🔈 #የሰራተኞችድምጽ

° " በየጊዜዉ የደመወዝ መዘግየቱ ህይወትን ከባድ አድርጎብናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰራተኞች

° " አሁን ላይ ችግሩ ተቀርፏል ከዚህ በኋላ የደሞዝ መዘግየት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " -ምላሽ የሰጡን አመራር


" የደመወዝ መዘግየት ፈተና ሆኖብናል " ያሉ የደቡብ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ሰራተኞች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ደመወዝ በየወቅቱ ሳይከፈል አይደለም እየተከፈለን እንኳን ኑሮ ከባድ ሆኖብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በተለያዬ ምክኒያት በ25 ወይም በ26 የሚገባዉ ደሞዝ እስከሁለት ሳምንት እየዘገዬ መግባቱ ችግር እየፈጠረብን ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ የሀምሌ ወር ደሞዛችን ባለመግባቱ ቤት አከራዮቻችን ሽሽት ላይ ነን " የሚሉት ሰራተኞቹ " ኑሮን ደግሞ የምታዉቁት ነው " በማለት የሚመለከታቸዉ አካላት ለችግራቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ ስሜ አይጠቀስ ብለዉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የድርጅቱ አመራር " አሁን ላይ ከሶስቱ ክልሎች ማለትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያና ከመእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የበጀት መልቀቅና ገንዘብ የማዘዋወር እንቅስቃሴ ተጀምሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶስቱ ክልሎች በተጨማሪ የሲዳማ ክልል ገና ዉሳኔ ላይ አለመድረሱን የገለጹት ኃላፊው ከነሱም ጋር ያለው ሁኔታ ቀስ ብሎ በውይይት መፍትሄ እንደሚፈለግለትና ከዚህ በኋላ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የዚሁ ተቋም ሰራተኞች ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሰማታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM