TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።

በዚህም መግለጫው ባለፉት #8_ወራት በአማራ ክልል በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝቡን እጅግ የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ መሆኑን ገልጿል።

" በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ #እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው " ብሏል።

" ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል " ሲል ምክር ቤቱ አስረድቷል።

እንደማሳያም ፦

➡️ በቀን በ29/7/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 የአንድ ቤተሰብ አባላትን እና 1 ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡

➡️ በ28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡

➡️ 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት 300 ሺህ ንር ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድለዉ ጥለዉታል፡፡

➡️ በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት " ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ " ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት 8 ወራት ፦
- ከ80 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን
- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መፈናቀላቸውን
- አርባ ሰባት (47) ሰዎች መታገታቸውን
- ከ260 በላይ ዘረፋዎች መፈፀማቸውን አሳውቋል።

" ይህን ዘረፋ፣ ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።

" ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት ፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ  " ሲል ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia