TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባህርዳር

በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት ፥ አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።

እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ ተፈፅመዋል ስለተባሉ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች ፣ ዘረፋና እገታዎች የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የሚመለከታቸው አካላትን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ይገኛል፤ ምላሽ እንዳገኘ ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተሰማ። ከነዚህም መካከል ፦ - ከስራ ፈቃድ፣ - ከግብር፣ - ከቢሮ ኪራይ፣ - ከፋይናንስ አቅርቦት፣ - ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ ተብሏል። ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉ ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው…
' ስታርት አፕ '

በኢትዮጵያ ለ ‘ስታርት አፕ’ ዘርፍ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተለያዩ የሕግና የፋይናንስ አሠራር ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቀዋል።

ምንድነው የተደረጉት ማሻሻያዎች / የተዘረጉት አዳዲስ አሰራሮችስ ምንድናቸው ?

- የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር ይችላሉ።

- ማንኛውም የውጭ ሀገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል ይችላል።

- አዲስ ፈጠራ ያላቸውና ሥራቸው ወደ ገቢ መቀየር የሚችሉ ወጣቶች በውጭ ሀገራት ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ በሚጠየቁበት ወቅት በባንኮች በኩል መንግሥት በሚያመቻቸው አሠራር ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት አማራጭ ይመቻቻል።

- በፈጠራ ላይ ለተመረኮዙ ቴክኖሎጂ መር ሥራ ፈጣሪዎች በጉምሩክ አሠራር ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን የሚቀንስና የጉምሩክ ድጋፍ የሚያገኙበት ማዕከል ይቋቋማል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፥ " ወጣቶች እንደሀገር የተመቻቸላቸውን ዕድል በመጠቀም ሃሳባቸውን አውጥተው ሥራ ላይ ማዋልና የተሻለ ገቢ ማግኘት አለባቸው " ብለዋል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ዒድአልፈጥር

የዒድ አልፈጥር በዓል #ጨረቃ ዛሬ ከታየች ነገ #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ ይከበራል።

በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል ጨረቃ ለማየት በቱማይር እና ሱዳይር የመመልከቻ ቦታ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
የትምህርት ቤት መፀዳጃ ቤት #ተደርምሶ የ3 ታዳጊ ተማሪዎች ህይወት ተቀጠፈ።

ዛሬ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የጉሎመኻዳ ወረዳ በሚገኘው " መረታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " መፀዳጃ ቤት ተደርምሶ 3 ተማሪዎች ወዲያው ህይወታቸው አልፏል።

የመደርመስ አደጋው በእረፍት ጊዜ ከረፋዱ በ4:00 ሰአት የደረሰ ሲሆን የሴቶች የጋራ መፃዳጃ ቤት ሲጠቀሙ ከነበሩ 6 እንስት ተማሪዎች 3ቱ ወድያውኑ ሲሞቱ 3ቱ ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ትምህርት ቤቱ ፤ ለመፀዳጃ ቤቱ መደርመስ መንስኤው በአከባቢው የዘነበ ከባድ ዝናብ እና መፀዳጃ ቤቱ ለረጅም ጊዜ ማገልገሉ እንደሆነ ገልጿል።

አደጋው በት/ቤቱ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ወላጆች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘን መፍጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ዕለት እንደሚውል ተገልጿል። Via Haramain @tikvahethiopia
የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን #የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።

በዚህም መግለጫው ባለፉት #8_ወራት በአማራ ክልል በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝቡን እጅግ የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ መሆኑን ገልጿል።

" በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ #እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው " ብሏል።

" ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል " ሲል ምክር ቤቱ አስረድቷል።

እንደማሳያም ፦

➡️ በቀን በ29/7/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 የአንድ ቤተሰብ አባላትን እና 1 ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡

➡️ በ28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡

➡️ 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት 300 ሺህ ንር ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድለዉ ጥለዉታል፡፡

➡️ በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት " ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ " ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት 8 ወራት ፦
- ከ80 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን
- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መፈናቀላቸውን
- አርባ ሰባት (47) ሰዎች መታገታቸውን
- ከ260 በላይ ዘረፋዎች መፈፀማቸውን አሳውቋል።

" ይህን ዘረፋ፣ ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።

" ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት ፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ  " ሲል ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#የፀሀይ_ግርዶሽ

ዛሬ ሰኞ በተለያዩ ሀገራት ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ እየታየ ይገኛል።

በተለይ በሜክሲኮ እና አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እየታየ ነው።

የተለያዩ ቦታዎች በፀሀይ ግርዶሹ ምክንያት ከ3 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በሙሉ #ጨለማ_ተውጠው ታይተዋል።

ክስተቱንም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ነው።

የፀሀይ ግርዶሽ #ጨረቃ በምድር እና በፀሀይ  መካከል ስታልፍ የፀሀይን እይታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በምትጋርድበት ጊዜ የሚከሰት ነው። 

@tikvahethiopia