TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TPLF #እንዳስላሰሽረ

በሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ።

ህወሓት ሰላማዊ ስልፍ ለማካሄድ ከጳጉሜን 3 - 5 ባሉት ቀናት የጠየቀ ሲሆን ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነው።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እንዳስላሰ ሽረ ቅርንጫፍ ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም በፃፈው የሰላማዊ ሰልፍ የፍቃድ ደብዳቤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰላማዊ መንገድ ድምፁ ለማሰማት መፈለጉ ያትታል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ፍቃድ በጠየቀበት ሰላማዊ ሰልፍ ፦

"
- ከባቢያዊ መለያየትና አገር የሚበትኑ ተግባራት ይቁሙ !
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የፀለምቲና ራያ ተመላሽ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ይጠበቅ !
- የህዝበኝነት ፓለቲካ በትግራይ እንቃወማለን !
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይተግበር !
- ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመለት ዓላማ ይተግብር !
- ህወሓትን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- ህወሓት ሰላምን ይደግፋል !
- ጦርነት የሚናፍቅ የህወሓት መሪ የለም ! "

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እንደሚያሰማ በፍቃድ መጠየቂያ ደብዳቤው ላይ ገልጿል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ለጠየቀው ' ሰላማዊ ሰልፍ ' የማካሄድ ጥያቄ መልስ የሰጠው የእንዳስላሰ ሽረ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ባለው የፓለቲካ ትኩሳት እና የአዲስ ዓመት መለወጫ በመሆኑ ምክንያት የፀጥታ ሃይሉ የተደራረቡ ስራዎች ስላሉበት ሰላማዊ ስልፉ እንዳልተፈቀደ አሳውቋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ በተምቤን ዓብዩ ዓዲ ዓዲግራትን ማይጨው ካካሄዳቸው ህዝባዊ ውይይቶች በመቀጠል በአክሱምና በእንዳስላሰ ሽረ ከተማዎች ለማካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም አቶ ጌታቸው ባጋጣመቸው የጤና እክል ምክንያቱ ውይይቱ ለሌላ ጊዜ መዛወሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ70እንደርታ

" የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፈቀድልን ህዝባዊ ስብሰባ ተከለከልን " ሲል ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን አሰማ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃል ፥ _ እሁድ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው አግኣዚ የስብሰባ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቕዶልን አባልና ደጋፊዎቻችን ጠርተን ስናበቃ አዳራሽ እንዳንገባ በታጣቂዎች ተከልክለናል " ብለዋል።

" በህጋዊ መንገድ የተፈቀደ ህዝባዊ ውይይት መከልከልና ታዳሚዎች ማንገላታት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው " ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር በተግባሩ ማዘናቸው በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተናግረዋል።

" የመቐለ ከተማ ፀጥታ ፅ/ቤት በፃፈልን ደብዳቤ መሰረት ስብሰባውን የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ ፓሊስ መድቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ማንነታቸውና ተጠሪነታቸው የማይታወቁ ሌሎች ሃይሎች ተሳብሳቢው ወደ ግቢ እንዳናሰግባ የአዳራሹ ሰራተኞች ሳይቀር እንዳይገቡ በር ላይ ለነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ስብሰባው ሳይደረግ ቀርተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እንደምክንያት ያቀረቡትም የከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለጋስ ማርያም ' እኔ ካልደወልኩኝ እንዳይገቡ ብለዋል ' የሚል ሲሆን ግለሰብዋ በደብዳቤ የፈቀዱትን ስብሰባ በዚህ መንገድ የከለከሉበት ምክንያት ለመጠየቅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸውን በመዝጋታቸው ምክንያት ልናገኛቸው አልቻልንም " በማለት ገልጸዋል።

የመቐለ ከተማ ፀጥታ ዘርፍና ፓሊስ መንግስታዊ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት መሞከሩን አመልክተው " ምስጋና ይገባዋል " ብለዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ፓሊስ እስከ አሁን ሰዓት ስለ ክልከላው የሰጠው ይፋዊ ማብራርያም ሆነ መግለጫ የለም። 

ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአንድ ዓመት በፊት ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ መመስረቱ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

ባጋጠመ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 በላይ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ተቀጠፈ።

የትራፊክ አደጋው ዛሬ  ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት አከባቢ የተከሰተ ሲሆን የሰሌዳ ቁጥር TG - 04539 የሆነ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከዓድዋ ወደ መቐለ ሲጓዝ ወርዒ ልዩ ቦታ  እንዳፈላሲ ቁልቁለት ሲወርድ ወደ ገደል በመግባቱ ነው አደጋው ያጋጠመው።

በውስጥ ከተሳፈሩ ሰዎች ከ10 በላይ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመላክተው 48 ሰዎች የመጫን አቅም ያለው መለስተኛ አውቶቡስ በአጋጣሚ 20 ሰዎች ብቻ አሳፍሮ መጓዙ ለሟችና ቁስለኞች መቀነስ ምክንያት ሆኗል።

የአደጋው ምክንያት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ይህ ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል ፤ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አይለያችሁ።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
" 60 ሰዎችን አግተው ወስደዋል ፤ 369 ከብቶች ተዘርፈዋል ፤ 19 ቤቶችን አቃጥለዋል " - በትግራይ ክልል የምስራቃዊ ዞን

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች 60 ሰዎች አግተው መውሰዳቸው 369 ከብቶችን በመዝረፍ 19 ቤት ማቃጠላቸው ተገልጿል።

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች የእገታ የዝርፍያና ቤቶች የማቃጠል ተግባር የፈፀሙት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የኢሮብና ጉሎመኸዳ ወረዳዎች እንደሆነ የዞኑ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ታግተው ከተወሱዱት 60 ሰዎች ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወጣቶችና የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ናቸው።

የኢሮብና የጉመኸዳ ወረዳዎች 8 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት የትግራይ ጦርነት ከተጀመረበት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወዲህ ሙሉ በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት የጉሎመኸዳ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ፥ ባሳለፍነው ዓመት መጨረሻ በዜጎች ላይ ያነጣጠረ አፈና ተባብሶ መቀጠሉ አመልክተዋል።

" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ክልል ግዛታዊ አንድነት ወደነበረበት ባለመመለሱና የኤርትራ ሰራዊት ከአከባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ባለመውጣቱ ለአፈናና ለከባድ የፀጥታ ስጋት አደጋ ተጋልጠናል " ብለዋል።

የጉሎመኸዳ ወረዳ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ነብዩ ስዩም በበኩላቸው " በሙሉና በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ የወረዳው 4 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አስከአሁን 52 ወገኖች ታፍነው መወሰዳቸው እረጋግጠናል " ብለዋል።

" ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ሙሉ በሙሉ ሸዊት ለምለም በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት ሃላፊው " የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሰራዊት በአከባቢው የለም " ሲሉ ገልፀዋል።

በተያያዘ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከተለያዩ የኢሮብ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 8 ሰዎች ታፍነው 222 ከብት፣ 157 ፍየልና በጎች ሲዘረፉ 19 ቤቶች በኤርትራ መንግስት መቃጠላቸው የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ሊቀ-መንበር ዶሪ አስገዶም አስታውቀዋል። 

የወረዳው የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እንደገለፀው አራት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው የአከባቢው ማህበረሰብ ለአራት ዓመታት በከፍተኛ የፀጥታ አደጋ ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ስሜት እንደሚገኝ የገለፁት የወረዳዎች ነዋሪና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ገልጸዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተተግብሮ የኤርትራ ጦር ከያዘው አካባቢ እንዲወጣ ፣ የህዝብ ደህንነት እንዲጠበው፣ ተፈናቃዮች ወደ ቂያቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ።

ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :- 

1. አቶ ጌታቸው ረዳ 
2. አቶ በየነ ምክሩ
3. ፕ/ር ክንደያ ገ/ሂወት
4. ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፈይ
5. ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃዲቕ
6. አቶ ረዳኢ ሓለፎም
7. ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
8. አቶ ኢሳያስ ታደሰ
9. አቶ ሰለሞን መዓሾ
10. አቶ ሺሻይ መረሳ
11. ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር 
12. አቶ ርስቁ አለማው
13. አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
14. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
15. አቶ ሩፋኤል ሽፋረ 
16. አቶ ነጋ ኣሰፋ 

ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነት " አባርሪያችኃለሁ " ብሏል።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈገውና የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳና በርካታ የማእከለዊ ኮሚቴ አባላት " ህገወጥ " ያሉትን 14ኛ ጉባኤ በማካሄድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መልሶ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle  

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ። በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል። የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ…
#Tigray

" ... የቆየው አመራር በአካልና በስልክ ስልጣን ለማስረከብ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም  " -  አዲሱ የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ፍቓዱ 

በቅርብ በትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር የተሾሙት  የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ፍቓዱ " የቆየው አመራር በአካልና በስልክ ስልጣን ለማስረከብ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም " ሲሉ ተናገሩ።

ይህን ያሉት ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ነው።

አቶ ተኽላይ ፥ በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ከተሾሙ ሁለት ሳምንት መቆጠሩን ተናግረዋን።

ነገር ግን የቆየው አስተዳደር በአካልም ሆነ በስልክ የስልጣን ርክክብ ለማደረግ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም።

" በመንግስት በጀት የመንግስት ተፃፃራሪ ሆኖ መቆም ሽፍትነት ነው " ያሉት አቶ ተኽላይ " ከዚህ በኋላ መንግስት ሕግና ስርዓት ለማስከበር ይገደዳል " በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

በቅርቡ የተከሰተው የህወሓት መሰነጣጠቅ ተክትሎ በየቀኑ አዳዲስ ክስተቶች በመታየት ላይ ይገኛሉ።

(ለማስታወስ)

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው ተተኪ የሚባሉ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ  አባላት ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያልሰጡትን 14ኛው ጉባኤ አካሂደዋል፡፡

14ኛው ድርጅታዊ ጉባኤው ህጋዊ አይደለም ያሉት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤው የስራ አሰፈፃሚ አድርጎ የመረጣቸው የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሊያ ካሳና የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ገ/መድህን ምትክ አዳዲስ የዞን አስተዳዳሪዎች ሹመዋል፡፡

የዶ/ር ደብረፅዮኑ ህወሓት መስከረም 6 /2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ 14ኛ ጉባኤው ያልተሳተፉት የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላይ ኮሚቴ  አባላት ከአባልነትና ከድርጅታዊ የስራ ሃላፊነታቸው ማባረሩን አሳውቋል።

የእነ ዶክተር ደብረፅዮኑ ህወሓት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ መግለጫ ካወጣባቸው 16 የድርጅቱ የማእከላይ ኮሚቴ 5 አሁንም በጊዚያዊ አስተዳደሩ እውቅናና ተቀባይነት ያላቸው የትግራይ ደቡባዊ ፣ ደቡባዊ ምስራቅ ፣ ምስራቅ ፣ ማእከላዊ ፣ ሰሜናዊ ምዕራብና የምዕራብ ዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡

በእነ ዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤ የማእከላይ ኮሚቴ አመራር በመሆን ከተመረጡት መካከል ይትባረክ ኣማሃና ኤልያስ ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ዋናና ምክትል በመሆን በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ በሃላፊነት ይቀጥሉ ይሆን ? በቀጣይ የምናየው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :-  1. አቶ ጌታቸው ረዳ  2. አቶ በየነ…
#Tigray

" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አቅዷል " - በህወሓት ጉባኤ ያልተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት

በህወሓት ጉባኤ ላይ ያልተሳፉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም " ህገመንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን ሌላውን የማባረር ሞራልና ስልጣን የለውም " ብለዋል።

