዲሁም ተወካዮች ፣ ከፍተኛ ኃላፊዎች ናቸው ወደ ትግራይ በመጓዝ ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ጋር ተገናኝተው የመከሩት።

አሜሪካ፣ ተመድ ፣ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላማዊ ድርድር እንዲቋጭ ጥረት እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል።

የፌዴራል መንግስት እና ትግራይን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት ሌላ ተጨማሪ እልቂት ሳይኖር ያሉ ችግሮች በሰላማዊ ድርድር እንዲፈቱ አቋም መያዛቸው ለሰላም ድርድር የተደራዳሪ አካላትን መሰየማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ፣ የተመድ ተወካዮች ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ከትግራይ ክልል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ይዘው ተመልሰዋል።

ከዚህ ቀደም መልዕክተኞቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ የመብራት፣ የቴሌኮም፣ የባንክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በፍጥነት ወደነበረበት መመለስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

በዚህም የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በዓለማቀፍ ማህበረሰቡ ተወካዮች በኩል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ልከዋል።

ደብዳቤው ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስልክ ፣ ባንክ፣ መብራት እና የመሳሰሉትን ለመመለስ እና አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማድረግ ወደ ክልሉ ገብተው ለሚሰሩ አካላት የደህንነት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።

በዚህ #የደህንነት_ማረጋገጫ አገልግሎቶችን ወደነበረበት መመለስ ለማስጀመር ምንም አይነት መሰናክል ሊኖር አይገባም ተብሏል።

ተጨማሪ https://www.eeas.europa.eu/eeas/ethiopia-eu-and-us-special-envoys-visit-mekelle-tigray_en

@tikvahethiopia