TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁በደሌ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ማለዳ ላይ ነው በደሌ ከተማ የገቡት።

በበደሌ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከቡኖ በደሌ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያለስራ ተቀምጠናል...

"ሰላም ፀግሽ M እባላለሁ ከሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ተመራቂ ሀኪም ነኝ። ከሀዋሳ፣ መቀለ፣ ድሬዳዋ፣ ዋቻሞ እና አዲግራት ዪኒቨርሲቲ 490 የምንሆን ተመራቂ ሀኪሞች ከወር በላይ ያለስራ ቤታችን ነን። መንግስት በጀት ከሌለው እንደሌሎች ተመራቂዎች የመስሪያ ፈቃድ(License) ይስጠን። ከ 6 ዓመት በላይ ተምረን የቤተሰብ እርዳታ መጠየቅ #ያሸማቅቃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኒውዝላንድ በሁለት መስጊዶች ላይ በተፈፀመ ጥቃት 50 ሰዎችን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ የአዕምሮ ምርመራ እንዲያደርግ ታዘዘ፡፡ ተጠርጣሪው የፍርድ ሂደቱን መከታተል ይችላል ወይስ የአዕምሮ በሽተኛ ነው የሚለውን ለመወሰን በባለሙያዎች እንደሚታይ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ካሜሮን ማንዴር ተናግረዋል፡፡ ግለሰቡ በ50 ሰዎች ሞት እና 39 ሰዎችን ለመግደል ባደረገው ሙከራ ክስ እንደሚመሰረትበትም ነው የሚጠበቀው፡፡ ባለፈው ወር በኒውዝላንድ የተፈፀመው ይህ ጥቃት በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የተባለ ሲሆን፥ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃንዳ አርዴርን እለቱን የጨለማው ቀን ሲሉ ገልፀውታል፡፡ ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሯ የተለያየዩ ዘመናዊ የጦር መሳሪዎችን ለማገድ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናዝራዊት አበራን የኢትዮጵያ ልዑክ በቀጣይ ማክሰኞ ይጎበኛታል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አደገኛ አፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ በቻይና እስር ላይ የምትገኘው ናዝራዊት አበራ በኢትጵያ ልዑክ በቀጣይ ማክሰኞ እንደምትጎበኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በሰጡት መግለጫ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የናዝራዊት አበራን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቻይና ጁዋንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ናዝራዊት አበራን ለሶስት ጊዜያት እንደጎበኟት ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት፡፡

ቃል አቀባዩ የቻይና መንግስት እስካሁን ምንም አይነት ክስ እንዳልመሰረተ የገለፁ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጉዳዩን በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለ መሆኑን ገልጸዋል።

Via #FBC/የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአፋር ክልል-ገዋኔ🔝

"ሰላም ፀግሽ ከ አፋር ክልል ገዋኔ ከተማ ነው። በአካባቢው ሰላምን ለማስከበር ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ወዲያ በአከባቢው ላይ ፍየል ሲጠብቁ ከነበሩ እረኞች ጋር አነስተኛ ግጭት በመፈጠሩ አንድ ወጣት ተገድሎአል። በዚህም ምክንያት በአከባቢው ላይ የሚገኙ ወጣቶች ተሰብስበው መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች መንቀሳቀስ አልቻሉም። ከሁለቱም ቦታ የሚመጡ መኪኖች ቆመዋል ማለትም ከአአ-ጅቡቲ እንዲሁም ከ ጅቡቲ-አአ። በተጨማሪም ወደ መቐለ የሚጒዙም የህዝብ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ይገኛሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወ.ሶ.ዩ/WSU/🔝

"ጅብሪል እባላለሁ ከዛሬ ጀምሮ ለ2ቀን የሚቆየው Ethiopian Horticultural Science Society #በወላይታ_ሶዶ_ዩንቨርሲቲ አዘጋጅነት በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሪሰርች ማዕከላት ተገኝተን ጉባኤውን መካፈል ጀምረናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህዝቡ ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ትግል ወደ ኢኮኖሚው በማዞር የኢኮኖሚ ትግል ማድረግ እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ተገኝተው ከህዝብ ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ። በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት ትግል መደረግ ያለበትና ትኩረት መሰጠት ያለበት አገርን እንዴት መገንባት ይቻላል? በሚለው ላይ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የተለመደውን የአቃፊነት፣ አብሮ የመኖርና የመቻቻል ባህሉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

#አፋር #ገዋኔ

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ እንዲሁም ከ ጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል። በተጨማሪም ወደ መቐለ የሚጒዙም የህዝብ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህዝቡ ትግሉን ወደ #ኢኮኖሚው ማዞር አለበት" የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ #በደሌ

@tsegabwolde @tikvahethiopia