TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስልክ ሻጮቹ ተያዙ‼️

በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተያዙ፡፡
.
.
‹‹ሦስት ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ #የሞባይል_ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ይዣለሁ።›› የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት

‹‹ፓኪስታናውያኑ የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው።›› ገዥዎች
.
.
ከሁለት ቀናት በፊት በሰቆጣ ከትመው ‹‹መንገደኞች ነን፤ ገንዘብ #አጥሮን›› በማለት አገልግሎት የማይሰጡ ሞባይል የሚሸጡ ሦስት ፓኪስታናውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ አስታወቁ።

ፓኪስታናውያኑ ተጠርጣሬዎች የተያዙት በሰቆጣ ከተማ ነጋዴዎች ሱቅ ድረስ በመሄድ ‹‹ገንዘብ አጥሮን ነው፤ ግዙን›› እያሉ ሲዘዋወሩ ነው። ነዋሪዎችም የገዙት ሞባይል የማይሠራ በመሆኑ ‹‹ይጣራልን›› ማለታቸውን ተከትሎ ሕጋዊ ፍተሻ መደረጉ ታውቋል። በፍተሻውም 26 ስማርት ስልኮች፣ 52 ሺህ የኢትዮያ ብር፣ መጠኑ ያልተገለፀ የፈረንሳይ ገንዘብ እና 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላሮችን ይዘው ተገኝተዋል።

ተጠርጣሬዎች ስልኮችን ከገንዘብ በተጨማረ በወርቅ እየቀየሩም በመያዛቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ሲመረመሩም ግንበኞች እንጂ ተንቀሴቃሽ ነጋዴዎች እንዳልሆኑ ተረጋግጧል።

ኢንስፔክተር ደጀን ‹‹ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ያገኘውን ጥቆማ እና ቅሬታ ተከትሎ ተጠርጣሬዎችን በሕግ እንዲጠየቁ የማድረጉን ሥራ ጀምሯል›› ሲሉ ለአብመድ ተናግረዋል።

አብመድ ያነጋገራቸውና ስማርት ስልኩን ገዝተው እንደማይሠራ ለፖሊስ ካመለከቱት መካከል አቶ መርሻ ገብረኪዳን እና ታደሰ መልኩ ‹‹በየሱቃችን መጥተው ግዙን እያሉን ነበር›› ብለዋል።

‹‹ሦስቱ ፓኪስታናውያን የሸጡልን ሞባይሎች ሲም ሲገባ የማይሠሩ ናቸው። ‹20 ሺህ ብር የሚሸጥ ሞባይል ነው፤ ገንዘብ ስላጠረን ግዙን› ብለው 5 ሺህ ብር ገዛን፤ ግን አይሠሩም ነበር፡፡ በኋላ ላይ በየሱቁ ሌሎችንም ግዙን ሲሉ ለፖሊስ አመልክተናል›› ብለዋል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ‹‹ድርጊቱ ‹ነጭ ስለሆንን አንጠረጠርም› ብለው አስበው እንደነበር ያመላክታል፤ ይሁን እንጂ ደሴ እና መቀሌ ተመሳሳይ ሥራ መሥራታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ›› ብለዋል።

ኢንስፔክተር ደጀን ወንጀሉ ወደሌሎች ከተሞች እንዳይስፋፋ ኅብሰተሰቡ ያደረሰው መረጃ የሚመሠገን እንደሆነም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia