TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም " - ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ በከንቲባነት ዘመኔ ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም አሉ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሬፌሰር ፀጋዬ ቱኬ። የቀድሞ ከንቲባ ይህ ያሉት ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ነው። በቅርቡ በተደረገ ግምገማ በ" ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው የተነሱት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በእሳቸው…
#Update #Sidama

የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ፤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።

የክልሉ ፖሊስ ፤ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በህግ ሲፈለጉ ነበር ብሏል።

ዛሬ 13/2/2016 ዓ.ም ረፋድ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን ገልጾ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሀዋሳ ከተማ የእስረኛ ማቆያ ይገኛሉ ብሏል።

የቀድሞው ከንቲባ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ የከፍተኛ የአመራር ግምገማ ረግጠው በመውጣት ተሸሽገው ነበር ያለው የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል ያልተቋረጠ ክትትል ሲደረግ ነበር ሲል አሳውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ያወጣው መረጃ የቀድሞውን ከንቲባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወደ ሀገር ሲገቡ ወይስ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ የሚለውን በግልፅ አያስረዳም።

ከወራት በፊት በሲዳማ ክልል በተደረገ ግምገማ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በ " ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው እንደተነሱ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት መግለፁ አይዘነጋም።

ፅ/ቤቱ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ግምገማውን ረግጠው እንደወጡ ከዛ በኃላም ያሉበትን አድራሻ እንደማያውቅ ገልጾ ነበር።

በኃላም የቀድሞው ከንቲባ የት ሀገር እንደሚገኙ በግልፅ ሳይናገሩ በህክምና ክትትል ላይ እንዳሉና በቅርቡ በህዝብ መኃል ተገኝተው እውነታውን እንደሚያጋልጡ ተናግረው ነበር።

በተጨማሪ ፦

- በከንቲባነት ዘመናቸው ህዝብን የሚጎዳ ቅንጣት ታክል ጥፋት እንዳልሰሩ፤

- እሳቸውን ማሳደዱ የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ ካልሆነ በስተቀር ፣ በክልሉ ይፋ ያልወጡ በህዝብ እንባና ላብ የከበሩ እንኳን ህግ ፈጣሪም ይቅር የማይለዉ  ወንጀል/ጥፋት የፈጸሙ የህዝብን ሀብት በሽፋን የሚዘርፉ አካላት እንዳሉ። እነዚህ አካላት የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በቅርብ  ይፋ እንደሚወጡ፤

- በክልሉ ያለው ነባራዊ ሁኔ ቡድንተኝነትና በሴራ ፓለቲካ የተተበተበ በመሆኑ እሳቸውም ሆኑ በተሻለ አፈጻጸም ላይ የነበሩ አመራሮች የፓርቲን መርህ ባልተከተለ መልኩ ከኃላፈነት መነሳታቸውን፤

- እድል ያገኙ ቀን እዉነቱን በማውጣት በመረጃና በማስረጃ እንደሚታገሉ ገልጸው ነበር።

በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ፖሊስ እንዳሳወቀው ግን የቀድሞ የሲዳማ መዲና ሀዋሳ ከንቲባ በህግ ሲፈለጉ ከቆዩ በኃላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa #Motor

በሀዋሳ ከተማ ከሞተር ሳይክል የታርጋ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ክፍል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአንፃሩ የሞተር ባለቤቶች ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ ታርጋ የላቹም ብሎ ያሳድደናል " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

አንዳንዶች ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ክልል  ታርጋ ወደ ሲዳማ ታርጋ መቀየር አለበት በሚል የመያዝና የማንገላታት ነገርም አለ ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ፤ ህብረተሰቡ ህጋዊ  ታርጋ በማዉጣት ህጋዊ ይሆን ዘንድ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር ተስፋዬ አክለውም፤ " የደቡብ ታርጋ አየተያዘ ነዉ " የሚባለዉ #ስህተት መሆኑን በመግለጽ ማንም በነጻነት ማሽከርከር እንደሚችል ገልጸዋል።

" በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሞተሮች ካሉ ስህተት ነው፤ ይለቀቃሉ። የደቡብ ክልል ታርጋ እስካልሸጠ እስካለወጠ ድረስ ችግር የለውም " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ከአዲስ ታርጋ ጋር በተያያዘ በጹሑፍ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ አባላት ታርጋ የላቹም ብለው ያሳድዱናል። እኔ በግሌ 2% ግብር ከከፈልኩ ወራቶች ተቆጥረዋል ነገር ግን ታርጋ ማግኘት አልቻልኩም የሚመለከተው አካል መፍትኤ ይስጠን፤ ትራፊክ ፓሊስ አባላት እያንገላቱን ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ይህንን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳንቾ ችግሩ መኖሩን በማመን ችግሩ ከሀገራዊ የዶላር ችግር ጋር ተያይዞ የመጣ (ለታርጋ ማሳተሚያ) መሆኑን አንስተዋል።

" አሁን ላይ ህትመቱ በማለቁ በሚቀጥለዉ ሳምንት ይሰጣል " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ታርጋ ያልደረሳቸዉ አሸከርካሪዎች ሪሲት በማሳየት እንዲንቀሳቀሱ የተያዙትም እንዲለቀቁ ከከተማዉ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ ምላሽ  ሰጥተዉናል።

መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Sidama

" ... እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻችሁን ከማስተማር ተቆጠቡ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በአብዛኛዉ ከደረጃ በታች መሆናቸዉ ተከትሎ 17 ኮሌጆች #መዘጋታቸዉ ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ባካሄደዉ የኦዲት ሪፖርትና የዉይይት መድረክ በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በህገወጥ ስራ መሰማራታቸዉ ገልጿል።

የቢሮዉ ሃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በዚህዉ ወቅት እንደገለጹት ኮሌጆቹ ገበያመር የሆነ አካሄዳቸውና በህግ የመመራት ስታንዳርዳቸዉ በስራ ላይ እንዲቆዩ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

በእለቱ የኦዲት ግኝቱን ተመስርቶ 17 ኮሌጆች ስራ እንዲያቆሙ ሲወሰን ኮሌጆቹ በመላዉ ሲዳማ የጀመሯቸዉን የማስተማር ስራዎች አቁመዉ ፈቃዳቸዉን እንዲመልሱ ተነግሯቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ያላግባብ #ሳያስተምሩ_አስመርቀዉ ስራ ፈላጊና የሀገር ሸክም በማድረጋቸዉ በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ የተገለጸ ሲሆን ቢሮዉ እጁ ላይ ያለዉን መረጃ ባፋጣኝ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ እንደሚልክ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ማህበረሰቡ እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻቸዉን ከማስተማር እንዲቆጠቡ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመላዉ ሲዳማ ክልል ከገበያዉ በላይ የተማረ ሰዉ በመኖሩ የአካዉንቲንግ ማርኬቲንግና የሰዉ ሀይል አስተዳደር ትምህርቶችን መማርም ሆነ ማስተማር የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

በህገወጥነት የተዘጉ ኮሌጆች ዝርዝር ፦

1. አትላስ ኮሌጅ - ሀዋሳ
2. ፊሪላድ ኮሌጅ - ሀዋሳ
3. ራድካል ኮሌጅ - ሀዋሳ
4. ስፓርታክ አፍሪካ ኮሌጅ - አለታ ጩኮ
5. ዩኒክ ስታር ኮሌጅ - አለታ ጩኮ
6. ዛክቦን ኮሌጅ - በንሳ ዳዬ
7. ሪፍት ቫሊ - ሀዋሳ
8. ዩንክ ስታር ኮሌጅ - ዳዬ
9. ኦሞ ቨሊ ኮሌጅ - ሞሮቾ
10. አፍን ፎር አፍሪካ - አለታ ወንዶ
11. ዩኤስ ኮሌጅ - ዳዬ
12. ዩኒክ ስታር ኮሌጅ - አርቤጎና
13. ፋርማ ኮሌጅ - ለኩ
14. ሮሜክ ኮሌጅ - ሀዋሳ
15. ካይዘን ዲዲ - ሁላ
16, ዩኒክ ስታር - ለኩ
17. ሄሊከን ኮሌጅ - ጭሬ

ኮሌጆቹ ለመዘጋታቸው የቀረበዉ ምክኒያት ምንድን ነዉ ?

* የኮሌጆቹ መምህራን የሲኦሲ ሰርተፊኬት አለመኖር
* የተማሪ ቁጥር ከስታንዳርድ በላይ መሆን
* ቋሚ መመህራን አለመኖር
* በአንድ ግቢ ድግሪና ቲቪቲ ማስተማር
* የመማር ማስተማር ቁሳቁስ አለመሟላት
* በቂ የሆነ የአስተዳደር መዋቅር አለመኖር
* ከተፈቀደላቸዉ ፕሮግራም ዉጭ ማስተማር የሚሉት ጉዳዮች ቀርበዋል።

መረጃውን የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa

" የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ባለማግኘታችን ከሀገር ወጭ ያገኘነው የስራ እድል ሊያልፍብን ነው " - ወጣቶች

" ያለው አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ ችግሩን ባፋጣኝ መቅረፍ አልተቻለም " -  የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ

በሀዋሳ ከተማ እና በአካባቢዉ ያሉ ስራ አጥ ወጣቶች ያገኙትን የውጭ ሀገር የስራ እድል ተከትሎ ማሟላት ካለባቸዉ መስፈርት ውስጥ አንዱ የሆነዉ የግብር መለያ ወይም ቲን ነምበር ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ቢያቀኑም ላለፉት ሰላሳ ቀናት ሊሳካላቸዉ አልቻለም።

እነዚህ ከሀዋሳና አካባቢዋ የተሰባሰቡ ወጣቶች ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተለያዬ መልኩ ያገኙትን የስራ እድል ለመጠቀም የጀመሩትን እንቅስቃሴ  የቲን ነምበር ጉዳይ እንቅፋት እንደሆነባቸዉና አሁን ላይ ጭራሹኑ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ መውጣቱን ይናገራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ቢሮዉ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ ካወጣ በኋላ በጎን አገልግሎት ሲሰጥ ይገኛል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ ምክኒያትም በከፍተኛ  ሁኔታ እየተጉላሉ መሆኑን ያነሳሉ።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ በሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ የግብር አወሳሰንና የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊዋ ወይዘሮ ሙላት ዮሴፍ እንደገለፁት ፤ በከተማዉ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ስምንት የቲን ነምበር ማሽኖች ስራ ማቆማቸዉን በማንሳት አሁን ላይ በአንድ ማሽን ብቻ እየታገሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም " በከተማዉ አገልግሎት እየሰጠ ያለዉ አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ መፍትሄ መስጠት አልቻልንም " ያሉት ሀላፊዋ አገልግሎቱ እስከ ጥር ሰላሳ የታገደው ጫና በመፈጠሩና ወሩ የግብር መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ ወጣቶችን ማስተናገድ ባለመቻሉ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የክልሉ መንግስት እንደሀገር የተጀመረዉን የውጭ ሀገር ህጋዊ  የስራ ስምሪትና ኮታ ተከትሎ የተቀመጠውን የትምህርት ደረጃ እድሜና ፍላጎት የመሳሰሉ መስፈርቶች ያሟሉ ከ900 በላይ ወጣቶች ወደ ሳውዲና መሰል የአረብ ሀገራት መላኩን በመግለጽ  አሁን ላይ የቲን ነምበር ፍላጎት ያላቸዉ ወጣቶች እድሉን በመንግስት በኩል ያገኙ  ሳይሆን ይልቁንም በራሳቸዉ መንገድ ያገኙ መሆናቸዉን የክልሉ የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጺዮን አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ እንደሚሉት ወደ #ካናዳ እና ሌሎችም ሀገራት በራሳቸዉ ጥረት ለመሄድ ቲን ነምበር የሚያስፈልጋቸው ወጣቶችን ለመርዳት ጥረት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ መምሪያዉ ያለዉ አንድ ብቻ የቲን ነምበር ማሽን ግን ችግር መፍጠሩን አመልክተዋል።

ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ለመፍጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ እስከ ጥር 30 አገልግሎት እንደማይኖር የሚገልጸዉን ማስታወቂያ የሰሙ ወጣቶች ጭንቀት ዉስጥ ሲሆኑ የሚመለከተዉ አካል አስፈላጊዉን መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጥያቄ ብናቀርብም አስተያዬት ከመስጠት ተቆጥቧል።

መረጃውን የላከው የሀዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Sidama

" #አፊኒ " የተሰኘውና በሲዳማ ባህላዊ የእርቅ ስነስርአትና የግጭት አፈታት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተሰራው ፊልም ትላንት በሀዋሳ ከተማ ተመርቋል።

ፊልሙ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የፊልሙ ባለቤትና ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ኃላፊነቱን ወስዶ ሲሰራዉ የነበረው የሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ነው ተብሏል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ፤ " አፊኒ ፊልም የሲዳማን ባህል ወግና ትውፊት የሚያንጸባርቅ ተንቀሳቃሽ ሙዚየም ነው " ብለውታል።

" አፊኒ " ፊልም የሲዳማን ባህል የማስተዋወቅ ዓላማ ያለዉና በኢንተርናሽናል ስታንዳርድ የተሰራ መሆኑ ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት " አፊኒ " ፊልም ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ መሰራቱን መግለጹን ተከትሎ ከፊልሙ አሰሪ ኮሚቴ " ትክክል አይደለም !! " የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር።

ይሁንና ትክክለኛ የፊልሙ ወጭ ስንት እንደሆነና ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተጨማሪ ፊልሙን በገንዘብ ስላገዙ አካላት መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ሊሳካ አልቻለም።

ሌላው ከምርቃት ስርዓቱ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወጥቷል እየተባለ ስለሚነገረው በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ መጠን ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

በቀጣይ ከሚመለከተው አካል መረጃ የምናገኝ ከሆነ እናቀርባለን።

መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል፣ በሥራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ።

አንድ ሹፌርም ህይወቱ አልፏል።

ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ የደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ሾፌርን ጨምሮ በስራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ ህይወት ቀጥፏል።

አደጋው በወረዳው ' ኤሬርቴ ወንዝ ' አጠገብ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ተነግሯል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ የሰጡት የሲዳማ ክልል ትራፊክና አደጋ መከላከል ተጠሪ ኮማንደር ከበደ ኮኔራ አደጋው ጠዋት 3:00 ሰዓት አካባቢ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር መድረሱን አረጋግጠዋል።

በወቅቱ የአካባቢውን የተሽከርካሪ ፍሰት ሲቆጣጠር የነበረው ትራፊክ ፖሊስ አንድ የሚኒባስ አሽከርካሪን አስወርዶ በመነጋገር ላይ እያለ አቅጣጫውን የሳተ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከዳራቸዉ ከነበረው ሲኖ ጋር እንዳጣበቃቸዉና ሁለቱም ወዲያዉ ህይወታቸዉ እንዳለፈ ገልጸዋል።

" በአካባቢዉ የነበረዉ ብቸኛ የትራፊክ ፖሊስ እና መረጃ አቀባያችን በመሰዋቱ አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልቻልንም " ያሉት ኮማንደር ወደቦታዉ ያቀኑት ባልደረቦቻቸው የሚያቀብሉት መረጃ በኋላ ላይ ለህብረተሰቡ  እንደሚያጋሩን ተናግረዋል።

በአደጋዉ የሁለቱ ዜጎች ህይወት ከመጥፋቱ ባለፈ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa

° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች

° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ


ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ከሰሞኑ በሰልፍና በጎን በሚገቡ ህገወጥ ቀጅዎች ስንማረር መሰንበታችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በየቀኑ በቴሌግራም የሚለቀቀዉ የነዳጅ ፕሮግራም ተቋርጦ በከተማው ውስጥ ያሉ ማደያዎች ሁሉ ዝግ ሆኑብን "  የሚሉት አሽከርካሪዎች በዚህም በእጅጉ ተቸግረናል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎትን አነጋግሯል።

እሳቸውም ፤ " እንደከተማ አንድ ማደያ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ ነው " በማለት በከተማዉ ምንም አይነት ነዳጅ አለመኖሩን ገልጸውልናል።

የቴሌግራሙ ፕሮግራም አለመውጣቱም ከዚህ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ ችግሩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ስብሰባ መቀመጣቸውን ገልጸው "  ማህበረሰቡ እና አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው እንዲታገሱ " ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama #Hawassa ° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን…
#Sidama

በሀዋሳ ከተማ 1 ሊትር ቤንዚን በድብቅ እስከ 180 ብር እየተሸጠ ነው።

በከተማይቱ ያሉ ሁሉም ማደያዎች ውስጥ ቤንዚን የለም ተብሏል።

ይህን ተከትሎ 1 ሊትር ቤንንዚን ከ150 ብር እስከ 180 ብር በድብቅ እየተሸጠ ይገኛል።

ቀድሞውም ቢሆን በከተማዋ በድብቅ ነዳጅ ይሸጥ ነበር። ዋጋውም 100 ብር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በመላ ከተማይቱ ነዳጅ መጥፋቱን ተከትሎ እስከ 180 ብር ደርሷል።

የከተማ ውስጥ ታክሲዎች በተለይ በከተሞች ዳርቻ ዋጋቸዉን እጥፍ ከማድረግ በዘለለ ኮንትራት ካልሆነ አንጭንም እያሉ መሆኑን ሰምተናል።

አንድ የሀዋሳ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል  " ዛሬ በሀዋሳ 1 ሊትር ቤንዚል ከ170 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። በየትኛውም ነዳጅ ማደያ ዛሬ ቤንዚል የለም " ብሏል።

" አንዳንድ ታክሲዎች ዝም ብለን ከምንቀመጥ ብለው 2 ሊትር ከ320 ብር ጀምሮ እየገዙ ፤ የ5 ብር መንገዶችን በ10 ብር እየጫኑ ነው ፤ ከዛ ውጭ ሌሎች በተለይ ባጃጆች በየጥሻው ቆመው ነው ያሉት " ብለዋል።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮም ሆነ የነዳጅ ጉዳይ የሚመለከተዉ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ትናንት ስብሰባ ላይ እንደነበሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

ስብሰባውን ተከትሎ እስካሁን ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም።

በትላንትናው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት  የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎት " ጉዳዩ አገር አቀፍ ችግር ነው " ብለዋል።

በማደያዎች ነዳጅ አለመኖሩን እና መንገድ የጀመረ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ እንደሌለ በመግለጽም ማህበረሰቡ እንዲታገስ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#Sidama

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፣ ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ በሚባለው አካባቢ ትላንት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ በ6 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

#SidamaRegionCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሲዳማ ክልል በወንሾ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ወገኖቻችን ቁጥር 9 ደርሷል። 6 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋለም ሆስፒታል ይገኛሉ። በሌላ በኩል ፤ በዛው ሲዳማ ክልል በቡራ ወረዳ በድንገተኛ ውኃ ሙላት የሁለት ሕጻናት ሕይወት አልፏል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል፣ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የውሀ ሙላት አደጋ የሞቱ ዜጎች 11 መሆኑን የሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበራ ዊላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ ዘጠኙ የሁለት አባወራ ቤተሰቦች ሲሆኑ አንዱ 5 አንዱ ደግሞ 3 ቤተሰቦቻቸዉን ማጣታቸውን ገልጸዋል።

አንድ ግለሰብ ከገበያ ሲመለስ ከተራራ የወረደ ናዳ ላዩ ላይ በማረፉ ለህልፈት እንደዳረገው ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ በቡራ ወረዳ ወንዝ ሞልቶ ከአቅጣጫው ውጭ በመፍሰስ በአካባቢዉ ያለ ቤት ውስጥ በመግባት 2 ልጆችን ህይወት መቅጠፉን ተናግረዋል።


ከአካባቢው ተራራማነትና ያለማቋረጥ ከዘነበው ዝናብ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ተጨማሪ አደጋዎች ይከሰታሉ ተብሎ ስጋት አለ።

ይህንንም ተከትሎ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ ፣ የጤና ቢሮና ሌሎች ተቋማት የተወጣጣ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደስራ ተገብቷል ብለዋል።

" ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው " ተብለው ከተለዩ ስድስት ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎችን የማውጣት ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

ከቀያቸዉ ከተነሱትን ራቅ ያለ ቦታ ዘመድ ያለው ወደዛ ሲሄድ ሌሎች በት/ቤቶች ፣ በቤተእምነቶችና መሰል ቦታዎች እየተጠለሉ መሆኑን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaHW

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ  ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ የሚያከናውኑት ከሐምሌ 25 ቀን 2016 እስከ ነሀሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን የከተማው ትምህርት መምሪያ አሳውቋል።

መምሪያው ፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ት/ቤቱ በበጋ ወቅት ከሚያስከፍለው የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ከ20% መብለጥ አይችልም ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪ ፥ ትምህርት ቤቶች በምዝገባ ወቅት ደስታ ወረቀትንና መሰል ቁሳቁሶችን በየትኛውም የእርከን ደረጃ መጠየቅ እንደማይችሉ አሳውቋል።

ትምህርት መምሪያው በ2017 ዓ.ም መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ ት/ቤቶች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ውጪ (ከላይ በዝርዝር ከተገለጹት ውጭ) ክፍያ ጨምሮ የተገኘ ት/ቤት እርምጃ ይወሰድበታል ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Sidama

" በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " - አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ

በሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ግምገማ መደረጉን ተከትሎ በርካታ የፖሊስ አዛዥች ከስልጣን ሲነሱ በጥቂቶች  ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተሰምቷል።

ከሰሞኑ በክልሉ ሲካሄድ የሰነበተውን የግምገማና የውይይት መድረክ አሰመልክተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ " በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " ብለዋል።

" በዚህ መሰረት በተደረገ ግምገማ በክልሉ በተለያዩ ዞን ወረዳና ከተማ አስተዳደር ውስጥ
ባሉ መዋቅር ይሰሩ ከነበሩ አመራሮች ውስጥ ሰባት የፖሊስ አዛዦችና ሙሉ የአንድ ክፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲጀመር ታዟል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ አመራሮች መካከል ፦
- የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ፣
- የሆኮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
- የጨቤ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ይገኙበታል።

የዳዬ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከኃላፊነታቸው ታግደው ከመልካም አስተዳደር ችግሮችና ከህገወጥ ንግድ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች እንዲጣራ ታዟል።

በተጨማሪም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ በዞኑ ህገ-ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመምጣቱና መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ ችለዋል።

በወረዳ ደረጃ ደግሞ የሁላ ወረዳ፣ የአለታ ጩኮ ወረዳ፣ የቡርሳ ወረዳና የጠጢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ያሉ ጠቅላላ ማኔጅመንቱ ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው ተነግሯል።

በመድረኩ በርካታ ችግሮች የተነሱ ሲሆን ለአብነትም ኪራይ ሰብሳቢነትና ባለጉዳይን ማማረር ጎልተዉ የተነሱ ክፍተቶች ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia