TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION🔈

" ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

እስካሁንም ድረስ ያልተገኙ በርካታ የቤተሰብ አካላት በመኖራቸዉ የሟቾችን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጸው ሊጨምር ይችላል።

ከጉዳቱ የተረፉ ሰዎችን ወደ አንድ አካባቢ አድርጎ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከአራቱም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ግን ከተፈቀደው የንግድ ባንክ አካውንት እና የአጭር መልዕክት ድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር ውጭ " ድጋፍ እናሰባስባለን " በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢ/ር ዳግማዊ አየለ ፥ " ከተፈቀደዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥሮች ወጭ ጥቅም ላይ የዋሉ የንግድ ባንክ አካውንቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እየተዘዋወሩ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ የምትሳተፉ አካላት ከድርጊታችሁ  እንድትቆጠቡ "  ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ፥ " አሁን ላይ ህጋዊ ሆኖ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000511561276 እንዲሁም በአጭር መልእክት ድጋፍ ለማድረግ ደግሞ 8991 ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከዚህ ዉጭ በሚዘዋወሩ አካውንቶችን እንዳይጠቀም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከመላው ኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከጉዳት የተረፉ ወገኖችን ስነልቦና የማከሙ ስራ የቀጣይ ዋና ተግባር እንደሚሆንና ይህም የሁሉም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል። (ሙሉ መግላጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
የዛሬው የምንዛሬ ዋጋ ስንት ነው ?

💵 US Dollar
#CASH
Buying ➡️ 74.7364
Selling ➡️ 76.2311

#TRANSACTION
Buying ➡️ 74.7364
Selling ➡️ 76.2311

💷 Pound Sterling
#CASH
Buying ➡️ 91.8787
Selling ➡️ 93.7162

#TRANSACTION
Buying ➡️ 96.2081
Selling ➡️ 98.1322

💶 Euro
#CASH
Buying ➡️ 81.0367
Selling ➡️ 82.6574

#TRANSACTION
Buying ➡️ 81.0366
Selling ➡️ 82.6574

ተጨማሪ ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
#Sidama

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፣ ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ በሚባለው አካባቢ ትላንት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ በ6 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

#SidamaRegionCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዛሬው የምንዛሬ ዋጋ ስንት ነው ? 💵 US Dollar #CASH Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 #TRANSACTION Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 💷 Pound Sterling #CASH Buying ➡️ 91.8787 Selling ➡️ 93.7162 #TRANSACTION Buying ➡️ 96.2081 Selling ➡️ 98.1322 💶 Euro #CASH…
በባንክ የምዛሬ ዋጋ በስንት ጨመረ ?

የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ከመደረጉ ከ3 ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ4895 ሳንቲም ነበር ፤ መሸጫው 58 ብር ከ6393 ሳንቲም ነበር።

አሁን ማሻሻያውን ተከትሎ በዛሬው የምናዛሬው ተመን አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 76 ብር ከ2311 ሳንቲም ሆኗል።

የአንድ ፓውንድ መግዣ ዋጋ 70 ብር ከ6759 ሳንቲም ፤ መሸጫው 72 ብር ከ0894 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 91 ብር 8787 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7162 ሳንቲም ሆኗል።

አንድ ዩሮ በ62 ከ3359 ሳንቲም ይገዛ ፤ በ63 ብር ከ5856 ሳንቲም ይሸጥ የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 81 ብር ከ0367 ሳንቲም ፤ መሸጫው 82 ብር ከ6574 ሳንቲም ሆኗል።

#ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል። (ሙሉ መግላጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ

ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ነገር ግን፣ በሁለትዮሽ የማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ (central bank deposits) እና በከረንሲ ልውውጥ (currency swap) መልክ የሚመጣውን 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከሌሎች ባለብዙ ወገኖች (multilaterals) ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውንና በሃደት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ የሚደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አያካትትም ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ " በዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የሚለገሰው ልዩ የገንዘብ እርዳታ የመንግሥትን የሪፎርም ሥራዎችን ጥንካሬ ያገናዘበና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ከሚባሉት የገንዘብ እርዳታዎች አንዱ ነው " ብሎታል።

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል። ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል። የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም…
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ?

1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል።

2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉ። ይህ ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይጠበቃል።

3ኛ. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

4ኛ. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡ በሂደት የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው የሚያስቀሩበት አሰራር ይዘረጋል።

5ኛ. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

6ኛ. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

7ኛ. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ተነስተዋል።

8ኛ. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

9ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ስዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሃሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

10ኛ. ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል።

11ኛ. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

12ኛ. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

13ኛ. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

#NationalBankofEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ? 1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል። 2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ…
#Ethiopia

በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች እና ፍቃድ የሚሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ላይ የሚሰሩ አካላት በራሳቸው መካከል እና ከደንበኞቻቸው ጋር በዋጋው ላይ ነጻ ድርድር በማድረግ የውጭ ምንዛሪ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንሰሚሆን ተነግሯል።

ባንኮች በየዕለቱ ለሚያደርጉት የውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚያውሉትን የምንዛሪ ዋጋ በቀኑ መጨረሻ ለብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ወይም Floating exchange rate " ወደ ስራ ገብቷል።

ማሻሻያውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74 ብር ከ7364 ሳንቲም እየገዛ በ76 ብር ከ2311 ሳንቲም በመሸጥ ላይ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል።

ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ምን አሉ ?

አየር መንገድ 577,746 የበረራ ሰዓቶችን እንደበረረና ይህም ቀደም ሲል ካለው 19 በመቶ እድገት እንዳሳየ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ አየር መንገዱ 17.1 ሚሊየን ተጓዧችን እንዳስተናገደ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆነው አለም አቀፍ ተጓዦች እንደሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል " ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ " ያለፈው በጀት ዓመት ማስተናገድ የተቻለው 2.7 ሚሊዮን የሀገር ተጓዦች ነበር " ብለዋል።

ከካርጎ ጋር ተያይዞ በዚህ ዓመት ካለፉት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ እንዳሳየ ተሰምቷል።

በዚህ በጀት ዓመት አየር መንገዱ ያጓጓዘው ጭነት መጠን ከ754, 681 ቶን ጭነት እንደሆነ ተናግረዋል።

" አየር መንገዱ ከካርጎ ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ " ቀደም ተብለው ከታዘዙ 20 የሚሆኑ አውሮፕላኖች ጋር ተደምሮ 125 የሚሆን አውሮፕላኖች እንደታዘዙ " ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

ከቦይንግ የታዘዙ አውሮፕላኖች አለመገኘታቸውን ተከትሎ የአውሮፕላን እጥረት እንዳጋጠመ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል። ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን…
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምን አሉ?

" ከቅርብ ወራት በፊት ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ቅሬታ ቀርቦልን ነበር፤ ይህም ከተሳፉሪዎች ሻንጣ ተያይዞ ወደኋላ እየቀረ ነው በሚልየቀረበ ነበር።

የተነሳውም የትራንስፖርቴሽን መዘግየትና የሻንጣ ዘግይቶ መድረስ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የተፈጠረው ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ብዙ ሻንጣ ይሸከማሉ፤ ሁሉንም ማስተናገድ ባለመቻላችን በሚቀጥለው በረራ ሻንጣዎችን እንልክ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከ737 አውሮፕላን ውጪ ከፍ ያለ የመንገደኞች ማመላለሻ እንዳንጠቀም እግድ ጥሎብን ነበር። በተጨማሪም በሳምንት ከ10 በረራ ውጪ እንዳናደርግ ተደርጎ ነበር።

መጋቢት ላይ ነው ይኼ የሆነው። ይህን ተከትሎ የኤርትራ ተጓዦች ከሻንጣቸው ጋር እንዲጓዙ ለማስቻል የተሳፋሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ተጓዦች ከሻንጣዎቻቸው ጋር እንዲጓዙ አድርገናል። ከዚያ በኋላ ይህ ነው የሚባል ቅሬታ አልሰማንም ነበር።

ይህን ተከትሎ ሰኔ መጀመሪያ ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀብለናል። ይህም የነበሩ በረራዎችን ወደ 15 እንድናሳድግና የምንጠቀመው አውሮፕላን ላይ ነበረው ገደብም መነሳቱን ተገልጾልን ነበር።

ይህንን ግን ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም፤ የአውርፕላን እጥረቶች አሉብን። በዚህ ምክንያት ይኽን ደብዳቤ ከተቀበልን በኋላ በነበረው አሰራር ቀጥለናል።

አሁን ላይ የወጣው ደብዳቤ ግን ከመስከረም 30/2024 በኋላ በረራ እንዳይደረግ የሚገልጽ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦብናል፤ በዚህ በጣም አዝነናል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቅሬታዎቹ ላይ እንወያይ ተብሎ ጥያቄ አልቀረበልንም፤ የነበሩ ችግሮች ላይ ቀደም ብለን መፍትሔ ሰጥተናል።

አሁንም የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ይህን የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ግን ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia