TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ‼️

ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ  የከተማ አስተዳደሩን #ያሳወቀ አካል አለመኖሩን የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

‘በሃዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል’ ተብሎ  በተሰራጨው #ሃሰተኛ_ወሬ ስጋት የገባቸው አንዳንድ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪና የንግድ ተቋማት #ተዘግተው ማርፈዳቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዶብሶ እንዳሉት ”ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ” በሚል  የከተማውን አስተዳደር ያሳወቀ አካል የለም፡፡

ይሁን እንጂ በሃዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ በተሰራጨው ሃሰተኛ ወሬ ስጋት የገባቸው አንዳንድ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪና የንግድ  ተቋማት ዛሬ ተዘግተው አርፍደዋል፡፡

የተወሰኑ የከተማው ነዋሪዎችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አለመላካቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

”የተናፈሰውን አሉባልታ በመስማት የከተማው ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት  ያለመላክና ሱቆቻቸውን የመዝጋት  እርምጃ መውሰዳቸው ተገቢ አይደለም’ ያሉት ኮማንደር መስፍን ‘የሃዋሳ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም የተዘጉ ቤቶች እንዲከፈቱ፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የከተማው ነዋሪዎች መደበኛ ኑሮውን ያለስጋት እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በከተማው አንዳንድ አካባቢዎች ንግድ ቤቶችን በማስፈራራትና በመዝጋት ገንዘብ የመውሰድና ባነሮችን አውርዶ የማውደም ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው የሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ፖሊስ አዛዡ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አዛዡ በሰጡት ምላሽም ነዋሪው በሰላም ወጥቶ እንዳይገባና በስጋት እንዲኖር በሚያደርጉና በተመሳሳይ ወንጀል የተሳተፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለአብነትም ከማውንቴን ስናክ ጎን በሚገኘው አንድነት ስጋ ቤት ዛሬ ጠዋት የዝርፊያ ወንጀል መፈጸሙንና በዚህ ወንጀል ውስጥ የተሳተፈ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል፡፡

የተቀሩት ሁለት ተጠርጣሪዎች እየተፈለጉ መሆናቸውን ፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል፡፡

በከተማው በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ሁከት የሚፈጥሩና ከተማውን የሚያውኩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

ከወንጀሉ ድርጊት ጀርባ ያለውን ሃይል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የከተማው ህዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ነዋሪዎች #ጥቆማ በመስጠት ከፖሊስ ጎን እንድቆሙ ፖሊስ አዛዡ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አየር ሃይል‼️

‘በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚናፈሰው ወሬ #ሃሰተኛ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል #ይልማ_መርደሳ ገለጹ።

ብርጋዴር ጄኔራሉ በምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ችግር መኖሩንና መንግስት ብዙ ትዕግስት ማሳየቱን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እርምጃ መውሰድ የጀመረ ቢሆንም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ‘በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ የሚነዛው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአካባቢው ከምድር ውጊያና የሰፈር ግጭት ያለፈና አውሮፕላን መጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ አለመኖሩንም ነው የገለጹት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
.
.
.
ምንም እንኳን መንግስት የአየር ጥቃት አልተፈፀመም፤ የሚናፈሰው ወሬም ሀሰት ነው ቢልም ከቀናት በፊት ቢቢሲ ያነጋገራቸው #የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ #የአየር_ጥቃት እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም #እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2011 ዓ.ም ያስመዘገባቸው ስኬቶች፣ በቀጣይ ዓመት ሊሰራ ያቀዳቸውንና ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች መገናኛ ብዙሃን ጠርቶ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ጥቂት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስም ተጠቅመው አፈፃፀሙን በተመለከተ #ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሀበራዊ ትሰስር ገፆች እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ይኸውም የባንኩ ትክክለኛ ገፅ እንደሆነ በማስመሰል የባንኩን ያለፈው ዓመት ክንውን አስመስለው የለቀቁትን ሃሰተኛ መረጃ ላነበበና መረጃውን ለሌሎች ሰላሳ ሰዎች እስከ መስከረም 20 ላጋራ/ሸር ላደረገ/፣ ባንኩ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ የሚያትት ሃሰተኛ መረጃ ነው፡፡

በመሆኑም #የተለቀቀው መረጃ ባንኩን በምንም ሁኔታ እንደማይመለከት እየገለፅን፣ ካሁን በፊት እንዳሳወቅነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃዎች የሚለቀቁት በባንካችን የሬዮና ቴሌቪዠን እንዲሁም በማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን ብቻ መሆኑን በድጋሚ እያሰወቅን፣ ህ/ሰቡ ከመሰል ሃሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን፡፡ በቀጣይ ባንኩን በተመለከተ መሰል #ሃሰተኛ መረጃ የሚለቁ ግልሰቦችን ለፍትህ አካል ለማቅረብ ባንኩ እየሰራ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ።

አበርገሌ ወረዳ 16, 900 #ሃሰተኛ የብር ኖቶች ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሃሰተኛ የብር ኖቶቹን ይዞ ትናንት በወረዳው ወርቃዲኑ ጥንስስ ከተማ ለመገበያየት ሲሞክር ተደርሶበት ነው።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia