TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ውስጥ ሞተር ሳይክሎችና ከ2 ቶን በላይ የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ማሽከርከር የማይችሉባቸው መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሰታወቀ።

ክልከላውን በሚጥሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጠንካራ እርምጃዎች እንደሚወሰድም አስጠንቅቋል።

ክልከላው ከቦሌ ፣ በኦሎምፒያ ፣ መስቀለ አደባባይ ፣ ብሔራዊ ቤተ -መንግሥት ፣ አራት ኪሎ በሁለቱም አቅጣጫ ነው።

ይህ በተመለከቱ የትራፊክ ፍሰቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው የትራፊክ ምልክቶች ተተክለዋል።

ክልከላው ነገ ታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን የተሽከርካሪ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ /
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02RhMb9b3k13NyQtQsPR81U8vn7dHTShcx9QwiKghqkR8CL9ZksK7EQ3mw8sCmo8ujl&id=100064830633094&mibextid=WiMSqg

@tikvahethiopia
#EOTC

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፦

(ባለፈው ዓመት የልደት በዓልን ጨምሮ ሌሎች መንፈሳዊ በዓላት አከባበርን በተመለከተ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው የተናገሩት)

" ... ይህንን የልደት በዓል ስናከበር የት ነው የምንሄደው ? ቀድሞ በዓሉን ለማክበር የት ነው የምንሄደው ? ስንል ጭፈራ ቤት አይደለም፣ ሙዚቃ ቤት አይደለም ፣ ይሄ በዓል የሚከበረው በጭፈራም አይደለም፤ በዘፈንም አይደለም፣ በሙዚቃም አይደለም፤ በበዓላችን ላይ ሙዚቃ እየቀላቀላችሁ / ጭፍራ እያስገባችሁ የበዓሉን እሴት / ሃይማኖታዊ ትርጉም የምታበላሹት #የሚዲያ አካላት ናችሁ።

ይሄ በዓል የሚከበረው በጭፈራም አይደለም፤ በዘፈንም አይደለም፤ በሙዚቃም አይደለም።

የበዓሉን ትርጓሜውን ማወቅ ያስፈልጋል። ያን እለት መላእክትና ሰዎች አልዘፈኑም እኮ፣ አልጨፈሩም እኮ ፤ መላእክትና ሰዎች ደስታቸውን የገለጡት በምስጋና ነው። ዕለቱ የሚከበረው በምስጋና ነው። አባቶቻችን የበዓሉን አከባበር ወደኛ ያደረሱት በዚህ መንገድ ነው። እኛም ለትውልድ የምናስተለልፈው በዚህ ሁኔታ ነው።

የበዓሉን መንፈሳዊ ስነስርዓት በጠበቀ መልኩ ወደትውልድ ማስተላልፈ ይኖርብናል።

የበዓሉንም መንፈሳዊ ስነስርዓት እሴት ስንል ለምን ተወለደ ? የት ተወለደ ? ከሚለው ትርጓሜ ይጀምራል፤ ሲወለድ ምን ተከሰተ፣ ምን ተደረገ ? መላዕክት፣ እረኞች፣ ሰባሰገል ምን አደረጉ ? ድንግል ማርያም ምን አደረገች ? እንስሳትስ ምን አደረጉ ? የሚሉትን ነገሮች ነው የምንወስደውና የምናስበው። ስለዚህ እነሱ ያደረጉትን እያደረግን ነው ለትውልድ ማስተላለፍ የሚገባን።

ይህ ለልደት በዓል ብቻ ሳይሆን የ #ጥምቀት በዓልም፣ ሌሎች መንፈሳዊያን በዓላቶቻችን ሁሉ ፣ መንፈሳዊያን በዓላት እስከሆኑ ድረስ በመንፈሳዊ ስነስርዓት ነው ማክበር የሚገባን፣ ሃይማኖታዊ በዓል ብለን እስከሰየምን ድረስ ሃይማኖቱ በሚፈቅደው ስነስርዓት/እሴት ነው በዓላቱ ተከብረው መዋል ያለባቸው፤ ተከብረው ማለፍ ያለባቸው።

ትውልዱም ማወቅ እና መማር ያለበት በእንዲህ ያለ ሁኔታ ነው። "

@tikvahethiopia
" በተፈጠረ የግለሰቦች አለመግባባት ህይወት ሊጠፋ ችሏል " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

" ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የግብርና ሚኒስቴር ሜካናይዜሽን የስራ ሂደት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ በረከት ፎርሲዶ በአንድ የመዝናኛ ስፍራ በጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል " የሚል መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት ተመልክቷል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማጣራት ጥረት አድርጓል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያዬታቸዉን የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ወንጀሉ የተፈጸመው በመዝናኛ ቦታ በተነሳ የግል ጸብ መሆኑን ገልጸዋል።

በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባት ሟች #በሽጉጥ ራሳቸዉ አካባቢ ተመተው መውደቃቸዉን ፤ ከተመቱ በኋላ ወደሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸዉ ሊተርፍ አለመቻሉን አስረድተዋል።

ኢንስፔክተሩ ፤ ፖሊስ አስክሬኑን ወደአዲስ አበባ ወስዶ ካስመረመረ በኋላ ለቤተሰብ ማስረከቡን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ጥቃት አድራሹና በወቅቱ ከእሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተይዘዉ እየተመረመሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለፁት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ " በአካባቢዉ የነበረ ካሜራ ሁነቱን ሙሉ በሙሉ ሬከርድ ማድረጉ ስራችንን አቅልሏል፤ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ይተላለፋል " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ #ሰላም

#ሰላም_ከሌለ_ሁሉ_ነገር_የለም!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" ... በምድር ላይ ሰላም ካልነገሰ በቀርን መቼም ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ሰላም ዓለምን የሚገዛ ነው ፤ ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም። ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ።

ለሰላም የሚሆን ዋጋ በዓለም ላይ አይገኝም። ብርም ይሁን ፣ ወርቅም ይሁን አልማዝም ይሁን #አይመጥነውም። ለሰላም የሚሆን ዋጋ አይመጥነውም ይሄ ሁሉ።

ሰላሙን የምናመጣው እኛው ነን ፣ የምናባርረውም እኛው ነን።

ሰላም በምድር መንገስ አለበት። ሰላም በምድር ካለ ሁሉም ነገር አለ ፦
- ሀብት አለ
- ትምህርት አለ
- ስልጣኔ አለ
- ድሃ በጉልበቱ፣ ሃብታም በሀብቱ ፣ የተማረም በእውቀቱ ሀገርን ያቀናል እራሱም ይኖራል።

ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው።

ስለ ሰላም #መጸለይ ምንጊዜም አስፈላጊ ነው። ሰላም በሶስት ፊደል የተወሰነች ብትሆንም ዓለምን #የምትገዛ ሰላም ናት። ሰላም ዓለምን ይገዛል ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚስተካከለው በሰላም ስለሆነ።

ስለ ሰላም ምንጊዜም ቢሆን #ሁሉም_ኢትዮጵያዊ በያለበት ጸሎት ማድረግ አለበት፤ በጸሎት ሁሉም ነገር ይገኛልና። "

የፎቶ ባለቤት፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው + ኢጃት (አዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል - ' የአእላፋት ዝማሬ ' - በኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ℹ️ ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው #ከሁለት_ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል። የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች ፦ -…
ዛሬ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት " በሚል ወደ ኤርትራ፣ አስመራ መጓዛቸው ተሰምቷል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " በሁለቱ ወንድማማች አገራት " የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመምክር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ብሏል።

በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር ማግኘት መንገድ ይጠርጋል  የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲይ ፕሬዝዳንቱ ወደ ተተለያዩ ሀገራት መሪዎች የስልክ በመደወል ውይይት ሲያደርጉ መሰንበታቸው ተሰምቷል።

ከማንም በፊት በቅድሚያ የደወሉላቸው ለግብፁ መሪ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሲሆን ከዛ በኃላ ከኳታር ኤሚር፣ ከኡጋንዳው መሪ ፣ ከቱርክ እንዱሁም ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ እና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር መክረዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ባደረገችው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ማንም የሚጎዳ አካልና #ሀገር ፤ የተጣሰ ህግና የተሰበረም እምነት እንደሌለ አሳውቃለች።

እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር፣ የቆዳ ስፋት እና እድገት ኖሯት የባህር በር አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ፣ ያለ አንዳች ግጭት እና ጦርነት በሰጥቶ መቀበል መርህ ጥቅሟን ለማስከበር እንደምትሰራ በተደጋጋሚ ገልጻለች።

ሀገራት ከበርካታ ሺህ ኪሎሜትሮች መጥተው በዚሁ ቀጠና ቤዝ ሲመሰርቱ ጥቅማቸው ለማስከበር መሆኑን የገለፀችው ኢትዮጵያ የቀጠናው ባለቤት የሆና እጆቿን አጣጥፋ የምትቀመጥበት ምክንያት እንደሌለ ገልጻለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው " - የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ምክር ቤት የበድር መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ ሸይኽ አብዱ ያሲንን የግድያ ሁኔታ በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በምርመራ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገልጿል። ወንጀል የፈፀመውን አካል በማፈላለግ ረገድ ፖሊስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማህበረሰቡ በንቃት ጉዳዩን እንዲከታተል እና…
#ይፈለጋል #Wanted

" ... ሟች ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ፤ ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው የተባለ ግለሰብ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡ #እጁን_እንዲሰጥም ፖሊስ አሳስቧል።

ፖሊስ ተጠርጣረው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አስተላልፏል።

የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ " የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበረ ሟቹ ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል። " ሲል አሳውቋል።

መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅ ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በወንጀል የተጠረጠረ ግለሠብን መደበቅ ሆነ እንዲያመልጥ መተባበር የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት " በሚል ወደ ኤርትራ፣ አስመራ መጓዛቸው ተሰምቷል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " በሁለቱ ወንድማማች አገራት " የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመምክር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ብሏል። በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር…
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነትን ውድቅ የሚያደርግ ሕግ ፈርመው አፅድቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ሕጉ " አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እንዲሁም የግዛት አንድነታችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው " ማለታቸው ተነግሯል።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ግን የሶማሊያ መንግሥት እንቅስቃሴዎችን ውድቅ በማድረግ ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን እየገለፀች ትገኛለች።

ሶማሊያ እያቀረበች ያለው ይገባኛል ሀሰት መሆኑን ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት አመታት መቆጠራቸውን፣ የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዬጵያ ጋር የተደረገው ስምምነት (MoU) ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲተረጎም የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለው እያሳወቀች ነው።

በሌላ መረጃ ፤ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ኤርትራ፣ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል። ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተነግሯል።

@tikvahethiopia