TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በዛሬው ዕለት Oxfam እና Save the Children ባወጡት ሪፖርት በድርቅ በተጠቁት፦
➡️ #ኢትዮጵያ
➡️ ኬንያ
➡️ ሶማሊያ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል።

ሪፖርቱ ዓለም መከላከል የሚቻላቸውን ተደጋጋሚ አደጋዎች መከላከል አለመቻሉን አጉልቶ ያሳያል ተብሏል።

Jameel Observatory ከተሰኘ ድርጅት ጋር በጥምረት የተሠራው ሪፖርት ዓለም ዳግም ከፍተኛ የረሃብ አደጋን ችላ ብሏል ሲል አስጠንቅቋል።

እ.አ.አ በ2011 በሶማሊያ ከ260,000 በላይ ሰዎችን (ከግማሽ በላይ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው) ከገደለው ረሃብ ጋር ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ሪፖርቱ ስጋቱን አስቀምጧል።

በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በኬንያ 3.5 ሚሊዮን ሰዎች በከፍተኛ ረሃብ እየተሰቃዩ ነው።

በ3ቱ ሀገራት ለከፍተኛ ረሃብ የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረበት ከ10 ሚሊዮን ወደ23 ሚሊዮን አድጓል።

በተደጋጋሚ ለቀረበው አስቸኳይ ድጋፍ " በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ " የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

እንደሪፖርቱ ከሆነ፦

➡️ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተ ድርቅ

➡️ በግጭቶች ምክንያት ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው

➡️ የኮቪድ-19 ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ምክንያት ሰዎች ችግሩን እንዳይቋቋሙ አድርጓል።

የዩክሬን ጦርነት እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዋጋ በማናር ችግሩን አወሳስቦታል።

በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ቢሰጡም የዓለም መሪዎች በጣም ከመዘግየታቸው ሌላ የሰጡት ምላሽ አነስተኛ ነው።

በዚህም በሚሊዮን ሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ማስጠነቀቂያ መሰጠቱን ቢቢስ ዘግቧል።

[ ሙሉ ሪፖርት ]

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ የአክሲዮን ገበያ የመመስረት ኃላፊነትን ተረክቧል።

የአክሲዮን ገበያ የመመስረት ኃላፊነት ለብሔራዊ ባንክ ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን አሁን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተላልፎ ተሠጥቷል።

በዚህም መሠረት ብሔራዊ ባንክ የአክሲዮን ገበያ የማቋቋም ስራ ሲያከናውን የነበረው ቡድን ስራውን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ በዛሬው እለት አስረክቧል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ ጋር የትብብር ስምምነት ማድረጉም ሪፖርተር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

➡️ ፈረንሳይ ፣ ጣልያን እና ስፔን 85 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ማባረራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ዲፕሎማቶቹ ሀገራቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል ተከሰው ሲሆን፤ ሩስያ ክሱ ሀሰት ነው ብላለች፤ የዩክሬን ጦርነት ከጀምረ ጊዜ አንስቶ 300 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከተለያዩ ሀገራት ተባረዋል።

➡️ ሩስያ ዛሬ የስፔን እና የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባረረች። እስካሁን 27 የስፔን፣ 34 የፈረንሳይ ያባረረች ሲሆን 24 የጣልያን ዲፕሎማቶችን ልታባርር እንደሆነ ተሰምቷል።

➡️ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የNATO አባላት ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ህብረቱ አባልነት እንዳይገቡ ያደረባትን ስጋት እንዲያከብሩ ጠየቀዋል። ኤርዶጋን ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ሀገር እንዲሆኑ ሀገራቸው ድጋፏን እንደማትሰጥ በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

➡️ የዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ቆሟል። ሁለቱም ወገኖች ለድርድሩ መደናቀፍ አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ነው።

➡️ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የፊንላንድ እና ስዊድን ለNATO አባልነት ያቀረሹትን ታሪካዊ ያሉትን ማመልከቻ ባደስታ እንደሚቀበሉትና አጥብቀው እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ባወጡት ተግለጫ ከUS ኮንግረስ እና ከNATO አጋሮች ጋር በመሆን በፍጥነት ፊንላንድ እና ስዊድን ወደ ጠንካራው የመከላከያ ህብረት (NATO) ለማምጣት እሰራለሁ ብለዋል።

➡️ ፊንላንድ NATO ለመቀላቀል ባሳለፈችው ውሳኔ ላይ የሩሲያ ምላሽ ድንገተኛ ቢሆንም እርምጃዎቹ ግን ወታደራዊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

#አልጀዚራ #ኤኤፍፒ #ዘኪየቭ_ኢንዲፔንደንት #አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ኃይሌ ምን አሉ ? ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በአዲስ አበባ ከቤታቸው እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም። ይህን ተከትሎ ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠቱ ቃል የሚከተለውን ብለዋል ፦ " ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ/ም ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጣው ከጓደኛው (አቶ ዮሐንስ ቧያለው) ጋር ቀጠሮ እንደነበረው…
#Update

ብርጋዴር ጄነራሉ ባሕር ዳር ናቸው ተብሏል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ምሽት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል።

ከአማራ ክልል የፀጥታ እና ደኅንነት እንዲሁም ከፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገው ሙከራ ለጊዜው አለመሳካቱን ቢቢሲ ጨምሮ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Wecare

በህፃናት ላይ የሚታዩ አስጊ የጤና ምልክቶች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ።

የ WeCare ET ሕክምና መተግበሪያ ሥመጥር ስፔሻሊስት ሐኪሞችን ባሉበት ቦታ ሆነው ለማማከር የሚያስችል መተግበሪያ ነው።

መተግበሪያውን ለመጫን ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ለበለጠ መረጃ 9394 ላይ ይደውሉልን።
መረጃዎችን ለማግኘት wecare.et ን ይጎብኙ
Wecare Et social medias

📌 Telegram: https://publielectoral.lat/WeCareET
#selamdoctor #wecareet
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች በእስር ላይ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎች የእስር ሁኔታን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ክትትል ሲያደርግ ነበር።

በተጨማሪ ከፓርቲውና ከእስረኞች ቤተሰቦች በቀረቡ አቤቱታዎች መነሻነት ከመጋቢት 1 እስከ 10 / 2014 ዓ/ም በቡራዩ ከተማ፣ በገላን ከተማ እና በሰበታ ፖሊስ መምሪያዎች በአካል በመገኘት ክትትል በማድረግ እስረኞችን፣ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎችን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተወካዮችን በማነጋገር ምርመራ አድርጓል። 

ኢሰመኬ በቡራዩ ፖሊስ መምሪያ በእስር ላይ የነበሩ፦

➡️ አቶ ሚካኤል ጎበና
➡️ አቶ ኬኔሳ አያና
➡️ ዶ/ር ገዳ ወልጅራ
➡️ አቶ ዳዊት አብደታ
➡️ አቶ ለሚ ቤኛ
➡️ አቶ ገዳ ገቢሳ የተባሉ የፓርቲው አመራር መሆናቸውን የገለጹ ስድስት እስረኞችን አነጋግሯል።

በተጨማሪ ኮሎኔል ገመቹ አያና በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል/እንዲሁም አቶ አብዲ ረጋሳ ገላን ከተማ በሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፖሊስ ካምፕ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ መሆኑን ከቤተሰብና ከጠበቆቻቸው መረዳት ተችሏል፡፡

በዚህ ምርመራ መሰረት፣ ፍ/ቤት በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደላቸው፣ የክስ መዝገቦቻቸው ተዘግተው በፍርድ ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱ፣ ምንም አይነት ክስ ያልተመሰረተባቸውና ዐቃቤ ሕግ ክስ የማይመሰርትባቸው መሆኑን በማረጋገጥ የምርመራ መዝገባቸው የተዘጋ፤ሆኖም ከወራት እስከ 2 ዓመት ለሚሆን ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙና የተወሰኑትም በእስሩ ሂደት በተፈጸመ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እና ድብደባ ለተለያዩ የአካል ጉዳቶችና የጤና እክል የተጋለጡ እስረኞች መሆናቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች በእስር ላይ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎች የእስር ሁኔታን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ክትትል ሲያደርግ ነበር። በተጨማሪ ከፓርቲውና ከእስረኞች ቤተሰቦች በቀረቡ አቤቱታዎች መነሻነት ከመጋቢት 1 እስከ 10 / 2014 ዓ/ም በቡራዩ ከተማ፣ በገላን ከተማ እና በሰበታ ፖሊስ መምሪያዎች በአካል በመገኘት ክትትል በማድረግ እስረኞችን፣…
#OLF

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፦

" የኦነግ ፓርቲ አመራሮች ለተራዘመ ጊዜ ከሕግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙ በመሆኑ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ እና ለደረሰባችው ጉዳት ሊካሱ ይገባል።

በተጨማሪ የፍርድ ቤትና የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ እየተጣሰ እስረኞቹ ከሕግ ውጪ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ስለሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አፋጣኝ ማጣራት አካሂዶ ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል "

▪️

የኢሰመኮ የሲቪል፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል ፦

" ታሳሪዎቹ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በመሆናቸው በሕዝባዊ አገልግሎት ስራቸው ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይጋለጡ ጥበቃ ሊደረግ ሲገባ፤ በተግባር የተገላቢጦሽ መሆኑ አሳዛኝ ነው ጉዳዩ አፋጣኝ እልባት ያስፈልገዋል "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሄዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ (የ2014 ዓ/ም) መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤውን አስመልክቶ ፥ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው ፤ ጉባኤው…
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 23 የመወያያ አጀንዳዎችን አጽድቆ በመወያየት ልዩልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ጀምሯል።

ዓመታዊው የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በጸሎት ከተጀመረ በኋላ በትላንትናው ዕለት በጠዋቱ መርሐ ግብር የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ መልዕክት አዳምጧል።

በመቀጠልም ሰባት አባቶችን የያዘ የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላትን በመሰየም አጀንዳዎችን አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ካደረገ በኋላ በኮሚቴው ተዘጋጅተው የቀረቡለትን አጀንዳዎች መርምሮ ማስተካከያ ካደረገባቸው በኋላ አጽድቋቸዋል።

በመቀጠልም በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል መሰረት የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ መልዕክት ያጸደቀ ሲሆን ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጠዋት የጉባኤ ውሎው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ የሚጠበቅ ሲሆን ከሰዓት በኋላን ጨምሮ እስከ እሁድ ድረስ በበዓላት ምክንያት ጉባኤው እንደማይካሔድ ታውቋል።

ምልዐተ ጉባኤው ከሰኞ ጠዋት ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን በማከናወን ቀሪ አጀንዳዎችን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia