TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 😢 ፦ " ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦ - ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት…
#ትግራይ

" ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን 2 ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ ! " - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ በነበረው የዓድዋ ድል በዓል  ላይ እምባ እየተናነቃቸው 😭 ንግግር አድርገው ነበር።

እሳቸው በእንባ ንግግር ሲያደርጉ የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ ከፍተኛ የሀዘን ስሜቱ ከፊቱ ይነበብ እንደነበር በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምን አሉ ?

" ዛሬ ወደ ትግራይ ስመለስ በህሊናዬ የሚመጡብኝ ብዙ ትዝታዎች አሉብኝ።

ይቅርታ አድርጉልኝና አጋጣሚውን ተጠቅሜ ማንሳት እፈልጋለሁ።

በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው ከነበሩ ወገኖች መካከል አንዷ ፈንጠር ብላ የተቀመጠች አንዲት ሴት ለማነጋገር ሞክሬ ነበር።

በተፈናቃዮች ካምፕ ጉብኝት ልብን የሚሰብር  ነው። ከቤት ንብረታቸው ወጥተው ፣ ክብራቸውን አጥተው ቁጭ ብለው ጉብኝት .. እኛ ደግሞ እንመጣለን ልናያቸው።

ታዲያ ያችን ሴት ጠጋ ብዬ ሳነጋግራት፤ በጥሩ አልመለሰችልኝም። ጥቂት ያመጣሁትን እቃ እንድታከፋፍልልኝ ነበር ልጠይቃት የነበረው ' ያንቺን እቃ አልፈልግም ' አለችኝ።

በሆስፒታል እና በመጠለያ ጣቢያቸው ሄጄ ያየዋቸዋን ሴቶች በእጅጉ አስባቸዋለሁ። እቺን ሴትዮ ለምንድነው የምትመልሽልኝ ስላት ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን ሁለት ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ መልስ የለኝም ፤ አይመልስም ብቻ ነው ያልኳት።

ጦርነቱ ተዛምቶ በአፋር ክልል ሰመራ ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበሩ የተማረኩ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን አግኝቻቸዋለሁ ሳናግራቸው ያሉኝ ከልቤ አይጠፋም ፤ ቦታቸው እዛ አልነበራም ትምህርት ቤት ነው።

ያሉኝ ' እኛ መመለስ የምንፈልገው ወደ ትምህርት ቤት ነው ' ይሄንን ወግቼ ያንን አሸንፌ የሚል ዓላማ አልነበራቸውም። በክፍላቸው ግርግዳ ላይ የፃፉት የለጠፉት የአፋር ህዝብ እንዴት ደግ እንደሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያዊ እንዴት እንደሚረዳዳ ነው።

ሌሎችም አሉ ብዙ እርጉዝ ሆነው ሶስት ልጅ ወልደው ሲንከራተቱ የነበሩ ... ለማንኛውም ብዙ መንከራተት ነበር።

ዛሬ እዚህ ቆሜ የትግራይ እናቶች ያሳለፉትን #ሰቆቃ በእውነቱ እረዳለሁ ለማለት ነው ይሄን ሁሉ የምናገረው። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎ !!

ዞሮ ዞሮ የማንኛውም ግጭት መጨረሻው ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የሰላም ስምምነት መፈረሙ አይቀርምና ይህ ሳይሆን ተጨራርሰን ተጨካክነን ፣ ዘርና ሃይማኖት መለያያ አድርገን ሃይማኖቶችን ከፋፍለን ሳይሆን በቅድሚያ መከላከል እንዳለብን መገንዘብ አለብን።

የዓድዋ ባለቤቶች እንዳልሆንን ገፅታችንን አጉድፈን አበላሽተናል። "

#TikvahFamilyAdawa

@tikvahethiopia