TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል " በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል። መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው። ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን…
#Konso #Ale #Amaro

2023 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ።

በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ከ2014 ተፈታኞች ጋር ድጋሚ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

ትላንትና የኮንሶ ዞን 773 ተማሪዎች ከ5 ትምህርት ቤቶች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ መወሰኑን መግለፁን የሚመለከት መረጃ ልከንላችሁ ነበር።

ከኮንሶ ዞን ባለፈ በአማሮ ልዩ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች 1171 ተማሪዎች በኧሌ ልዩ ወረዳ በ3 ትምህርት ቤቶች 79 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

በአጠቃላይ በአንድ ዞን እና ሁለት ልዩ ወረዳዎች የድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱት 2,023 ተማሪዎች ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች በአካባቢያቸው ላይ የፀጥታ ችግር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ከፍተኛ በሆነ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ሆነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተፈተኑ ሲሆን ነገር ግን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊያስገባቸው የሚችል ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም።

@tikvahethiopia
🔈#Konso

" ታጣቂዎቹ ተመልሰው ይመጣሉ በሚል አሁንም በፍርሀት ውስጥ ነን " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች

ከሰሞኑ በወረዳው ዋና ከተማ ሰገን በድንገት ከወደደራሼ አቅጣጫ ተነስተው መጥተዋል ከባሉ ታጣቂዎች በፖሊስ ፣ በከተማው አስተዳደርና ፣ በንጹሀን ዜጎች ላይ በከፈቱት ጥቃት ከ10 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸዉን ተሰምቷል።

ቅዳሜ አመሻሽ ጀምሮ ጥቃቱ መከፈቱን የገለጹት ነዋሪዎች በከተማዉ ውስጥ የነበሩ ፖሊሶችና የአስተዳደር ቢሮ የጥቃቱ ኢላማና ቀዳሚ ሰለባ ከመሆናቸው በላይ የመጀመሪያ ዙር ጥቃት እንደተፈጸመ ድጋፍ የሚሰጥ ሀይል ከተለያዬ ቦታ ወደስፍራዉ በፍጥነት አለመላኩን ተከትሎ ሁለተኛ ዙር ጥቃት በበነጋታዉ ጠዋት መከፈቱን አስረድተዋል።

የወረዳው ነዋሪዎች " የሰው ነፍስና በርካታ ንብረት መዳን ሲችል ጉዳት ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

እስከእሁድ ጠዋት በቀጠለዉ ተኩስ ሱቆች መዘረፋቸውን ፣ ቤቶች መቃጠላቸዉና አካባቢው አስፈሪ መልክ መያዙን ተከትሎ አሁን ላይ በርካታ ሴቶችና ህጻናት ወደአጎራባች መንደሮች እየተሰደዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

" ከሀይቤና ቀበሌ በመነሳት የተለመደ የከብት ዘረፋና የነብስ ማጥፋት ወንጀሎች ነበሩ " ያሉት ነዋሪዎቹ " ካሁን በፊት ሁኔታውን መንግስት ይቆጣጠረዉ ዘንድ ጥያቄ ማንሳታቸውን ለአብነት እንኳን ከሳምንት በፊት በወረዳው አስተዳደር ከማህበረሰቡ ጋር በነበረው ስብሰባ መነሳቱን " ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ድንገት በመምጣት ጥቃት ያደርሳሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።

" ሁኔታዉ ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ በፊት ከወረዳው ባለፈ የዞንና የክልል አመራሮች ጣልቃ መግባት አለባቸው " በማለት " ቤታቸዉ ለተቃጠለባቸውና ንብረታችዉ ለወደመባቸው ግለሰቦች ዝናብ ላይ በመሆናቸው አፋጣኝ ድጋፍ እንፈልጋለን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ነዋሪዎቹ የመንግስት ኃይሎች ለእርምጃ መዘግየት ዋጋ አስከፈለን ሲሉም " አክለዋል።

ግጭቱን አስመልክተዉ የሰገን ዙሪያ አስተዳዳሪ አቶ ኡርማሌ ኡጋንዴ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጅ በሰጡት ቃል አስራ አንድ ሰው መሞቱን ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ ግን የሟቾቹን ቁጥር አስራ ሶስት በማድረስ ስምንቱን ነዋሪ አምስቱ ደግሞ ፖሊስ መሆናቸዉን ገልጸዉ ከዚህም ሊያልፍ ይችላል ብለዋል።

አሁን ላይ ከወረዳዉ ባለፈ በዞኑ ደረጃ የኮንሶ ዞን የሀዘን መግለጫ በማዉጣት ሁኔታዉን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የዞኑን ህዝብ ግንኙነት ቢሮና የፖሊስ መምሪያ ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

ዞኑ " ጽንፈኛ እና አሸባሪ " ያላቸው ኃይሎች በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ንጹሃን ሰዎችና የፖሊስ አባላት መገደላቸውን አረጋግጧል።

ምን ያህል ሰው እንደተገደለ የሰጠው ቃል የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM