TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OROMIA

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።

ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።

ኢሰመኮ ፦

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)

ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ #በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦

* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።

* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።

* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Oromia

ዛሬ ሌሊት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016…
#Oromia

ኢሰመኮ ፦

- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።

- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤ 
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።

- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። 

- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።

ለምሳሌ ፦

👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።

👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።

👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።

👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

#Oromia #Ethiopia #EHRC

@tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OROMIA #PEACE " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ…
ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ?

#አልተገኙም

" ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ

በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም

የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል።

ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል።

የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል።

" ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል።

" የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል።

" በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA
#OFC #OLF

@tikvahethiopia
#ethiotelecom #Oromia

በኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን በጸጥታ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ 87 የሞባይል ጣቢያዎች ተጠግነው በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎችና ከተሞች ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት እንዳገኙ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ተቋሙ ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት በምዕራብ እና በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሩ ጉዱሩ እንዲሁም ቄለም ወለጋ ዞኖች የሚገኙ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል።

የኃይል አቅርቦትን ባላገኙ አካባቢዎች ላይ ጀነሬተር ፣ ነዳጅና አስፈላጊ ግብዓት በማሟላት የጥገና እና የማሻሻያ ስራዎች በማጠናቀቅ 87 የሞባይል ጣቢያዎችን አገልግሎት ዳግም በማስጀመር በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎች እና ከተሞች አገልግሎት እንዳገኙ አሳውቋል።

እስካሁን በተከናወኑ ስራዎች ፦
- በሆሩጉዱሩ 18 የሞባይል ጣቢያዎች፣
- በምዕራብ ወለጋ 19 ጣቢያዎች፣
- በቄለም ወለጋ 17 ጣቢያዎች፣
- በምስራቅ ወለጋ 12 ጣቢያዎች
- በምዕራብ ሸዋ 1 ጣቢያ ጥገና ተደርጎ አገልግሎት ማስጀመር እንደተቻለ አመልክቷል።

በተጨማሪ ከዚህ በፊት በተሟላ መልኩ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ አጠቃላይ 20 የሞባይል ጣቢያዎች አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን በተቀሩት አካባቢዎችም ላይ ጥገናው እንደሚቀጥል አሳውቋል።

@tikvahethiopia @ethio_telecom
#Oromia

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ይፋ ሆነ።

በኦሮሚያ ክልል የ2016 የ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ትምህርት ቢሮው የማለፊያ ነጥቡንም አሳውቋል።

የማለፊያ ነጥብ ፦
ለወንዶች እና ለሴቶች 50% እና ከዚያ በላይ፣
ለአርሶ አደር አከባቢዎች ለወንዶች 48%፣ ለሴቶች 45% እና ከዚያ በላይ፣
ለአካል ጉዳተኞች ለወንዶች 45% እና ለሴቶች 42% እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አመልክቷል።

ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ።

የ6ኛ ክፍል፡-
https://oromia6.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል፡-
https://oromia.ministry.et/#result

በተጨማሪም በቴሌግራም ቦት
@emacs_ministry_result_qmt_bot 'Start' ካሉ በኋላ ክልላቸውን ወይም ኦሮሚያ ክልል የሚለውን በመምረጥ የምዝገባ ቁጥራቸውን እና ስማቸውን በማስገባት ማየት ይችላሉ።

@TikvahEthiopia
#Oromia

" አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ምዕመናን በታጣቂዎች ተገድለዋል " - ነዋሪዎች

በአርሲ ሀገረ ስብከት፣ በአሰኮ ወረዳ በጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ " የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን " አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ካህኑ ሥጋ ወደሙን አቀብለው ምእመናንን እያሳለሙ በነበረበት ሰዓት ነው የተገደሉት።

3 ምዕመናን ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ ድርጊቱን የፈጸሙት " ኦነግ ሸኔ " ተብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

ግድያው የተፈጸመው ከነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ / ም ጀምሮ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ከዚህ ባለፈም ፥ በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያኗን ሲረዱ የነበሩ ምዕመናን ተለይተው ሀብት እና ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናን ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም ተፈጥሮ እንደነበር አንስተው " ለበላይ አካል ብናሳውቅም ጩኸታችንን የሚሰማ አጥተናል " በማለት ጥሪ ማቅረባቸውን ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Oromia : በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ባለፉት ሦስት ሳምንታት ልጆቻቸውን ቀንበር አሸክመው እና በማኅብረሰቡ ክብር ያላቸውን ዕቃዎች ይዞ ባልተለመደ ሁኔታ አደባባይ ወጥቷል።

ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች አደባባይ የወጡት ከአቅማቸው በላይ ለሆነ ችግሮች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመማጸን መሆኑን በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳታፊ የነበሩ እና ያስተባበሩ ሰዎች ተናግረዋል።

ይህ ለዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ቅርብ የሆነው እና በግብርና እንዲሁም በወተት ምርቱ ይታወቅ የነበረው አካባቢ ሰላም ርቆት ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው መግባት፣ አርሶ መሰብሰብ፣ መገበያየት እና ልጆቻቸውን ትምህር ቤት መላክ ካቃታቸው ዓመታት ማለፋቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት ላለፉት ሁለት ተከታታይ የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በአካባቢው ባሕል መሠረት ነዋሪዎች " ማለቂያ የሌለው ሰቆቃ " እንዲያበቃ ልጆቻቸው እና በሬዎቻቸው ላይ ሞፈር ጠምደው እንዲሁም የክብር የሆኑ መገልገያዎቻቸውን ይዘው በመውጣት ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል።

በዞኑ የሚገኙት ፦
- ኩዩ፣
- ደገም፣
- ሂዳቡ አቦቴ፣
- ወረ ጃርሶ፣
- ግራር ጃርሶ፣
- ደራ እና ያያ ጉለሌ ወረዳዎች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ተጠቃሽ መሆናቸው ይነገራል።

በታጣቂዎች እንቅስቃሴና መንግሥት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ሰላም ከራቃቸው ዓመታት አልፈዋል።

በዞኑ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ፣ ዘረፋ ፣ መፈናቀል እና እገታ ነዋሪውን ዕለት ከዕለት እየረበሸው የሚገኝ ጉዳይ ሆኗል።

Credit - BBC AMAHARIC

@tikvahethiopia
#Oromia : በኦሮሚያ ክልል ተፈርዶባቸው እስር ላይ የነበሩ 3,611 ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳውቋል።

247ቱ ሴቶች ናቸው።

የሞት ቅጣት ያለባቸው የህግ ታራሚዎች፤

ተደጋጋሚ ወንጀል የፈጸሙ

➡️ ሀሰተኛ ማስረጃ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠየቁ የህግ ታራሚዎችን ይቅርታው አያካትትም ተብሏል።

የይቅርታው መስፈርት ፦
° በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የታረሙ
° ከተጎጂ ቤተሰብ ጋር የታረቁ
° የገንዘብ መቀጮ የከፈሉና ይቅርታ እንዲደረግላቸው የጠየቁ ናቸው ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#Oromia : በመሬት ናዳ የሦስት እህትማማቾች ሕይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩ 3 እህትማማቾች መሞታቸውን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኑራ መሐመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ህይወት የጠፋው በአንድ አባወራ መኖሪያ ቤት አፈር ተደርምሶ ነው።

የእናት እና አባት ህይወት ሲተርፍ ሶስቱ ልጆቻቸው ሞተዋል።

አደጋው የተከሰተው ጷጉሜ 2 ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ ሲሆን አስክሬናቸውን የአካባቢው ማህበረሰብ በነጋታው በማውጣት የቀብር ስነ ስርዓታቸው እንዲፈጸም መደረጉን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ገልጾልናል።

አደጋው በተከሰተባቸው አኮ ጅሩ፣ኢሉ ኩታዬ እና ኡነይ ቀበሌዎች ከሰው ህይወት ህልፈት በተጨማሪ በሰብል የተሸፈነ 20 ሄክታር ማሳ መውደሙ ተነግሯል።

በተጨማሪም ከጅማ ሆሮ ወደ ጊዳሚ የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተቱ መዘጋቱን እና ለማስከፈት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ሃላፊው አክለዋል።

ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ተጨማሪ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ 10 ቤቶች ላይ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማንሳት ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍሩ እየተሰራ ነው ተብሏል።

Via @tikvahethmagazine
#Oromia

" በኦሮሚያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እኛ ዝግጁ ነን " - ጃል ሰኚ ነጋሳ

" በጃል መሮ (ኩምሳ ድሪባ) ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥና የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጃል ሰኚ ነጋሳ አሳውቀዋል።

' ከተመረጡ ' መገናኛ ብዙሃን ጋር በስልክ ቆይታ ያደረጉት ጃል ሰኚ ባለፈው ረቡዕ ዕለት ወጥቶ ሲዘዋወር የነበረው የማዕከላዊ ዞን ዕዝ በጃል መሮ ከሚመመራው ቡድን መነጠሉን የሚገልጸው መግለጫ " አዎ የኛ የቡድናችን ነው " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ጃል ሰኚ ፥ " (የኦነሰ) ህግና ደንብ መተዳደሪያ ደንብ የሌለው ድርጅት ነው " ብለዋል።

" ጥፋት ሲሰራ ተጠያቂነት የሌለበት ድርጅት ነው፣ ህግና ደንብ ሲኖር አንዱ ሲያጠፋ ለማስተካከል የሚያስችል ህግ ይኖራል ግን አሁን በአንድ ሰው የሚመራ መሆኑን አይተንና ተረድተን እንዲሁም ወደ ድርጅቱ ህግና ደንብ ተመልሰን እርስ በእርሳችን እናስተካክል ብለን ለኦሮሞ ህዝብ ባለን ክብር ባህልና ወጉን ጠብቀን ነው በህዝቡ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ከዚህ ባለፈ በህግ ሊታይ ይገባል፤ በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ በ2017 በተደነገገው ህግና ደንብ መመራት አለብን ብለን ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር ጋር መቀጠል አንችልም ብለን ነው መግለጫ ያወጣነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ዋና አዛዥ የምንለውን ወደፊት ኦሮሚያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ጋር ተነጋግረን ነው የምንመርጠው ፤ ስለዚህ ከዚህ በኃላ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አይወክለንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ጃል ሰኚ በኦሮሚያን ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

" በሰላማዊ መንገድ ስንል በድርጅቱ ፕሮግራም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የቀጠለውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ይታትራል። ስለዚህ መንግሥት ከሰላማዊ መንገድ ከእኛ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ከሆነ እኛም ለመነጋገር ዝግጁ ነን ፤ እንዴት ነው የምንነጋገረው ? የት ነው ? ከማን ጋር ? የሚለውን የውይይቱ ጊዜ ሲደርስ ይገለጻል " ብለዋል።

አሁን ላይ ከመንግሥት ጋር ድርድር እየተደረገ እንደሆነ ተጠይቀው " አሁን ከመንግሥት ጋር የጀመርነው ግንኙነት የለም " ሲሉ መልሰዋል። #ቪኦኤአፋንኦሮሞ

@tikvahethiopia