TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በቁጥጥር ስር ዋለ። በስዊዲን የወሲብ ጥቃት በመፈፀም ተጠርጥሮ በህግ የሚፈለገው ጁሊያን አሳንጅ ላለፉት ሰባት ዓመታት በለንደን በሚገኘው የኢኳደር ኤምባሲ ተጠልሎ ቆይቷል።

የብሪታኒያ ፖሊስ አሳንጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን ይፋ አድርጓል። ኢኳዶር በኤምባሲው የሰጠችው ጥገኝነትን ማቋረጧን ተከትሎ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። ሀገሪቱ በኤምባሲዋ ያስጠለለችው አሳንጅ በተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በመጣሱ ነው ያቋረጥኩት ብላለች።

ፖሊስ የዌስት ሚኒስቴር ማጀስትሬት ፍርድ ቤት በፈረንጆቹ 2012 ባወጣበት የእስር ማዘዣ መሰረት ነው በቁጥጥር ስር ያዋለው።

Via #fbc #cnn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

የአይኤስ-አይኤስ መሪው አቡባክር አል-ባግዳዲ ሶሪያ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን ሳይገደል እንዳልቀረ ተሰምቷል። አሜሪካ በትላንትናው ዕለት ሶሪያ ውስጥ የISIS መሪውን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ሰንዝራ ነበር።

#CNN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines #CNN

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን CNN ለማስታወቂያ 60 ሺ የአሜሪካ ዶላር መድቤያለሁ ማለቱን ሸገር ሰምቷል፡፡ CNN አየር መንገዱን እና ኢትዮጵያን በአለም ለማስተዋወቅ ተመርጧል ተብሏል፡፡

በ60 ሺህ ዶላርም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በአሜሪካ በሚገኘው እውቁ የቴሌቪዥን ቻናል Cable News Network (CNN) ይተዋወቃል ብለው ለሸገር ኤፍ ኤም የተናገሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ናቸው፡፡

በCNN የቴሌቪዥን ቻናልም ስለ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚነገር ማስታወቂያ ለ2 ወር በየቀኑ 3 እና 4 ጊዜ ይተዋወቃል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከCNN ጋር በማስታወቂያው ጉዳይ እንዳልተፈራረመ ነገር ግን በሂደት ላይ እንዳለ አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

(SHEGER FM)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራሃቱ የሲ ኤን ኤን (CNN) ን የዓመቱ ጀግና ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡ #ጀግኒት #CNN

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FerweyniMebrhatu #CNN

"ፍሬወይኒ መብራሃቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የ2019 የሲ.ኤን.ኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ በመጠራቷ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል። ሴት ልጆች በትምህርት ቤት እንዲቆዩ ያላት ቆራጥነት፣ እንዲሁም ማኅበረሰቧን የተሻለ ለማድረግ ያላት አቋም የሚደነቅ ነው። ኢትዮጵያ በፍሬወይኒ ኮርታለች።" ዶ/ር ዐብይ አህመድ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር)
.
.
"የእኛው ፍሬወይኒ CNN የ2019 ጀግና ሆነች!! እንኳን ደስ አለሽ! በተፈጥሯው ጉዳይ ለሚሸማቀቁ: ከትምህርታቸው ለሚስተጏጎሉ: ለሚያቋርጡ:ከሌላው በታች የሆኑ ለሚመስላቸው..የአገራችን ሴቶች ትልቅ ቀን ነው!ተባብረን ዘላቂ መፍትሄ እናምጣ!" ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
በኬንያ 3 አሜሪካዊያን ተገድለዋል...

ትናንት በኬኒያ ላሙ ዳርቻ የጦር ሰፈር በተፈፀመው ጥቃት 3 አሜሪካውያን መገደላቸው ተሰምቷል። አሜሪካና ኬንያ በጋራ በማጠቀሙት በላሙ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር አል-ሸባብ በፈፀመው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር አባል እና 2 ኮንትራክተሮች በድምሩ 3 አሜሪካዊያን ሲገደሉ ሌሎች 2 ግለሰቦች ደግሞ ቆስለዋል።

#AlAin #CNN #AssociatedPress
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በአሜሪካ ዋሽንግተን ስቴት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 6 የደረሰ ሲሆን 18 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተነግሯል።

#CNN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#CNN : በትግራይ በመንቀሳቀስ የሰራው ዘገባ ፦

- ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ምድር ለቀው ይወጣሉ ካሉ ሳምንታት ቢያልፉም የኤርትራ ወታደሮች ግን በትግራይ አሉ።

- የኤርትራ ወታደሮች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ ያደናቅፋሉ።

- የCNN ጋዜጠኞች የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ኬላዎችን ሲቆጣጠሩ፣ ወሳኝ የሆኑ የእርዳታ መስመሮችን በመያዝ እርዳታ ሲያደናቅፉ ፣ በክልሉ ካሉት ጥቂት ሆስፒታሎች በአንዱ ውስጥ ተዘዋውረው የህክምና ሰራተኞችን እንደሚያስፈራሩ ሪፖርት አድርገዋል።

- የኤርትራ ወታደሮች በማዕከላዊ ዞን ለ2 ሳምንት፣ በሰሜን ምዕራብ ለ1 ወር የዕርዳታ ማመላለሻ መንገዶችን ዘግተው ነበር።

- CNN ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር የሚሰሩ የደህንነት ኃላፊዎች ነገሩኝ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ወታደሮች ላይ ቁጥጥር የለውም።

- በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የተንቀሳቀሱ የCNN ጋዜጠኞች የኤርትራ ወታደሮች መመልከታቸውን ተናግረዋል፤ የተወሰኑት የድሮውን የኢትዮጵያ ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው።

https://amp.cnn.com/cnn/2021/05/12/africa/tigray-axum-aid-blockade-cmd-intl/index.html?__twitter_impression=true

@tikvahethiopia
#አሜሪካ

ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ፤ በሉዊዚያና ግዛት ከታች አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ባሉ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት እንዲለጥፉ ታዟል።

ትላንት ደግሞ የኦክላሆማ ግዛት በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲጀመር አዟል።

የግዛቱ ትምህርት ቢሮ በግዛቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው በአስቸኳይ እንዲያካትቱና እንዲያስተምሩ መመሪያ አስትላልፏል።

በግዛቱ የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ሪያን ዋልተርስ የተላከ መመሪያ " አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን " የሚፈልግ አስገዳጅ ድንብ ነው ይላል።

ዋልተርስ " መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ነው "  ብለዋል።

" ያለ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ እውቀት የኦክላሆማ ተማሪዎች የአገራችንን መሠረት በትክክል መረዳት አይችሉም " በማለት ነው በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲሰጥ መታዘዙን ያመለከቱት።

በግዛቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ይተገበራል።

ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ እያንዳንዱ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረው ይገባል ተብሏል። ሁሉም አስተማሪዎች በክፍሉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማስተማር እንዳለባቸው ታዟል።

የሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን ይህንን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ብለዋል።

አንድ መንግሥትን ከሃይማኖት መለያየት እንዳለበት የሚሰራ ተቋም ፥ " የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች አይደሉም " ብሏል።

" ሪያን ዋልተርስ የተሰጠውን የመንግሥት ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ሃይማኖታዊ እምነቱን በሌሎች ላይ ለመጫን እየተጠቀመበት ነው። ይህ እኛ ባለንበት ሊሳካ አይገባም " ብሏል ተቋሙ።

በአሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ለማስጠበቅ የሚሰራው ኢንተርፌይዝ አሊያንስ ፤ " መመሪያው ግልጽ በሆነ መልኩ ሃይማኖትን መጫን ነው " ሲል ገልጾታል።

" እውነተኛ የእምነት ነፃነት ማለት የትኛውም የሃይማኖት ቡድን አመለካከቱን በሁሉም አሜሪካውያን ላይ እንዳይጭን መከላከል ነው " ብሏል።

#BBC #CNN

@tikvahethiopia
" ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን ! " - ጆ ባይደን

በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲያቸውን ወክለው ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የጤናቸው ነገር አሳሳቢ ነው እየተባለ ነው።

" እርጅናም ተጫጭኗቸዋል፣ በትልልቅ መድረኮች የሚነገሯቸውን ነገሮች እየሳቱ ነው ፤ ስለዚህ ምክትላቸው ይተኳቸውና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከሩ " የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ባይደን ግን ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ ፥
- ፍጹም ጤናማ መሆናቸውን ፣
- እንደ ቀድሞው መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሥራቸውን መጨረስ ካልቻሉ ብቻ እንደበቃቸው ምልክት እንደሚሆን፣
- አሁን ላይ ምንም ዓይነት የድካም ምልክት እንደሌላቸው ነው የሚመልሱት።

ትላንት በነበረ አንድ የNATO ፕሮግራም የሚዲያ መግለጫ ላይ ፥  የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ለንግግር ሲጋብዙ " ፕሬዝደንት ፑቲን " ብለው መጥራታቸው በሥፍራው የነበረውን ታዳሚ አስደንግጧል።

ዜሌንስኪም ክው ብለው ቀርተዋል።

ወዲያው ግን ጆ ባይደን ፥ " የፑቱን ነገር አሳስቢ ሆኖብን እዛ ላይ ብዙ ስለቆየሁ ነው ፤ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ " ሲሉ ስህተታቸውን አርመዋል።

ዜሌንስኪ " እኔ እሻላለሁ ! (ከፑቱን ማለታቸው ነው) " ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደንም ፥ " በእርግጥም በደንብ ትሻላለህ " ሲሉ መልሰዋል።

ከዚህ ቀጥሎ በነበረ አንድ መግለጫ ላይ ደግሞ የገዛ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስን " ምክትል ፕሬዝዳንት ትራምፕ " ብለው ሲጠሩ በርካቶች በድንጋጤ ተመልክተዋቸዋል።

በቅርብ ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበረ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ክርክር ወቅት ያሳዩት አቋምም ምርጫውን ለማሸነፍ አጠያያቂ ሆኖ ነበር።

የ81 ዓመቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ግን " ደህና ነኝ ምርጫውንም አሸንፋለሁ " ባይ ናቸው።

ክስተቶቹን የሚያሳይ ቪድዮ ከላይ ተያይዟል።

#BBC
#CNN

@tikvahethiopia
#USA

ከግድያ የተረፉት የቀድሞው ፕሬዜዳንት ትረምፕ !

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለቀጣዩ ምርጫ ፔንሰልቬኒያ፣ ባትለር ውስጥ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ እያሉ ከሕዝቡ መካከል በተተኮሰ ጥይት ደም በደም ሆነው ከመድረኩ ሲወርዱ ታይተዋል።

ትረምፕ የድንበር አቋራጮች ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ ለማሳየት ሲጋብዙ እና የቁጥር ማሳያ ደውል መደወል ሲጀምር ከሕዝቡ መካከል የተኩስ ድምጽ የተሰማው።

ከዚያም ትረምፕ ቀኝ እጃቸውን ወደ አንገታቸው ሲልኩ ታይተዋል።

ወዲያውኑ ፊታቸው ላይ ደም ሲወርድ ታይቷል።

ትረምፕ ተኩሱ ከተሰማበት አቅጣጫ በኩል ራሳቸውን ለመከለል ወደ ታች ሲሸሹ እና የደኅንነት ሠራተኞች በፍጥነት ወደ መድረኩ ሲሮጡ ታይተዋል።

በዚህ ሰዓትም የሕዝቡ ጩኸት ይሰማ ነበር።

ትረምፕ ቀና ብለው እጃቸውን ወደላይ ሲያነሱ በምርጫ ቅስቀሳው ላይ የነበረው ሕዝብ ጩኸት ከፍ ብሎ ተሰምቷል።

የ "ሴክሬት ሰርቪስ " የሕግ አስከባሪዎች ትራምፕ በፍጥነት ከመድረክ እንዲወርዱ አድርገዋል።

ትራምፕ የግድያ ሙከራው ከተደረገባቸው በኃላ ወደ ሆስፒታል ተወስደው እርዳታ ከተደረገላቸው በኃላ ኒው ጀርዚ ተመልሰዋል።

ያለ ምንም የሰው ድጋፍ እራሳቸው እየተራመዱ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ታይተዋል።

" ደህና " መሆናቸውም ታውቋል።

የግድያ ሙከራውን የፈጸመው ግለሰብ በአሜሪካ ሴክሬት ሰርቪስ ደኅንነት አባላት መገደሉን ተሰምቷል።

ከተጠርጣሪው በተጨማሪ ሁለት ሰዎች በተኩስ ልውውጡ መገደላቸውን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰላቸው ተገልጿል። #VOA #CNN

@tikvahethiopia