ከሰሞኑን በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማባረሩ ይታወሳል።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ " ህገ-መንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ሌላውን የማባረር ህጋዊና ሞራላዊ ስልጣን የለውም " ከማለት ባለፈ " መፈንቀለ መንግስት ለማካሄድ ማቀዱን ደርሰንበታል " ብለዋል።

" የህገወጡ ቡድን መሪ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጄኖሳይድ ፍትህ እንዲያገኝና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መታገል ሲገባው ጉዳቱ ወደ ቁጥር ጨዋታ በማውረድ የህዝብ መስዋእትና የወጣቶች ጉዳት ዋጋ እያሳጣው ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል " ኒው ሆራይዘን " ከተሰኘ የማህበራዊ ሚድያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ወቅትም " By the way ከአንድ ሚልየን በላይ አለቀ የሚለው ፤ ማስረጃ የለው፣ ጥናት የለው ፣ ለማስፈራርያ ነው የሚውለው። ተጨፍጭፈናል ለማለትም አይደለም ፣ ጄኖሳይድ ተፈፀመብን ለማለትም አይደለም። አመራሩ አስጨረሰን ይላል ፤ አመራር ለመምታት ፣ ስልጣን ለመያዝ የማይሰራ ነገር የለም። " ሲሉ ተናግረው ነበር።

በኃላም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ " በህዝባችን ላይ የተፈፀመው ጄኖሳይድ አሁንም በርካታ በወራሪዎች ስር ያሉ የትግራይ አከባቢዎች ነፃ ባለመውጣታቸው ምክንያት የተሟለ መረጃ መስጠት ባይቻልም የደረሰው እልቂት ግን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ መሆን እንደሚችል ለመግለፅ እፈልጋሎህ " የሚል ማስተባበያ ለመስጠት ሞክረዋል።

የአቶ ጌታቸው ቡድን ህገ-ወጥ ሲል የሚጠራውን የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድንን " ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ሸምጥጦ በመካድ የዓለም ማህበረሰብ የተከራከረለትና የመሰከረውና የህዝብ እልቂት ወደ ጎን በመተው ዋጋ የሌለው እንዲሆን ወሰኖ ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።

" ህገወጥ ቡድኑ ቡድናዊ የስልጣን ፍላጎቱ በፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ፣ በማሰፈራራትና ሃሳቦች በማፈን ለመጫንና ለማሳካት ላይ ታች በማለት ይገኛል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ይባስ ብሎ የመንግስት መዋቅር አንዲፈርስና ትግራይ መንግስት አልባ ሆና የረብሻና ግርግር ማእከል እንድትሆን እየሰራ ነው " ሲል አሳውቋል።

" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ማቀዱ ግልፅ ሆኗል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ጊዚያዊ አስተዳደሩና ህዝቡ ከአደገኛ አካሄዱ ሊያስቆሙት ይገባል " በማለት አክለዋል።

50 ዓመት ያስቆጠረ ድርጅት እንደ አዲስ እንዲመዘገብ በማድረግ የትግራይ ህዝብ ትግል የካደው ቡድን ህዝቡና የዳያስፓራ አባላት እንዲታገሉት ጥሪ አቅርቦ የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ለማስመለስ ፓለቲካዊ ውይይት መጀመሩን አመልክቷል።

መላው ህዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርቧል።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያልተሳተፉና ሂደቱን የተቋወሙት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነታቸው አባርሪያለሁ " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray

አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ።

በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል።

ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች አልፈፅምም ማለትና ማደናቀፍ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።

ሁለቱ የዞን የስራ ሃላፊዎች ከመስከረም 8/2017 ዓ.ም ከነበራቸው የስራ ሃላፊነታቸው ተሰናብተው የተሰጣቸው የመንግስት ንብረትና ስራ እንዲያስረክቡ በተፃፉላቸው የስንብት ደብዳቤዎች ተገልፆላቸዋል።

አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት በቅርቡ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተመረጡት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተክተው  የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና  አስተዳዳሪነት እንዲመሩ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾሙ ናቸው። 

በተመሳሳይ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 6/2917 ዓ.ም " ከአባላትና ከድርጅታዊ ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ ደብዳቤ የፃፈላቸው የህወሓት ማእካላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ማእከላይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የአክሱም ከተማ የፀጥታ ሃላፊ ፣  የተምቤን ዓብዩ ዓዲ ከተማ ከንቲባና ሁለት የዞን የስራ ሃላፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ በማደናቀፍ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል።  

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ። በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል። ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ…
#Tigray

" የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል።

ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር።

ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት አመራሮች ክፍፍል እና ስለ ጸጥታ ኃይሉ ተነስቷል።

ካቢኔው " ከጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና ውጪ ፦
- መንግስታዊ የስራ ምደባ ማካሄድ ፣
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ማፍረስ
- የመንግስት መዋቅር ለመረበሽና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

" መንግስት ለዚህ መሰል ተቀባይነት የሌለው እንቅስቃሴ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ከህወሓት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ካቢኔው " በአሁኑ ወቅት በህወሓት አመራሮች ዙሪያ የተፈጠረው መከፋፈል በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረ ተደርጎ መወሰዱ ልክ አይደለም " ብሏል።

" ክፍፍሉ በጥቂት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረ ነው " ያለው ካቢኔው " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከህወሓት ከሙሁራን ከፀጥታ አካላትና ከተፎካካሪ ድርጅቶች በተወጣጡ አካላት የተደራጀ መሆኑ ከግምት ውሰጥ በማስገባት ከህወሓት ክፍፍል ጋር አቆራኝቶ መግለፅ ልክ አይደለም " ሲል ገልጿል።

ካቢኔው ስለ ፀጥታ ኃይሎች ባነሳው ነጥብ " የፀጥታ አካላት ሁሉም ዓይነት ችግሮችና ፈተናዎች ተቋቁመው የህዝብ ፀጥታ ለማስከበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አወንታዊ እና እውቅና የሚቸረው ነው " ብሏል።

" ስራዎቻቸው ከማንኛውም የፓለቲካ አስተሳሰብ ነፃ በማድረግ ገለልተኛ አቋም ይዘው እንዲሰሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ይደግፋል ያበረታታል " ሲል አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ። በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች…
#Tigray
 
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።

ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው " ቡድን " ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።

መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ " የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ' ቡድኑ ' የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት " ይላል።

ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ' ቡድኑ' ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።

ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።

" ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል " በማለት አክለዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ  ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ  አውጥቷል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው  ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ  ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት  ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው " ብሏል።

ምንም እንኳን " ኢ-ህገመንግስታዊ " ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን " ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል " ሲል አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል።  አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ…
#Update

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሚመራው የህወሓት ቡድን ጋር ያላቸው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚሰራ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን ተናግሯል።

በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መስከረም 20/2017 ዓ.ም በመቐለ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።

ውይይቱ ለሁለት የተከፈለው ድርጅት ለማዳንና የትግራይ ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ያለመ  ነው ተብሏል።

በዚህም ወቅት በአቶ ጌታቸው የሚመራው ቡድን የተፈጠረው ልዩነት እንዲሰፋ እየሰራ ያለው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይሳካ የተሰለፈ የሰላም ፀር የሆነ ሃይል ነው " ብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የህወሓት ህጋዊነት እንዳይመለስ እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይፈፅምና የተገኘው ተነፃፃሪ ሰላም እንዳይቀጥል እንቅፋት የሆነው " የሰላም ፀር " ሲሉ የጠሩትን በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራውን ህወሓት ከሰዋል። 

" በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል ጉባኤ አካሂጃለሁ በሚል ሽፋን ራሱን እንደ ህጋዊ በመቁጠር የወረዳና የከተማ ምክር ቤቶች እየሰበሰበ ይገኛል " በማለት አክለዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል በስም ማጥፋት ተግባራት መሰማራቱ የገለፀው በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው የሚመራ ህወሓት ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብና ሰርዓት እንዲይዝ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ዛሬ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ላይ መሰረት ያደረገ ውይይት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia