TIKVAH-ETHIOPIA
#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ወራት ብቻ ለአንድ ሰው የ1 ሺህ 496 ቀን አበል / 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል የተከፈለበት ግቢ ነው። የዚሁ ተቋም ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። @tikvahethiopia
#WachamoUniversity

#በከባድ_የሙስና_ወንጀል የተጠረጠሩት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በአጠቃላይ በ6 ግለሰቦች ላይ የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።

የክስ መመስረቻውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ፦
1ኛ. የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ አጊሾ ( ዶ/ር)፣
2ኛ. የዩኒቨርሲቲው አካዳሚና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ታምራት ታገሰ ተኮራ (ዶ/ር)፣
3ኛ. ኮንትራክተር የሆነው ደሳለኝ አስረዳ፣
4ኛ. የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ሙላቱ ኤርትሮ ጡንዳዳ፣
5ኛ. የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሃንስ ረገዮ እና
6ኛ. የቀድሞ የአዋሽ ባንክ ሆሳህና ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ የነበረው መለሰ ግርማ ኤርጋኖ ናቸው።

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ምን ይላል ?

ተጠርጣሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፣ ለንግስት ኢሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል የኦክስጂን ማምረቻ ለማስገንባት መቀመጫውና ዋናው መ/ቤቱን ካናዳ ቶሮንቶ ካደረገ " ኤ. ኤ. ኤምዲ. ቴክኖሎጂ ኢንካ " ለተባለ ድርጅት የመንግስትን የግዢ መመሪያው ባልጠበቀ መንገድ በ5 አመት አፈጻጸሙ እየታየ መከፈል የሚገባውን አሰራሩን በመተላለፍ በውል ላይ የተዘረዘሩ ስራዎች ሙሉ በሙሉ ባልተሰሩበት ሁኔታ ለድርጅቱ የ57 ሚሊየን 383 ሺህ 956 ብር ከ72 ሳንቲም ለታለመለት አላማ ሳይውል በመክፈል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 ከመቶ ማለትም 117 ሚሊየን 10 ሺህ 859 ብር ከ60 ሳንቲም የውል ማስከበሪያ ሳይቀርብ እና ስራውም በውል ላይ በተገለጸው ጊዜ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ ይህ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ለመንግስት ገቢ መደረግ የነበረበትን ጥቅም አሳጥተዋል።

" ደሳለኝ አስረደ የግንባታ ስራዎች ተቋራጭ " የመምህራን መኖሪያ ቤት ሁለት (2) ህንጻ ግንባታ ስራ ግንቦት 2013 ዓ/ም እና ጥር 2016 ዓ/ም ላይ በተገባው ውል መሰረት ለዚሁ ህንፃ ተቋራጭ በተጋነነ ዋጋ በመስጠት 272 ሚሊየን 170 ሺህ 210 ብር ከ60 ሳንቲም ያለአግባብ ለተጨማሪ የግንባታ ወጪ መደረጉ ፤ ክፍያ በመፈጸም በዚህ ልክ በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስና ለውለታ 26 ሚሊዮን ብር ጥቅም ማስገኘትና ማግኘት።

በዝምድና እንዲሁም በትውውቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባለቤት እህት እና ሌሎች 2 ሰራተኞች ባልሰሩት ስራ በአበል መልክ የዩኒቨርሲቲውን ገንዘብ ያለአግባብ በመመዝበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች እስካሁን ድረስ እጃቸው ለጊዜው ካልተያዙ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር በመንግስት ላይ 487 ሚሊየን 333 ሺህ 912 ብር ከ78 ሳንቲም ጉዳት እንዲደርስና ለሌሎች ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኙ ተደርጓል።

ዐቃቤ ሕግ 15 ቀን የክስ መመስረቻ እንዲሰጠው ፍርድ ቤትን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ዋስታና ጠይቀዋል።

ፍ/ቤት የተጠርጣሪዎችን ዋስትና በማለፍ ለዐቃቤ ሕግ የ15 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Via https://telegra.ph/FBC-08-15

@tikvahethiopia