TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት⬇️

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከጥሪ እና በዓላት ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት ችግር እንዳይገጥማቸው ዝግጅት ማድረጉን ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ።

እንደሚታወቀው አዲሱን የትምህርት ዘመን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት #ለነባር እና #አዳዲስ ተማሪዎች ጥሪ የሚያቀርቡበት ነው።

ይህንንም ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ አዲስ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሚቀላቀሉት እና ነባር ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች የሚጓዙ ሲሆን በዚህ ወቅትም ተማሪዎች ለከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ይዳረጋሉ።

ችግሩንም ለመቅረፍም የዩኒቨርስቲዎቹን የጥሪ ጊዜ እና ዩኒቨርስቲዎቹ የሚገኙባቸው አከባቢያዊ በዓላትን ያገናዘበ ስርዓት በትምህርት ሚንስቴር እና በትራንስፖርት ባለስልጣን በመዘርጋቱ ከአምና ጀምሮ ችግሩን መፍታት ማቻሉን ተገልጿል።

በዚህ ዓመትም ይህንን ያገናዘበ አሰራር እንደሚተገበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መደረጉን በትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎቻቸውን የሚጠሩበት ወቅት የተለያየ እንዲሆን እና ጥሪውም በዚህ ወቅት ላይ የሚከበሩ በተለይ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎቹ የሚጠሩበት ወቅት በዛው አከባቢ በስፋት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በአላት ጋር እንዳይጋጩ
ተደርጓል።

እንዲሁም በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ገብተው አስፈላጊውን ዝግጅቶች በማድረግ ትምህርት የሚጀምሩበትን ጊዜ እንዳይዘገይ ለማድረግ፤ የአጭር ርቀት ጉዞ ብቻ የተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች በጊዜያዊነት የረጀም ጉዞ እንዲፈቀድላቸው ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የነበረው የኪሎ ሜትር ገደብ መነሳቱንም በትራንስፖርት ባለስልጣን የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ ተስፋየ በላቸው ተናግረውል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia