TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Gambella

ከ6 አመት በላይ ጋምቤላ ክልልን ሲመሩ የቆዩት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው ተነስተው አዲስ ፕሬዚዳንት ዛሬ ተሹሟል።

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ አለሚቱ የዛሬው ሹመት እስኪሰጣቸው በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል።

በክልሉ ም/ቤት " የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በሠላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው ነው " ተብሏል።

የቀድሞው ፕሬዜዳንት አቶ ኡመድ ሌላ የፓርቲ ተልዕኮ እንደሚሰጣቸውም ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጋትሏክ ሮን (ዶ/ር) ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

° " በየጊዜዉ የደመወዝ መዘግየቱ ህይወትን ከባድ አድርጎብናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰራተኞች

° " አሁን ላይ ችግሩ ተቀርፏል ከዚህ በኋላ የደሞዝ መዘግየት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " -ምላሽ የሰጡን አመራር


" የደመወዝ መዘግየት ፈተና ሆኖብናል " ያሉ የደቡብ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ሰራተኞች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ደመወዝ በየወቅቱ ሳይከፈል አይደለም እየተከፈለን እንኳን ኑሮ ከባድ ሆኖብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በተለያዬ ምክኒያት በ25 ወይም በ26 የሚገባዉ ደሞዝ እስከሁለት ሳምንት እየዘገዬ መግባቱ ችግር እየፈጠረብን ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ የሀምሌ ወር ደሞዛችን ባለመግባቱ ቤት አከራዮቻችን ሽሽት ላይ ነን " የሚሉት ሰራተኞቹ " ኑሮን ደግሞ የምታዉቁት ነው " በማለት የሚመለከታቸዉ አካላት ለችግራቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ ስሜ አይጠቀስ ብለዉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የድርጅቱ አመራር " አሁን ላይ ከሶስቱ ክልሎች ማለትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያና ከመእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የበጀት መልቀቅና ገንዘብ የማዘዋወር እንቅስቃሴ ተጀምሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶስቱ ክልሎች በተጨማሪ የሲዳማ ክልል ገና ዉሳኔ ላይ አለመድረሱን የገለጹት ኃላፊው ከነሱም ጋር ያለው ሁኔታ ቀስ ብሎ በውይይት መፍትሄ እንደሚፈለግለትና ከዚህ በኋላ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የዚሁ ተቋም ሰራተኞች ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሰማታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray
 
መምህርቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

በትግራይ፣ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ሌሊት ጭካኔ የተሞላበት እጅግ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል።

አስቃቂ ግድያ የተፈፀመባት መምህርት ብርኽቲ ተስፋማርያም ትባላለች።

የትግራይ መምህራን ማህበር በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ በአባሉ ላይ በተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ግድያ የተሰማው ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።

የዚህ እጅግ አሰቃቂ የወንጀል ተግባር ፈፃሚዎች በአስቸኳይ ተጣርተው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጣልባቸውም ጠይቋል።

ሟች መምህርት ብርኽቲ ተስፋማርያም ከሑመራ ተፈናቅለው ከባለቤታቸውና 3 ልጆቻቸው በእንዳስላሰ ከተማ ይኖሩ እንደነበር ማህበሩ አመልክቷል።

" የሟች ባለቤት ቤት ውስጥ አለማደሩ ያጠኑና ያረጋገጡ ግፈኞች ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም መምህርትዋ ልጆችዋ ፊት አርደው ገድልዋታል " ብሏል የመምህራን ማህበሩ።

" ይህ አስነዋሪ የግፍ ተግባር የትግራይ ህዝብ መልካም እሴት የሚፃረርና የሚያጎድፍ ሰይጣናዊ ተግባር ነው " ያለው መገለጫው " የፍትህ አካላት የአሰቃቂ ተግባሩ ፈፃሚዎች በማጣራት የህግ የበላይነት እንዲያረጋግጡ እንጠይቃለን " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፣ የግድያ ተግባሩ የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ እንዳስላሰ ሽረ ፀጥታና ፓሊስ ፅህፈት ቤት ስልክ ደውሏል።

የከተማው ፓሊስ ዋና አዛዥ የሆነ ኢንስፔክተር አወጠሀኝ ፣ የወንጀል ተግባሩ የማጣራት ጉዳይ በሃላፊነት የያዙት የወንጀል ማጣራት ሃላፊ መሓሪ ኪዳነ ደውሎ የሁለቱም የእጅ ስልካቸው አይነሳም።

ይሁን እንጂ ከከተማው የፀጥታ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ በሪሁ ባገኘነው መረጃ በሟችዋ መምህርት ላይ የተፈፀመው የወንጀል ተግባር የሚያጣራ ከጸጥታ ከፖሊስና የህግ አካላት የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#Ethiopia

" በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በመንግስትም ሆነ በታጣቂዎች በኩል እውነተኛ ከልብ የመነጨ ፍላጎት የለም።

በሁለቱ ክልሎች ባለው ግጭት ምክንያት ንጹሃን እየሞቱ፣ እየተፈናቀሉ፣  እየታገቱ እና ንብረታቸው እየወደመ ነው።

መንግስትም ሆነ በጫካ ያሉ አካላት ይህንን እያወቁ ችግሮቻቸውን በንግግር ለመፍታት ግን ፍላጎት የላቸውም።

ይህም መንግስት እየመራሁት ነው፣ ጫካ ያሉ አካላት ደግሞ እየታገልኩለት ነው ለሚሉት ህዝብ ያላቸውን ምልከታ ያሳያል።

በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ማድረግ ብቻውን መፍትሄ አያመጣም።

ሰላም የሚመጣው እውነተኛ ሰላም በመሻት እና በፖለቲካ ውሳኔም ጭምር ነው።

አሁን በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየታየ ያለው ግን መናናቅ እና አንዱ አንዱን ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ነው።

ይህ ደግሞ ንጹሀን ዜጎች ባሉበት ስቃይ እንዲቀጥሉ አድርጓቸዋል። "
- ደስታ ዲንቃ (የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ)

#ShegerFMRadio

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ወራት ብቻ ለአንድ ሰው የ1 ሺህ 496 ቀን አበል / 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል የተከፈለበት ግቢ ነው። የዚሁ ተቋም ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። @tikvahethiopia
#WachamoUniversity

#በከባድ_የሙስና_ወንጀል የተጠረጠሩት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በአጠቃላይ በ6 ግለሰቦች ላይ የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።

የክስ መመስረቻውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ፦
1ኛ. የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ አጊሾ ( ዶ/ር)፣
2ኛ. የዩኒቨርሲቲው አካዳሚና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ታምራት ታገሰ ተኮራ (ዶ/ር)፣
3ኛ. ኮንትራክተር የሆነው ደሳለኝ አስረዳ፣
4ኛ. የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ሙላቱ ኤርትሮ ጡንዳዳ፣
5ኛ. የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሃንስ ረገዮ እና
6ኛ. የቀድሞ የአዋሽ ባንክ ሆሳህና ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ የነበረው መለሰ ግርማ ኤርጋኖ ናቸው።

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ምን ይላል ?

ተጠርጣሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፣ ለንግስት ኢሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል የኦክስጂን ማምረቻ ለማስገንባት መቀመጫውና ዋናው መ/ቤቱን ካናዳ ቶሮንቶ ካደረገ " ኤ. ኤ. ኤምዲ. ቴክኖሎጂ ኢንካ " ለተባለ ድርጅት የመንግስትን የግዢ መመሪያው ባልጠበቀ መንገድ በ5 አመት አፈጻጸሙ እየታየ መከፈል የሚገባውን አሰራሩን በመተላለፍ በውል ላይ የተዘረዘሩ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ባልተሰሩበት ሁኔታ ለድርጅቱ የ57 ሚሊየን 383 ሺህ 956 ብር ከ72 ሳንቲም ለታለመለት አላማ ሳይውል በመክፈል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 ከመቶ ማለትም 117 ሚሊየን 10 ሺህ 859 ብር ከ60 ሳንቲም የውል ማስከበሪያ ሳይቀርብ እና ስራውም በውል ላይ በተገለጸው ጊዜ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ ይህ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ለመንግስት ገቢ መደረግ የነበረበትን ጥቅም አሳጥተዋል።

" ደሳለኝ አስረደ የግንባታ ስራዎች ተቋራጭ " የመምህራን መኖሪያ ቤት ሁለት (2) ህንጻ ግንባታ ስራ ግንቦት 2013 ዓ/ም እና ጥር 2016 ዓ/ም ላይ በተገባው ውል መሰረት ለዚሁ ህንፃ ተቋራጭ በተጋነነ ዋጋ በመስጠት 272 ሚሊየን 170 ሺህ 210 ብር ከ60 ሳንቲም ያለአግባብ ለተጨማሪ የግንባታ ወጪ መደረጉ ፤ ክፍያ በመፈጸም በዚህ ልክ በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስና ለውለታ 26 ሚሊዮን ብር ጥቅም ማስገኘትና ማግኘት።

በዝምድና እንዲሁም በትውውቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባለቤት እህት እና ሌሎች 2 ሰራተኞች ባልሰሩት ስራ በአበል መልክ የዩኒቨርሲቲውን ገንዘብ ያለአግባብ በመመዝበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች እስካሁን ድረስ እጃቸው ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር በመንግስት ላይ 487 ሚሊየን 333 ሺህ 912 ብር ከ78 ሳንቲም ጉዳት እንዲደርስና ለሌሎች ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኙ ተደርጓል።

ዐቃቤ ሕግ 15 ቀን የክስ መመስረቻ እንዲሰጠው ፍርድ ቤትን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ዋስታና ጠይቀዋል።

ፍ/ቤት የተጠርጣሪዎችን ዋስትና በማለፍ ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Via https://telegra.ph/FBC-08-15

@tikvahethiopia
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ ዓለም የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች በአንድ ላይ ያጣማረ ለርሶ ሚገባ ዘመናዊ ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#MesiratEthiopia

🌟 ፋይናንስ ትንበያ እና በጀቲንግ ስልጠና 🚀

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም ያዘጋጀው የኦንላይን ፋይናንስ ትንበያ እና በጀቲንግ ስልጠና ላይ ይሳተፉ!

ቀን፡ ነሃሴ 10, 2016
ከቀኑ 8:00 - 11:00 ሰዓት

👉 አሁኑኑ በ https://forms.gle/ArtHvGNn2YxuDBst9 ይመዝገቡ!
--
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ሰሞኑን " ዶላር በጣም ጨምሯል " በሚል የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ የንግዱ አካላት እጅግ እያማረሯቸዉ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ብለዋል።

" አሁን ላይ ነጋዴው እቃውን በሌሎች ነጋዴዎች ሱቅና በራሱ መጋዘን ሲያስቀምጥ አይናችን እያዬ እቃዉ የለም በሚል ዋጋ ሊጨምር ሲሞክር ማየት ያማል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " እስከ 1,080 ብር የነበረዉ ዘይት 1380 ብር ሲገባ ዶላር ነው " አሉን " እሺ የቲማቲምና ሽንኩርቱስ ዋጋ መናር ከየት መጣ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

1 ኪሎ ሽንኩርት ከ40 ብር ተነስቶ 90 ብር ቲማቲም 20 ብር የነበረው 40 እና 45 መግባቱን ጤፍም በኪሎ ከ10 ብር በላይ እንደጨመረ ጠቁመዋል።

ስሚንቶ ላለፉት ወራት ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ " የለም " እየተባለ እንደሆነ ገልጸዋል።

የነዳጅ ጉዳይ ግን በፊትም አንስቶ ፈተና ነበር አሁን ብሶበት ራስ ምታት ሆኖ ቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀዋሳ ላይ የገበያውን ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የተቋቋመ ግብረሀይል መኖሩን በመስማታችን  የነዋሪዎችን ቅሬታ ይዘን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግረናል።

እሳቸውም ፥  " አሁን ላይ እቃ በሚደብቁ እና አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ግብረሀይሉ  ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው " ብለዋል

ግብረሀይሉ  በሰራዉ ስራ ሁለት ማደያዎች እና 62 የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የምግብ ግብአትና የብረታብረት አቅራቢዎች በ8ቱ ክፍለ ከተሞች  መታሸጋቸዉንና እቃዎችም ተወርሰዉ ህገወጦቹ ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አዛዡ ማህበረሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም የፖሊስን ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የአሽከርካሪዎችድምፅ

“ በአምስት ቀናት ውስጥ 7፣ ባለፉት ዓመታት ከ170 በላይ ሾፌሮች በሽፍቶች ተገድለዋል፡፡ ወደ 90 የፎቶ ማስረጃዎች አሉን ” - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

አሽከርካሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ በ " ሽፍቶች " መታገት እና መገደላቸው እንዳልቆመ፣ መንግስትም ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ለችግሩ ትኩረት እየሰጡ እንዳልሆነ ሾፌሮችና ጣና የከባድ መኪና አሽርካሪዎች ማኀበር ምሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡

ለቲክቫህ ኢትዮጵካ ቃሉን የሰጠው ማኀበሩ ፣ ሰሞኑን እንኳ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን 5 ሹፌርና ረዳት፣ አንድ ነጋዴ እንደተገደሉ፣ ሁለት ሰዎች ታፍነው እንደተወሰዱ ገልጿል፡፡

" መንገዱ የሱዳን ቦርደር (ድንበር) ነው፡፡ ሽንኩርት ኢምፖርት የሚደረግበት፣ ቡና፣ ባቄላ ኤክስፖርት፣ የሚደረግበት ዋና መንገድም ነው፡፡ ነገር ግን ሽፍታ ነው የሚፈነጭበት፡፡ በተደጋጋሚ ነው ይሄ ችግር የተከሰተው፡፡ ሰሚ አካላ የለም፡፡ በቃ አሽከርካሪውም ከመሄድ መቆጠብ አለበት " ብሏል፡፡

" በአምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 7፣ ባለፉት ዓመታት ከ170 በላይ ሾፌሮች በሽፍቶች ተገድለዋል፡፡ ወደ 90 የፎቶ ማስረጃዎች አሉን፡፡ ከዛ ውጭ በማኀበራዊ ሚዲያ ያልወጣ፤ በየቦታው እተዳፈነ የቀረ ነፍስ አለ " ነው ያለው፡፡

" ችግሩ በየአካባቢው አለ " የሚለው ማኀበሩ ፣ " በኦሮሚያ ክልልም ከመተሐራና ወለጪቲ መካከል ከፍተኛ የስጋት ቀጠና ነው፡፡ ሾፌር ይዘረፋል፤ ይገደላል፤ ማንም ሳላልተቆጣጠረው ጥቃቱ አልቆመም " ሲል ወቅሷል፡፡

" በቅርቡ ደባርቅ ላይ የተገደለ ሾፌር አለ፡፡ ሁመራ መስመር ላይም የተገደለ ሹፌር አለ፡፡ በሁመራው መስመር የተገደለው ያውም የመከላከያዎችን ግዳጅ ጭኖ እየሄደ ነው፡፡ በአንድ ቀን 5 ሾፌርና ረዳት የሚገደልበት አሰቃቂ ሁኔታ ነው ያለው " ብሏል፡፡

" ትልቁ ክፍተት ፀጥታ የማስከበር ሂደቱ መላላት ነው፡፡ አግቶ ስልክ ተደደዋውሎ ገንዘብ የሚቀበልን ሽፍታን ስልክ በጂፒኤስ ጠልፎ ተከታትሎ እርምጃ መውሰድ ይቻላል፡፡ የተወሰነ ቦታ ላይ እንዲህ ቢደረግ ማንም ይህን ድርጊት አይሞክረውም " ሲል አስገንዝቧል፡፡

" ' ቴክኖሎጂውን ታጥቀናል ' እየተባለ ቴክኖሎጂው የዜጎችን ሕይወት ካልታደገ ምን ያደርጋል ? " ሲል ጠይቋል፡፡

አሽከርካሪዎችስ ምን አሉ ?

" መንግስት ሁሌ ህግ ያስከብር፤ ጥበቃ ያድርግልን ብለን ለፍልፈናል፡፡ በቃ ጉዳያችሁ አይመለከተኝም ብሎናል ማለት ነው፡፡

አሽከርካሪዎች ያላቸው አማራጭ ራሳቸውን በራሳቸው ማስከበር ነው፡፡

ችግር ወዳለበት ቦታ ባንሄድ እኮ ግብዓት ማቅረብ ሲቆም መንግስት መንገዱን ይጠብቀው ነበር፡፡

ስለዚህ አሁን የምንወቅሰው ራሳችንን ነው፡፡ ሾፌር የጫነውን ጤፍ የሚመገብ ሽፍታ ነው ሾፌርን የሚገድለው፡፡ ስለዚህ ሾፌሩም ጤፍ መጫን አቆሞ ያንበረክከዋል፡፡

ህዝብን የሚያገለግል ሾፌር ነው የሚገደለው፡፡ ስለዚህ ህዝብም አገልግሎት ሲቋረጥበት መንገዱን ወጥቶ ይጠብቃል፡፡ በቃ! መፍትሄው ይሄው ብቻ ነው፡፡

ለአመታት በተደጋጋሚ ሹፌር እየተገደለ፣ እየታገተ ስለጉዳዩ የሚዘግብ የመንግስት ሚዲያ የለም፡፡ ጎንደር ላይ ሰሞኑን እንኳ ለአገር ትልቅ አበርክቶ ያላቸው 6 ነፍሶች ወድቀው ቀርተዋል፡፡ ግን ማንም ጉዳይ አላለውም
" ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡

ስለጉዳዩ ከዚህ ቀደም የጠየቅነው የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ችግሩ እየቀነሰ እንደሆነ ነበር የገለጸው፣ አሽከርካሪዎች ግን እንዳውም ችግሩ እየባሰ ሂዷል ባይ ናቸው፡፡

የሚመለከታው አካላት ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ከሆኑ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር እንደሚጀምር ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤ ተመልክተናል።

ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል።

ደብዳቤው ከ2017 ትምህርት ዘመን ጀምሮ ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።

በዚህም፦

- የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የ2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 27 ድረስ ይሰጣል።

(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

ምንጭ ➡️ @tikvahuniversity
#Tigray

" ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ብሎ ራሱን በራሱ በመጠየቅና በመመለስ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

በመቐለ ከተማ ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር (GSTS) ለ3 ቀናት ያዘጋጀው ትግራይ ክልል መልሶ በማቋቋም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ ጀምሯል።

በመክፈቻው መርሃ ግብር ፦

➡️ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ

➡️ ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በም/ ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደርና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ

➡️ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

በመክፈቻው አቶ ጌታቸው ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ፥ " ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ብሎ ራሱን በራሱ በመጠየቅና በመመለስ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል " ብለዋል።

" ያለውን መድረክ በመገንዘብ የመፍትሄ ሃሳብ በማስቀመጥ የበኩሉ ሃላፊነት መወጣት አለበት " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሙሁራኑ ውይይት ማንኛውም ፓለቲካዊ ልዩነት ይኑር ችላ መባል እና መታለፍ የሌለባቸውን በመያዝ እንዲጠሩ መስራት ይጠበቅበታል " ሲሉ አስገዝበዋል።

ለ3 ቀናት ይቆያል በተባለው የውይይት መድረክ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ፣ ውይይትም ይደረጋል ተብሏል።

ከመላው ኢትዮጵያ ጨምሮ ፥ ከአፍሪካ ፣ አሜሪካ ፣ አወሮፓና ልሎች የዓለም ክፍሎች የተጋበዙ የትግራይ ሙሁራን ተሳታፊ እንደሆኑ ተሰምቷል።

ፎቶ ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia 
#DireDawa

" አንዳንዴ አላህን መፍራት ያስፈልጋል። ክርስቲያም ከሆን የምናመልከውን ፈጣሪን መፍራት ያስፈልጋል።

ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

በአንድ ለሊት የውጭ ምንዛሬው ሲጨምር ባንክም ውድድር ውስጥ ገብቷል።

ግን እዚሁ ስቶር የነበረውና ከ3 ወር በፊትና ከዛ በፊት የገቡ እቃዎች በአንዴ 300 ፐርሰንት መጨመር ሃጢያት አይደል ? አላህ እራሱ ይወደዋል ወይ ?

የሃላል ነገር ነው አይደል ሰው መብላት ያለበት፤ ይሄ ድሃ ማህበረሰብ ነው ሁሌ እናተን በችግር ጊዜ የሚያግዛችሁ።

ቢያንስ ለ3 ወር ! በአዲሱ ምንዛሬ ሲገባ ያኔ እኮ ባላንስ ይደረጋል ፤ ምን ነበር የሚለውን ማየት ይቻላል።

ወደ እርምጃ ሲገባ ግን የከፋ ይሆናል።

እውነቱን ለመነጋገር ከእናተ የድሃውን ማህበረሰብ እምባውን ማበስ ይሽለናል። በግልጽ ለመነጋገር።

ለሰው ብላችሁ አይደለም፤ ለማንም ብላቹ አይደለም ለህሊናችሁ ብላችሁ ስሩ፤ ዛሬ የዘራችሁትን ነገ ልጆቻችሁ የተሻለ ነገር ያገኛሉ። "

የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር (በቅርቡ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ውይይት የተናግሩት)

#DireDawaCity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከኢትዮጵያ መንግሥት የተበረከተላቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " አልቀበልም " ብለው መልሰው ከመድረክ መውረዳቸው ይታወሳል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ ይሆናል። ምክንያቱም ስጦታ በግድ ውሰዱ ስለማይባል " ሲል ለኤፍ ኤም 97.1 ተናግሯል። አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፤ ለሙያውና…
#GemedoDedefo

ከፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እጅ የተሰጣቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " የኛ የአሰልጣኞችን ልፋት አመጥንም " ብለው ሳይቀበሉ የቀሩትና በኃላም " እዛ ቦታ ላይ ያን ማድረግ አልነበረብኝ ፤ ተሳስቻለሁ " በማለት ህዝቡን እና ፕሬዜዳንቷን በይፋ ይቅርታ የጠየቁት አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ " ታስረዋል " ከሰዓታት በኃላ ደግሞ  " ከእስር ተፈተው ወደ ቤት ገብተዋል " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩባቸው ነበር።

እሳቸው ግን " እኔ አልታሰርኩም ፤ እስር ቤትም አልነበርኩም  " ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዙሪያ ታማኝ ነው የሚባለው ጋዜጠኛ ኤቢሳ ነገሰ አሰልጣኙን በስልክ እንዳገኛቸውና " ጉዳዩም እንደሚባለው እንዳልሆነ "  ገልጿል።

እሳቸው አሰልጣኝ ገመዶም እስር ቤት እንዳልነበሩ ቃላቸውን እንደሰጡት አመልክቷል።

" እኔ አልታሰርኩም " ማለታቸውን ጋዜጠኛው አሳውቋል።

በሌላ በኩል አሰልጣኙ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ መታሰራቸው " ውሸት ሀሰተኛ ዜና " እንደሆነ እና ቤታቸው እንደሚገኙ ገልጸው ወዲያው ደግሞ አጥፍተውታል።

ጉዳዩን ከሚያውቁ ሌሎች አካላት በተገኘው መረጃ ግን አሰልጣኙ ታስረው እንደነበር ፤ ምሽት ላይ ግን መፈታታቸው ተሰምቷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሰልጣኙ " አልወስድም " ያሉት  ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ እንደሚሆን ማሰወቁ ይታወሳል። " ስጦታ በግድ ውሰዱ አይባልም " ነው ያለው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው። የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው። በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል። ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም። …
#Ethiopia

" ኢትዮጵያ ፓሪስ ላይ በአትሌቲክሱ ያስመዘገበችው ዝቅተኛ ውጤት በቀናት ውስጥ ተረስቶ አጀንዳው ተቀይሯል።

ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው ? ቀጣዩ እርምጃስ ምንድነው ? ወይስ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል ነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራባት አትሌቲክስ ታሟል። ስለሆነም ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የአትሌቲክስ ሰዎች ሁሉ ቁጭ ብለው መክረው ለውጥ ያምጡ።  

ዳግም ህዝብ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ዘላቂ መፍትሄ በአስቸኳይ መፈለግ አለበት።

ለነገ ዛሬ ካልተሰራ ተመሳሳይ ነገር ይጠብቀናል። " @nousethiopia

@tikvahethiopia