TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpdateSport የአውሮፓ ቻምፕዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆኗል...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ግርማ...

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ #የመጀመሪያ ሰው መሆናቸውን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ገለጸ፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት በ12 አመት የፕሬዝዳንትነት ቆይታቸው የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን በማቋቋም ይታወሳሉ፡፡ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ካቋቋሟቸው ተቋማት መካካል በ1995 ዓ.ም የተመሰረው የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ይጠቀሳል፡፡

በወቅቱ የአይን ባንኩን ከማቋቋም ባሻገር የአይን ብሌናቸውን ብርሃናቸውን ላጡት ወገኖች ለመለገስ ቃል ገብተው ነበር፡፡

ይህም በሀገሪቱ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል፡፡ እናም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ህይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአይን ብሌናቸው መለገሱን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ለምለም አየለ ገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ቡና❤️ባህር ዳር ከነማ!!

‹‹ከእግር ኳስ ደጋፊዎች 50 ሺህ 315 ብር ተሰብስቧል፤ የተሰበሰበው ገንዘብ በማረሚያ ቤት ከፍተኛ የአካል እና የስነ ልቦና ጉዳት ለደረሰበት ለአቶ #ዮሀንስ_ጋሻው እና ለተፈናቃዮች የሚውል ነው፡፡››
.
.
የባሕርዳር ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማሕበር የባሕር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር በባሕር ዳር አለማቀፍ ስታዲዮም ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉና በማረሚያ ቤት ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ የሚሆን ገንዘብ አሰባስቧል፡፡

አብዛኛውን ድርሻ ከባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎች የተገኘ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቡና እና ከባሕርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች 50 ሺህ 315 ብር ተሰብስቧል፡፡

የተሰበሰበው ገንዘብ በማረሚያ ቤት ከፍተኛ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት ለደረሰበት አቶ ዮሀንስ ጋሻው የሚውል እንደሆነ ነው ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው፡፡

የባሕር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ሂሳብ ሹም አቶ ቢኒያም ላቀው አንደነገሩን አቶ ዮሀንስ አፋጣኝ ህክምና ስለሚያስፈልጋቸው እና ከፍተኛ የህክምና ወጪ ስለተጠየቁ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖችም እርዳታ ይደረጋል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ #ቢኒያም ገለፃ እስካሁን ገንዘብ ሲሰበሰብ በክለቡ ደጋፊዎች ላይ ብቻ የታጠረ ነበር፡፡ አሁን ግን የተፈናቃይ እና የተጎጅዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ከክለቡ፣ ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከባለሃብቶች እና ሌሎች የክለብ ደጋፊዎችን በማስተባበር ለሌሎች ወገኖችም እርዳታውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጦልናል፡፡ ከባሕር ዳር አለማቀፍ ስታዲዮም የመግቢያ ትኬት ሽያጭ የተወሰነ ለሰብዓዊ እርዳታ እንዲለቀቅ እንጠይቃለን ብሏል፡፡

#ከፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በቀጣይ በሰብዓዊ እና ማሕበራዊ ድጋፍ ላይ ስፖርቱ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማሳደግ መታሰቡን ተሰምቷል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️
ትኩረት ለሞያሌ‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

"በሀመር እና ኛንጋቶም ወረዳዎች በአርብቶ አደሮች መካከል በተከሰተው #ውዝግብ የሀመር አርብቶ አደሮች ከጅንካ ወደ ኛንጋቶም ሲሄዱ የነበሩትን ሁለት የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች እና ሁለት የመንግስት መኪናዎች ከእነ ሙሉ ተሳፋሪዎቹ ከትላንት ከሰአት ጀምሮ #ታግተዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አሜሪካ ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ በሶማሊያ በፈፀመችው የአየር ኃይል ጥቃት 62 #የአል_ሸባብ ታጣቂዎችን መግደሏን አስታውቃለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolse @tikvahethiopia
ቤንሻጉል ጉምዝ‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእርሻና በዕጣን ሙጫ ኢንቨስትመንት ዘርፍ መሬት ወስደዉ ባላለሙ 102 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸዉ መሰረዙን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

ከ164 በላይ ለሚሆኑ ባለሃብቶች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አከባቢ ደንና መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ከ6 መቶ በላይ ባለሃብቶች በእርሻ ኢንቨስትመንት፣ በዱር ዕጣንና ሙጫ እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ ተሰማርተዉ ይገኛሉ፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ሰሞኑን ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ከ62 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የኢንቨስትመንት እርሻ መሬት ተቀብለዉ ያላለሙ 102 ባለሃቶች ፈቃዳቸዉ ሙሉ ለሙሉ በመሰረዝ ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲደረግ ተወስኗል ብለዋል የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ኢሳቅ፡፡

ፎርጂድ የባንክ እስቴትመንት በማቅረብ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ወስደዉ ደን እየጨፈጨፉ ከሰል ሲያመርቱ የተገኙ 3 ባለሃብቶች በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል፡፡

ሰፋፊ መሬቶችን ተቀብለዉ በዱር ዕጣንና ሙጫ ዘርፍ የተሰማሩ 20 ባለሃብቶች መካከል የ14ቱ ባለሃብቶች ፈቃድ በመሰረዝ መሬቱን ለአልሚ ባለሃብቶችና ለስራ አጥ ወጣቶች እንዲተላለፍ ዉሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡

ከቀረጥ ነፃ ገብተዉ ለታለመለት ዓላማ ያልዋሉ የ37 ባለሃብቶች ንብረት የሆኑ 56 የእርሻ ትራክተሮችና 26 ፒክአፕ መኪኖችን ባሉበት እንዲታገዱና የገቢዎች ሚኒስቴር ተከታትሎ ህጋዊ ዕርምጃ እንዲወስድ የኢንቨስትመንት ቦርዱ ወስኗል፡፡

እንዲሁም በአፈፃፀማቸዉ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ሚገኙ 164 ባለሃብቶች የመጨረሻ
#ማስጠንቀቂያ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡

ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንኮች ብድር የወሰዱ 113 ባለሃብቶች ብድራቸዉን በአግባቡ እየመለሱ ባለመሆናቸዉ አበዳሪ ተቋማት የህግ አሰራሩን ተከትለዉ እርምጃ መዉሰድ እንዳለባቸዉ ዉሳኔ መተላለፉን አቶ ኢሳቅ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት በማዕድን ዘርፍ ለተሰማራ አንድ ባለሃብት ብቻ እስከ 300 ሄክታር የማዕድን መሬት ይሰጥ እንደነበር የተናገሩት ሃላፊዉ በዘርፉ ለተሰማራ ባለሃብት 20 ሄክታር ብቻ እንዲሰጠዉና የተቀረዉን ለመሬት ባንክ ገቢ እንዲያደርግ ዉሳኔ ተላልፏል፡፡

በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች ለአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ዉስንነት መስተዋሉን የገመገመዉ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርዱ የተወሰኑ ባለሃብቶችም የፀጥታ ስጋት በመሆናቸዉ እርምጃ ለመዉሰድ መገደዱን አቶ ኢሳቅ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

©EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️መንግስት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲመለከተው ተማሪዎች ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየትን አስመልክቶ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አወጀ።
በዚህም መሰረት በነገው እለት ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

via~Ahadu Radio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የአስከሬን ሽኝትና የቀብር ሥነስርዓት፦

1. ማክሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2011 ከምሽቱ በ12 ሰዓት በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው በመኖሪያ ቤታቸው የአስከሬን አቀባበል ይደረጋል።

2. ታህሳስ 10 ቀን 2011 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስንብት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

3. ታህሳስ 10 ቀን 2011 ቤተሰቦቻቸውና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ይፈፀማል።

የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአገራዊ አገልግሎታቸው የሚመጥን ሽኝት የሚደረግላቸው መሆኑንና ለክብራቸውም መድፍ የእደሚተኮስ ከፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️መንግስት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያለውን ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲመለከተው ተማሪዎች ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia