#Tigray

አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ።

በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል።

ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች አልፈፅምም ማለትና ማደናቀፍ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።

ሁለቱ የዞን የስራ ሃላፊዎች ከመስከረም 8/2017 ዓ.ም ከነበራቸው የስራ ሃላፊነታቸው ተሰናብተው የተሰጣቸው የመንግስት ንብረትና ስራ እንዲያስረክቡ በተፃፉላቸው የስንብት ደብዳቤዎች ተገልፆላቸዋል።

አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት በቅርቡ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተመረጡት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተክተው  የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና  አስተዳዳሪነት እንዲመሩ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾሙ ናቸው። 

በተመሳሳይ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 6/2917 ዓ.ም " ከአባላትና ከድርጅታዊ ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ ደብዳቤ የፃፈላቸው የህወሓት ማእካላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ማእከላይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የአክሱም ከተማ የፀጥታ ሃላፊ ፣  የተምቤን ዓብዩ ዓዲ ከተማ ከንቲባና ሁለት የዞን የስራ ሃላፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ በማደናቀፍ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል።  

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia