TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል። ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን…
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምን አሉ?

" ከቅርብ ወራት በፊት ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ቅሬታ ቀርቦልን ነበር፤ ይህም ከተሳፉሪዎች ሻንጣ ተያይዞ ወደኋላ እየቀረ ነው በሚልየቀረበ ነበር።

የተነሳውም የትራንስፖርቴሽን መዘግየትና የሻንጣ ዘግይቶ መድረስ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የተፈጠረው ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ብዙ ሻንጣ ይሸከማሉ፤ ሁሉንም ማስተናገድ ባለመቻላችን በሚቀጥለው በረራ ሻንጣዎችን እንልክ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከ737 አውሮፕላን ውጪ ከፍ ያለ የመንገደኞች ማመላለሻ እንዳንጠቀም እግድ ጥሎብን ነበር። በተጨማሪም በሳምንት ከ10 በረራ ውጪ እንዳናደርግ ተደርጎ ነበር።

መጋቢት ላይ ነው ይኼ የሆነው። ይህን ተከትሎ የኤርትራ ተጓዦች ከሻንጣቸው ጋር እንዲጓዙ ለማስቻል የተሳፋሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ተጓዦች ከሻንጣዎቻቸው ጋር እንዲጓዙ አድርገናል። ከዚያ በኋላ ይህ ነው የሚባል ቅሬታ አልሰማንም ነበር።

ይህን ተከትሎ ሰኔ መጀመሪያ ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀብለናል። ይህም የነበሩ በረራዎችን ወደ 15 እንድናሳድግና የምንጠቀመው አውሮፕላን ላይ ነበረው ገደብም መነሳቱን ተገልጾልን ነበር።

ይህንን ግን ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም፤ የአውርፕላን እጥረቶች አሉብን። በዚህ ምክንያት ይኽን ደብዳቤ ከተቀበልን በኋላ በነበረው አሰራር ቀጥለናል።

አሁን ላይ የወጣው ደብዳቤ ግን ከመስከረም 30/2024 በኋላ በረራ እንዳይደረግ የሚገልጽ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦብናል፤ በዚህ በጣም አዝነናል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቅሬታዎቹ ላይ እንወያይ ተብሎ ጥያቄ አልቀረበልንም፤ የነበሩ ችግሮች ላይ ቀደም ብለን መፍትሔ ሰጥተናል።

አሁንም የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ይህን የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ግን ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia