TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የ " SKYTRAX " ውድድር ላይ በ5 ዘርፎች ሽልማት ተቀዳጀ።

አየር መንገዱ አሸናፊ የሆነባቸው ዘርፎች ፦

🇪🇹 " Best Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 6ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Economy Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Onboard Catering in Africa 2023 " ለተከታታይ 2ኛ ግዜ

🇪🇹 " Cleanest Airline in Africa 2023 " ዘርፎች ናቸው።

አየር መንገዱ ሽልማቶቹን በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው " Paris Air Show " መርሐ ግብር ላይ ተቀብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#Axum #EthiopianAirlines

የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል።

ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም።

የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው።

በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ ስለሌለ ስራ መስራት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

በንግድ ዘርፍ ላይ ያሉ ወገኖች ብዙ ደክመው የሚያዘጋጇቸውን ቁሳቁሶች እና ባህላዊ አልባሳት የሚገዛቸው እንዳጡ አመልክተዋል።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዑክ ከኣክሱም ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር። በዚህም ወቅት የአክሱም ኤርፖርት ጥገና ዋነኛው አደጀንዳ እንደነበር ታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መ/ቤት የክልሎች የጥገና ሂደት አስተባባሪ አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ አየር መንገዱ ለኤርፖርቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች መገብየት እንደጀመረ አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ ፤ " ምን አለ ? ምን ቀረ ? የሚለውን ለይተን ኤርፖርቱን ለመጠገን የሚያስፈልጉን መሳሪያዎች በመግዛት ላይ ነን። በግዢ ሂደት ላይ ያሉ አሉ። " ብለዋል።

ጥገናው ለህዳር ጽዮን በዓል ይደርሳል ?

ጥገናው ለህዳር ጽዮን ማርያም በዓል አይደርስም ተብሏል።

በየአመቱ ኣክሱም ከተማ የሚከበረው የህዳር 21 ጽዮን በዓል በተለይም ከጦርነት በፊት እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎች ከሀገር እና ከውጭ ይገኙበት እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ያለው የሰላም ሁኔታም እጅግ በርካታ ሰዎች ወደ ከተማው በብዛት እንዲገቡ እድል የሚፈጥር ነው።

ነገር ግን እስከ በዓሉ ድረስ ያሉት ውስን ቀናት ስለሆነ የኣክሱም ኤርፖርት ተጠግኖ የመጠናቀቅ እድል የለውም ተብሏል።

አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ " የህዳር ጽዮን በዓልን ለማድመቅ የሽረ እንደስላሰ ኤርፖት አስፈላጊ በሆነ መሳሪያዎች እንዲሁም የቦይንድ አውሮፕላን የሚያርፉባቸው ስፍራዎች ለማስተካከል፣ ለማጠናከር እና ለማስፋፋት ባለሞያዎች ተሰማርተዋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ " ኢቲ106 " የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " ችግር እንዳጋጠመው ይታወቃል።

ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

- የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።

- ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።

- ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።

- ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።

- ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።

Video Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" የአየር መንገዳችንን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት ጀምሮ የአየር መንገዱን ዩኒፎርም የለበሰ ሰራተኛን የራሱን ሻንጣ በማስተካከል ላይ ሳለ የሚያሳይ ምስል ከተሳሳተ መረጃ ጋር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመዘዋወር ላይ እንዳለ ገለጸ።

ይህን ተከትሎ ፦
* በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ባልደረባ (Ethiopian Aircraft Technician) መሆኑን

* የአየር መንገዱ ዓርማ የታተመበት ሻንጣም የሰራተኛው መሆኑን፤

* በምስሉ ላይ የሚታየው ቦታ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ሰራተኞች የግል ንብረቶቻቸውን እና ለስራ የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች የሚያስተካክሉበት አካባቢ መሆኑን ግልጿል።

ሌሎቹ ቦርሳዎችም በምስሉ ላይ ያልተካተቱ የሌሎች ሰራተኞች ቦርሳዎች ናቸው ብሏክ።

" ይህ ስፍራ የመንገደኞች ሻንጣ ሊገኝበት የማይችል ለሰራተኞቻችን ብቻ የተከለለ ቦታ ነው " ያለው አየር መንገዱ በተጨማሪም ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት በደህንነት የካሜራ ዕይታ ውስጥ የሚገኝ እንደሆነ አመላክቷል።

በስራ ገበታው ላይ የሚገኝ የአየር መንገዱን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖኛል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ በምስሉ ላይ የሚታየው የአየር መንገዱ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ባልደረባና የሚያስተካክለው ሻንጣም የራሱ መሆኑን አስገንዝቧል።

ደንበኞቹም ከሚዘዋወረው ምስል ጋር ተያይዞ ምንም ስጋት እንዳያድርባቸው አሳስቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች ሆነ ለንብረቶቻቸው ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሰራኞቻችንም ደረጃውን የጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት ትጉህ መሆናቸውን አመልክቷል።

በተሳሳተ መረጃ የብሔራዊ አየር መንገዱን ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች እንድትጠበቁ ሲልም መክሯል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ፤ ሰራተኞቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፦
- ኢሚግሬሽን ፣
- የጉምሩክ ፣
- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል።

" ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም " ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን ፤ ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር አስታውሰው " ድርጊቱን የፈፀሙ የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ተሰምቷል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት #AddisAbaba በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ መዚህ መሰረት ፡- - ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኤርፖርት የሚመጡ ሁሉ የመንገድ መዘጋቱን ታሳቢ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም መንገደኞች ለበረራ ወደ ኤርፖርት በሚሄዱበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳቸው እንዲጠብቁ አሳስቧል።

የሚዘጉት መንገዶች #የትኞቹ_ናቸው ? በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፦ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/88048

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል። ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን…
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምን አሉ?

" ከቅርብ ወራት በፊት ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ቅሬታ ቀርቦልን ነበር፤ ይህም ከተሳፉሪዎች ሻንጣ ተያይዞ ወደኋላ እየቀረ ነው በሚልየቀረበ ነበር።

የተነሳውም የትራንስፖርቴሽን መዘግየትና የሻንጣ ዘግይቶ መድረስ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የተፈጠረው ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ብዙ ሻንጣ ይሸከማሉ፤ ሁሉንም ማስተናገድ ባለመቻላችን በሚቀጥለው በረራ ሻንጣዎችን እንልክ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከ737 አውሮፕላን ውጪ ከፍ ያለ የመንገደኞች ማመላለሻ እንዳንጠቀም እግድ ጥሎብን ነበር። በተጨማሪም በሳምንት ከ10 በረራ ውጪ እንዳናደርግ ተደርጎ ነበር።

መጋቢት ላይ ነው ይኼ የሆነው። ይህን ተከትሎ የኤርትራ ተጓዦች ከሻንጣቸው ጋር እንዲጓዙ ለማስቻል የተሳፋሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ተጓዦች ከሻንጣዎቻቸው ጋር እንዲጓዙ አድርገናል። ከዚያ በኋላ ይህ ነው የሚባል ቅሬታ አልሰማንም ነበር።

ይህን ተከትሎ ሰኔ መጀመሪያ ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀብለናል። ይህም የነበሩ በረራዎችን ወደ 15 እንድናሳድግና የምንጠቀመው አውሮፕላን ላይ ነበረው ገደብም መነሳቱን ተገልጾልን ነበር።

ይህንን ግን ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም፤ የአውርፕላን እጥረቶች አሉብን። በዚህ ምክንያት ይኽን ደብዳቤ ከተቀበልን በኋላ በነበረው አሰራር ቀጥለናል።

አሁን ላይ የወጣው ደብዳቤ ግን ከመስከረም 30/2024 በኋላ በረራ እንዳይደረግ የሚገልጽ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦብናል፤ በዚህ በጣም አዝነናል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቅሬታዎቹ ላይ እንወያይ ተብሎ ጥያቄ አልቀረበልንም፤ የነበሩ ችግሮች ላይ ቀደም ብለን መፍትሔ ሰጥተናል።

አሁንም የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ይህን የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ግን ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

ዛሬ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 09፡00 ሰአት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ መገደዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

ይህ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎች ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አመልክቷል።

አየር መንገዱ ፥ " የመንገደኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብሎ " ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎቻችን የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን " ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ላጋጠማቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 " የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው…
#EthiopianAirlines

ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ ከነገ ጀምሮ ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር እንደሆነ ገልጿል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

" የትኬት ገንዘብ ይመለስልን " የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ ገልጿል።

በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia