#Tigray , #Mekelle

የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ እና የተመድ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ተወያዩ።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልእከተኛ ማይክ ሀመር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛ አኔት ዌይበር፣ የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ፣ የካናዳ እና ጣልያን አምባሳደሮች እንዲሁም ተወካዮች ፣ ከፍተኛ ኃላፊዎች ናቸው ወደ ትግራይ በመጓዝ ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ጋር ተገናኝተው የመከሩት።

አሜሪካ፣ ተመድ ፣ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላማዊ ድርድር እንዲቋጭ ጥረት እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል።

የፌዴራል መንግስት እና ትግራይን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት ሌላ ተጨማሪ እልቂት ሳይኖር ያሉ ችግሮች በሰላማዊ ድርድር እንዲፈቱ አቋም መያዛቸው ለሰላም ድርድር የተደራዳሪ አካላትን መሰየማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia