TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወንጂ

" ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻልም " - የሟች ቤተሰብ

ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ስለተገኙት 5ቱ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ቤተሰቦቻቸው ምን አሉ ?

ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜ አጠቀስ ያሉ የሟች ቤተሰብ አባል ፦

" 6 ሰዎች ነበሩ ፤ ለስራ በሄዱበት ነው የታገቱ። ምንድነው ሲባል ገንዘብ ነው የሚፈልጉት ፤ መጀመሪያ በሰው 600 ሺህ ብር አሉ ከዛ ደግሞ 300 ሺህ ብር አሉ።

የተጠየቀውን ገንዘብ መ/ቤቱ እንደ ህግ አይፈቅድም ብሎ ህዝብ፣ ሠራተኛው በሙሉ ማሰባሰብ መሯራጥ ጀመረ፤ እነሱን ለማትረፍ።

በዛ መሃል ከቤተሰብም ከምንም ገንዘቡ ተሰባስቦ ከእነሱ ጋር ግንኙነት አድርገን ገንዘብ ሰጥተን ለማስለቀቅ ሲባል ይሄ ወንጀል ነው ተብሎ የቤተሰብ አካል ሁሉ እንዲያዝ ተደርጎ ግንኙነቶቹም እንዲቆሙ ተደረገ።

ከዛ ፌዴራል እነሱን እናስለቅቃለን በሚል ገብቶ ግጥሚያ ገጥሞ ወንድሞቻችን በዚያ ምክንያት ህይወታችን አለፈ።

ምንም ማድረግ አይቻልም ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር። ስድስት ነበሩ አምስቱን ገደሏቸው። አንዱ አምልጧል ተብሏል አንዴ ሞቷል ይባለል ጭራሽ ሌላ ሰቀቀን ነው ለቤተሰብ ያ ሰውየ በህይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም። "

ሌላ አንድ የቤተሰብ አባል ፦

" እስከ ማክሰኞ ዕለት የሚፈልጉትን ብሩን ሰብስበን ፤ በአንድ ሰው 300 ሺህ ብር ነው የተስማማነው  ፤ ለእሮብ ጥዋት ብሩን እንድንሰጥና ቤተሰቦቻችንን እንድንወስድ ተነጋገርን።

ከዛ ብሩ ተሰብሰቦ ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን በካሽ እየቆጠርን እያለ መጡ ፖሊስ አባላት ከነብራችን ያዙን ከዛ " ብር መያዝ ብር መሰብሰብ እንደ ወንጀል እንደሚቆጠር አታውቁም ወይ ? " ብለው ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አሰሩን።  የተገረፈም አለ፣ ከየቤቱ አንድም ሁለትም ሰው ታሰረ ብቻ በጅምላ ነገሮችን እንደዛ አደረጉ፤ ወንጀለኛን በመርዳት በመደገፍ በሚል።

አጋቾች ሀሙስ ይሄ ነገር እንደ ሰሙ ብሩም እንደተያዘና ከዚህ መረጃ ተነግሯቸዋል (ብሩ ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ነው ቀጥታ ተይዞ የገባው ከቤተሰቦቻችን ጋር) ፤ አጋቾቹ ያገቷቸውን ቤተሰቦቻችንን ከተነጋገርንበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ህይወት እንዳጠፉ ተነገረን።

5ቱ ሰዎች ናቸው የተገደሉት። እጅግ በጣም አዘንን በቀል የእግዚአብሔር ነው ብለን ሁሉንም ነገር ትተናል።

6 እና 7 ቀን ከ60 ኪ/ሜ በላይ በእግር አስጉዘዋቸዋል። በየጫካው አሳድረዋቸዋል። ይህን በየአካባቢ ያሉ ሰዎች ነግረውናል። በጣም አዝነናል፤ ሞት አንድ ነው ግን እንዴት እንደዚህ አንድ ሞትን ለምኖ እስኪሞት ድረስ የተለመኑትን ሞት እንኳን ሳይሰጧቸው ተሰቃይተው ነው ቤተሰቦቻችን የሞቱት፤ ባሉበት በስብሰው።

መሳሪያ ብቻ አይደለም ያገኛቸው #በስለትም እንደተቆረጡ ሆስፒታል ሄደን አይተናል። በጣም አዝነናል። "

6ቱ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የካቲት 29 ነበር በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ለስራ ወደ ፋብሪካው የሸንኮራ ማሳ በማቅናት ላይ እያሉ  የታገቱ። ከፍተኛ ገቢ አላቸው ተብለው የተገመቱት ሲታገቱ ሌሎች ተለቀዋል። ከ6ቱ አምስቱ ተገድለዋል።

4ቱ ፋብሪካውን ለረጅም አመታት ያገለገሉ አንጋፋ ሰራተኞች ናቸው አንዱ ገና ወጣት ነው። ሁሉም ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሟች ቤተሰቦችን ቃል ያዳመጠው ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ  / ጋዜጠኛ ኬኔዲ አባተ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

@tikvahethiopia
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።

ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።

የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።

ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።

በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።

በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።

በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።

እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።

(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)

@tikvahethiopia
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

" ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ነው " እየተባለ ወደ ተለያዩ የባንኩ ደንበኞች ስልክ እየተደወለ የግል መረጃ መውሰድና የኦንላይን ዝርፊያ እየተሞከረ ይገኛል።

ቀደም ብሎ አንድ #አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ - ወንድ) ሳያውቀው ለባንክ ሰራተኛ ደውሎ ያጋጠመውን ክስተት አጋርተናል።

የዜጎችን ሀቅና ገንዘብ አታለው ለመዝረፍ ስልክ ከሚደውሉት መካከል #ሴቶችም ስለሚገኙበት ጥንቃቄ አድርጉ።

ከላይ ባለው የድምፅ ቅጂ የምትሰሟት አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ-ሴት) ከንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት እንደደወለች በማስመሰል ፦ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ኔትዎርኩ please try again ፣ connection problem ፣ error ፣ service not available " የሚል ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ትገልጸለች።

በዚህ ምክንያት ባንኩ ከብዙ ደንበኞቹ ቅሬታ በመምጣቱ ፤ " ችግሩን በዋናው የንግድ ባንክ መ/ ቤት #ሲስተም ላይ ለማስተከል ነው " በማለት የደንበኛውን የግል መረጃዎች በመቀበልና በማታለል ዝርፊያ ለመፈፀም ሞክራለች።

አሁን ላይ እንዲህ ያሉት አጭበርባሪዎች ተበራክተዋል ተጠንቀቁ።

ለማንኛውም #የማታውቁት ስልክ የባንክ መረጃችሁን እንዳትሰጡ።

@tikvahethiopia
እንደልብ ለ 7 ቀናት !

በ350ብር ብቻ ያልተገደበ ሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether
" በቴክኒካል ብልሽት የዲጅታል አገልግሎት ተቋርጧል " - CRRSA

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፤ በዋና የከተማው መረጃ ማዕከል ላይ የቴክኒካል ብልሽት እንዳጋጠመው አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት የዲጂታል አገልግሎቱ ከትላንት ጀምሮ እንደተቋረጠ ገልጿል።

ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ጥገና በማድረግ ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሆነም አስረድቶ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ? ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው…
#ትግራይ
 
የትግራይ የማህበረሰብ ተወካዮች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በመከሩበት ወቅት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጦርነት በፊት ለንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፍያ የወሰዱት የብድር ወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት እንዲነሳ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወሳል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምን የተደረሰ ውሳኔ አለ ? ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ፤ የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ከፍተኛ አመራሮችን አነጋግሯል።

አመራሮቹ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ትእዛዝ እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ከጦርነቱ በፊት የተወሰደው የብድር ወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት በሚመለከት አጥንቶ በ10 ቀናት ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ አገር አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞዋል ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰጡት ትእዛዝና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ፤ በጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ የሚመራ ፦
- የመከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር አብራሃም በላይ 
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ
- የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ
- የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ 
- የጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ተክልወለድ አጥናፉ 
- የትግራይ የማህበረሰብ ንግድ ከፍተኛ አመራሮች በአባልነት ያካተተ አገር አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

አገር አቀፍ ኮሚቴው ፦
ከጦርነቱ በፊት የተወሰደው በድር ምን ያህል እንደሆነ ?
የብድሩ ወለድ የወለድ ወለድና ቅጣት ስንት እንደሆነ ? አጥንቶ ያቀርባል ያሉት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ከፍተኛ አመራሮች ፤ በጦርነቱ የወደመ የንግድና የኢንቨስትመንት የገንዘብ መጠን ሳይጨምር የወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት ብቻ እስከ 60 ቢሊዮን ብር እንዲሰረዝ በጥናት ያቀርባል ብለዋል።
 
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት ለብሄራዊ ባንክና ገንዘብ ሚንስቴር ጨምሮ ጥያቄው ለሚመለከታቸው ከፍተኛ የፌደራል የሚንስቴር መ/ቤቶች በተደጋጋሚ መቅረቡም አስታውሰው ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ትእዛዝና ባስቀመጡት አቅጣጫ ጥናቱ አስከ መጋቢት 20/2016 ዓ.ም ተጠናቅቆ ቀርቦ እንደ ጡረታው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

መረጃው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                        
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ? - " ችግሩ የተከሰተው አንድ ሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስህተት በመፈጠሩ ነው። የተፈጠረው ስህተት ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቶ ነበር። " - " የሲስተም ማሻሻያው የተተገበረው አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር። ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ችግር እንዳለ ሊለይ…
" እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እናሳውቃለን - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ከ " ቢቢሲ ኒውስ ዴይ " ጋር በነበራቸው ቆይታ ባንኩ የሲስተም ብልሽት ባጋጠመው ወቅት የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

" በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን ስለሆኑ እናውቃቸዋለን። " ያሉት የባንኩ ፕሬዜዳንት ፤ " የፈጸሙት ተግባር በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ለፖሊስ ማንነታቸውን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ አርብ መጋቢት 6 ለሊት የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ዘግቧል።

ይህ ወጥቷል የተባለው ገንዘብ ትክክለኛ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት የባንኩ ፕሬዝዳንት ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።

" ገና ኦዲት እየተደረገ ነው። ዝውውሩ ውስብስብ ነው። ጤናማ የሆነ ዝውውር የፈጸሙ እንዳሉ ሁሉ፤ የሌላቸውን ገንዘብ ያወጡም አሉ። ስለዚህ ማጣራት ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ጊዜ ይፈልጋል። ምናልባት በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንጭርሳለን ብለን እንጠብቃለን "ብለዋል።

አቶ አቤ ፤ 10 ሺህ የሚሆኑ #ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አርብ ሌሊት ከ490 ሺህ በላይ " ጤናማ እና ጤናማ ያልሆኑ " የገንዘብ ዝውውሮች መከናወናቸውን መናገራቸው ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia
መተግበሪያዎን ሲቢኢ ብር ላይ ያስቀምጡ
በቀላሉ በርካታ ደንበኞች ዘንድ ይድረሱ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
" ኑ ቸርነትን እናድርግ "

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ገልጿል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " በየጊዜው በሚከሰከቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ወገን ለወገኑ መርዳት ስላለበት ሌሎች አገልግሎቶችን ለጊዜው በመግታት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራ ተወስኗል " ብለዋል።

በተለይም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በስፋት ድጋፍና እርዳታ እንደሚደረግ በዚህ የጾም ወቅት ደግሞ ምጽዋት ማድረግ አግባብም እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ፤ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በዚህ ወቅት ፤ በአንድ ልብ እና ሀሳብ በመሆን ለተቸገሩት መድረስ እንደሚገባ ፤ ብፁዓን አባቶች በማስተማር ፤ ማኅበራት ፣ ሰንበት ት/ቤቶች ፣ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ በገንዘብ በዓይነት ሊበላሹ የማይችሉ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማኅበሩ ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ፦
- ብፁዓን አባቶች ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ ፤
- በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ትምህርተ ወንጌል ፤
- የመዝሙር አገልግሎት፤
- ዶክመንተሪ ቪዲዮ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አባቶችን ጨምሮ የሚደረግ መርሐ ግብር ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከማህበሩ ባገኘው መረጃ ፤ የመግቢያ ትኬት መቶ ብር እየተሸጠ ሲሆን በዕለቱ እዛው በር ላይም ይሸጣል።

አሁን በተዘጋጀው የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ለማይችሉ በተለያዩ በሚዘጋጁ የድጋፍ ማድረጊያዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የመርሐ ግብሩን የመግቢያ ትኬት :-
1.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2.  በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3.  በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5.  በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6.  በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ይገኛል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ በ09 44 71 82 82 እና 09 42 40 76 60 መደወል ይችላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሥራ ሲያመሩ በአማራ ክልል ጎጃም ውስጥ ስለታገቱ ዜጎች ሰምቶ እንደሆነና መረጃው ይኖረው እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል። የተጀመረ ምርመራ ካለም ማብራሪያ ጠይቀናል። አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ መረጃው አለን። በሥራ ላይ ነን። ምናልባት እንግዲህ ፋይንዲንጎች ሲኖሩ እናሳውቃለን ” ሲሉ አረጋግጠዋል።…
#Update

• " በአማራ ክልል ውስጥ የተያዙት ልጆቻችን እንጀራ ፍለጋ የወጡ እንጅ ሌላ ተለእኮ እንደሌላቸዉ እኛ ምስክሮች ነን " - የጋርዱላ ዞን የሀይማኖት አባቶች

• " ወጣቶቹን መልምሎ የወሰደዉ የግል ድርጅት መሆኑ የወጣቶችን ለስራ መሰማራት ያሳያል " - የጋረዱላ ዞን አስተዳደር

ከሰሞኑ ለስራ ጉዳይ ወደታላቁ የህዳሴ ግድብ በመሄድ ላይ ሳሉ በፋኖ ተያዙ ስለተባሉ ወጣቶችን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ኩናሎ ፤ ከዞናቸዉ ለስራ ሄደዉ የተያዙ ወጣቶች እጅግ አሳሳቢ እንደሆነባቸዉና ከሀገር ሽማግሌ እስከ ሀይማኖት አባትና የመንግስት አካላት ወጣቶቹን ለማስለቀቅ ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ ፤ ወጣቶቹ ከደራሼ አሌና አካባቢዉ በባለሀብት በኩል ተመዝግበዉ እንጀራ ፍለጋ መሄዳቸውን በመግለጽ " ይህ ደግሞ ንጽህናቸዉን ይገልጻል " ብለዋል።

አሁን ላይ ጉዳዩን ውጤታማ ለማድረግ  ከቀይ መስቀል ጋርም ስራ እየተሰራ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ የአማራ ክልልና የፌደራል መንግስቱም እየጣሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የጋርዱላ ዞን ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ቀሲስ መምሬ ተክሌ ደስይበለዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " እነዚህ ወጣቶች ምስኪን እነጀራ ፈላጊ እንጅ የፖለቲካ ተልእኮ የላቸዉም " ብለዋል።

" አሁን ላይ የታጋቾቹ ቤተሰቦች ከአማራ ክልል ጋር ተነጋግራችሁ ልጆቻችን አስመልሱ " በማለት እየጠየቁን ነው የሚሉት ቀሲስ መምሬ ተክሌ ፤ " የልጆቹን ንጽህና ተረድተዉ  የያዟቸዉ አካላት ይለቁልን ዘንድ  እንጠይቃለን " ብለዋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለስራ ሲሄዱ ተያዙ ከተባሉ ወጣቶች ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፦ " ልጆቹ አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ እንዳገኟቸው፤ ሲመሯቸው የነበሩትም ወታደሮች እንደነበሩ ከራሳቸው ከተገኘው መታወቂያቸው ማረጋገጣቸውን ነገር ግን በቀጣይ ከ72 እስከ 100 ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ " አሳውቀው ነበር።

ምንም እንኳን ይህ ከተባለ ቀናት ቢያልፉም የወጣቶቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

➡️ " የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል " - የዶክተር በሀይሉ ቤተሰብ 

➡️ " ይቅርታ መረጃው የለኝም " - የአዲስ አበባ ፓሊስ

እውቁና እጅግ የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር በኃይሉ ኃይሉ መገደላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ዶ/ር በኃይሉ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ለጥዋት ሩጫ በሚል በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው የተገለጸው።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለዋል።

ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ? ቤታቸው የት አካባቢ ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ቀብሩ ተፈጽሟል፣ ከትላንት ወዲያ ሰዓሊተ ምህረት " ብለው፣ ቤታቸውን በተመለከተም፣ " ቦሌ ሚካኤል ነው። ሞተ ያሉት ደግሞ ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስን ለመጠየቅ ጥረት አድርጓል።

የኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት አጭር የፅሑፍ  ምላሽ፤  " ይቅርታ መረጃው የለኝም " ሲሉ ለጊዜው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በቀጣይም የአዲስ አበባ ፖሊስን ስለ ጉዳዩ የምጠይቅ ይሆናል።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ የቀድ ጥገና ሀኪሙን ግድያ በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንዳለ ለኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ አንድ የማኀበሩ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፣ " እኔም በማኀበራዊ ድረገፅ ነው የሰማሁት በጣም ያሳዝናል " ብለዋል።

አክለውም፣ " ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው ተመሳሳይ ነገር የተፈጸመው። ዶክተር እስራኤል ጥላሁን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሏል። እየሆነ ያለዉ ነገር ልብ ይሰብራል። ሁኔታውን አጣርተን መግለጫ እናወጣለን። ለአሁኑ ግን በቂ መረጃ የለንም በጉዳዩ ዙርያ " ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር በበኩሉ በዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ሞት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ መግለጫ አውጥቷል።

ለዶክተሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia