TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Orange

የፈረንሳዩ ኦሬንጅ የቴሌኮሙንኬሽን ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎትን ማሳወቁ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ መግዛት የሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን ከሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ መጠየቋ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት የቀድሞው ፋራንስ ቴሌኮም የአሁኑ ኦሬንጅ ቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት በይፋ ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል።

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከዚህ ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መወያየታቸውን በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ፥ “በኢትዮ-ቴሌኮም ካፒታል ውስጥ ለመግባት በይፋ ካሳወቀው ኦረንዥ (ቴሌኮም) ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ኢኮኖሚዋና ገቢዋ በፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኘውና ከ100 ሚሊየን ህዝብ በላይ ያላት አገራችን በውጭ ባለሀብቶች ዘንድ ያላት ተፈላጊነት እንደቀጠለ ነው” ብለዋል።

ኦሬንጅ ኩባንያ አሁን ላይ ፈረንሳይን ጨምሮ በአውሮፓ፤ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ የቴሌኮሙንኬሽን አገለግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን አጠቃላይ የድርጅቱ አጠቃላይ ሀብት ከ100 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ነው።

ድርጅቱ እስከ ፈረንጆቹ 2020 ድረስ በ26 የዓለማችን አገራት ከ250 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት። ከዚህ ውስጥ ከ200 ሚሊዮን በላይ ያህሉ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የብሮድባንድ ተጠቃሚዎች ናቸው።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
የቦዴፓ ዕጩ ተወዳዳሪ ሞተው ተገኙ።

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት አቶ አይናድስ ሞላ ደንበሩ በግልገል በለስ ከተማ ሞተው መገኘታቸውን ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳወቀ።

ከዚሁ ጋር በተገኛ ፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃል ፥ "አቶ አይናድስ ሞላ ትናንት ማታ በግልገል በለስ ከተማ ተገድለው ተገኝተዋል" ብለዋል።

አክለውም ፥ "እጅግ በጣም አዛሳኝና ልብ ሰባሪ ክስተት ነው፤ የአሟሟቱ ሁኔታ ገና እየተጣራ ይገኛል" ሲሉ ገልፀዋል። ፓርቲው ለድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች፣ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛልም ብለዋል።

መረጃው ከኢት ኤፍ ኤም ሬድዮ እና ከፓርቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 3,400 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 97 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 93 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#Eid_al_Adha

በዓለም ላይ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዛሬውን የኢድ አል አደሃ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ሲያከብሩት ውለዋል።

ከላይ በተለያዩ ሀገራትና አካባቢዎች የነበረውን የበዓል ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን እንድትመለከቷቸው ልከንላችኃል።

ፎቶዎቹ ፦
- በአል አቅሳ መስጊድ (እየሩሳሌም)
- በታላቁ ካምሊካ መስጊድ (ቱርክ፤ ኢስታንቡል)
- በኢራቅ (ኪርኩክ)
- በኬንያ (ናይሮቢ)
- በየመን (ሰንዓ)
- በአፍጋኒስታን (ሄራት)
- በሱማሊያ (ሞቃዲሾ) የነበረውን የበዓል ድባብ የሚያሳዩ ናቸው።

የፎቶ ባለቤቶች : AFP , AP , Anadolu , EPA , Reuters

@tikvahethiopia
#Tokyo2020

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ 🇪🇹 አትሌቲክስ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ተጓዥ ቡድን ዛሬ ምሽት ወደቶኪዮ ይበራል። አትሌቶቻችን በሰላም እንዲገቡ እንመኛለን። በመጪው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከፍ እንደሚያደርጉ ባለሙሉ ተስፋ ነን።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ወቅታዊ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታ ፦

የትግራይ ክልል ከአፋር ክልል እና አማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስኑት አካባቢዎች ግጭቶች ስለመቀጠላቸው ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከቀናት በፊት የህወሓት ታጣቂዎች ወደአፋር ክልል ዘልቀው ጥቃት ስለመፈፀማቸው መግለፃቸው አይዘነጋም።

በየአካባቢው ስላሉ መረጃዎች በመከላከያም ሆነ በሌሎች አካላት ዝርዝር መረጃ ባይሰጥባቸውም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለያየ ያልተረጋገጡ መረጃ በስፋት ይሰራጫሉ።

መሬት ላይ ስላለው የወታደራዊ እንቅስቃሴ የተለያዩ አክቲቪስቶች እና የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚያሰራጩት መረጃ ውጭ በግልፅ እና በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም ፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁሙን እያከበረ ትንኮሳ ሲፈፀምበት አስፈላጊውን የኃይል እርምጃ እንደሚወስድ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከትላትና በስቲያ ከሳምንታት በኃላ ወደሚዲያ ብቅ ያሉት የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ፥ ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት በአስተማማኝ ቁመና ላይ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

TPLF የትግራይ ህዝብ ማዕከሌ ነው የሚል ከሆነ እስካሁን ህዝቡን ያሰቃየው እንደሚበቃው አውቆ ለ3ኛ ዙር ቆም ብሎ እንዲያስብ ፤ መንግስት ያመቻቸውን የተናጠል የተኩስ አቁም እሱም ተግብሮ የሚፈልገውን ፖለቲካዊ ጥያቄ መደራደር እንዳለበት እንመክራለን ብለዋል ጄኔራሉ።

ከዚህ ውጭ በቅድመ ሁኔታ ተሽቆጥቁጦ ሰላም ሊመጣ እንደማይችል መታወቅ አለበት ፤ ቅድመ ሁኔታ ደርድሮ እዚህ ውስጥ ተገብቶ ነው የምደራደረው የሚለው ተቀባይነት አይኖረውም ሲሉም ተደምጠዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-07-21

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ ስታንዳርድ በጊዜያዊነት ታግዷል፤ ለምን ? አዲስ ስታንዳርድ ትላንት በፌስቡክ ገፁ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለጃከን አሳታሚ የተሰጠውን ፈቃድ በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል። ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፈቃዱን ያገደበት ምክንያት አላብራራም ብሏል ፤ የሚዲያ ሥራዎቹንም ከሐምሌ 8/2013 ጀምሮ በጊዜያዊነት ማቆሙን የጃከን አሳታሚ አሳውቋል። ኩባንያው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ በሰፈረው…
አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተጣለው ጊዜያዊ እገዳ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ የበየነ መረብ ሚዲያ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ማንሳቱን ተሰምቷል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው እገዳውን ለማንሳት መወሰኑን ያስታወቀው።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል፡፡

:አዲስ ስታንዳርድ' በሕወሓት የሚመራውን ኃይል “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በመድረስ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ ሆኗል” በሚል ሚዲያውን በጊዜያዊነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

እገዳው መነሳቱን በማስመልከት በድረገጹ መግለጫ ያወጣው አዲስ ስታንዳርድ፣ አስቀድሞም እገዳ የተጣለበት ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑን ገልጿል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ግን ከሚዲያው ጋር በተያያዘ ያሉ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ቀጣይ መዘዛቸው ስለማይታወቅ እገዳ አንስቶ ለመወያየት መምረጡን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የሚዲያ ዐዋጅ በቅርብ ጊዜ የወጣ ከመሆኑ ባለፈ ዐዋጁ በሚደነግገው መሰረት ገና ቦርድ አለመቋቋሙን የገለጹት አቶ መሀመድ፣ ተቋሙ በሽግግር ላይ ከመሆኑ እና ሀገሪቱም ካለችበት ሁኔታ አንጻር በባለስልጣኑ ውሳኔዎች ዙሪያ የሚፈጠሩ ክፍተቶች እንደሚኖሩ አምነው በመነጋገር እየተሸሻሉ እንደሚሄዱ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ጊዜያዊ እገዳ ከጣለ በኋላ፣ ሁሉም ሚዲያዎች ከ "ሕወሓት" ጋር በተያያዘ የትግራይ መከላከያ ኃይል እና የትግራይ ክልል መንግስት የሚል ስያሜ እንዳይጠቀሙ የሚያስጠነቅቅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tokyo2020 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ 🇪🇹 አትሌቲክስ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ተጓዥ ቡድን ዛሬ ምሽት ወደቶኪዮ ይበራል። አትሌቶቻችን በሰላም እንዲገቡ እንመኛለን። በመጪው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከፍ እንደሚያደርጉ ባለሙሉ ተስፋ ነን። Photo Credit : EPA @tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #TokyoOlympics2020

በቶኪዮ 2020 (2021) በአትሌቲክሰ ሃገራችንን ከሚወክለው የልኡካን ቡድን መካከል የመጀመሪያ ዙር ተጓዥ የሆኑት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የቡድኑ ኦፊሻል ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የፌዴሬሽኑ አቃቤ ነዋይ እንዲሁም የአትሌቲክስ ቡድኑ መሪ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ትላንት ምሽት ወደ ጃፓን ቶኪዮ መጓዛቸውን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

@tikvahethiopia