TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ #የኢትዮጵያ እና #የሶማሌላንድ ወታደራዊ አመራሮች ውይይት አደረጉ።

ዛሬ በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተገኝቶ ውይይት አድርጎ ነበር።

በውይይቱም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ #አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

Photo Credit - FDRE Defense Force

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

የመጀመሪያ የተረክ በM-PESA አሸናፊዎቻችን የባጃጅ እና የስልክ ሽልማታቸውን ተረክበዋል! ለአሸናፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላቹ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።

የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia 

#TerekBeMPESA     
#FurtherAheadTogether
https://vm.tiktok.com/ZM6mBe9SX

ሚና ፈርኒቸር ... ከዘመኑ ጋር 🤌

ቤቶን ለማሻሻል ጊዜው አሁን ነው ‼️
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
ጅቡቲ ከ8 ቀናት በኃላ ዝምታዋን ሰብራለች።

በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከተፈመ በኃላ ስለ ቀጠናው ጉዳይ ሀገራት እና ተቋማት አቋማቸው ሲገልጹ ፣ ምክር ያሉትንም ሲለግሱ ነበር።

አብዛኞቹ ስለ ስምምነቱ በቀጥታ ባያነሱም በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለው ግንኙነት እንደሚያሳስባቸው ነው የገለጡት።

የኢትዮጵያ ጎረቤት #ጅቡቲ ደግሞ ስምምነቱ ከተፈረመ ከ8 ቀን በኃላ ዛሬ ቀጠናዊ ሁኔታን በተመለከተ አቋሟን ገልጻላች።

ስለ ስምምነቱ ያለችው አንዳች ነገር የለም።

የጅቡቲ መንግሥት ፤ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ  መካከል ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበውና በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

መግለጫው የተለየ ሀገር ስምን ሳይጠቅስ #የሁሉም የኢጋድ አባል ሀገራት ሉዓላዊነት ፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አስገንዝቧል።

NB. የጅቡቲው ፕሬዜዳንት ኢሳማኤል ኦመር ጌሌህ የወቅቱ የኢጋድ ፕሬዜዳንት ናቸው።

ጅቡቲ ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የውይይትን መንገድን እንዲመርጡና ያለው ውጥረት እንዲረግብ በመቀራረብ እንዲሰሩ ጥሪዋን አቅባለች።

ሁኔታውን በተመለከተ ውጥረት እንዲረግብ ከሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት ጋር እንደምትሰራ አረጋግጣለች።

ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ከጎረቤትነቷ ባለፈ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ ቁርኝት አላት ፤ በዓመታዊ የወደብ እና የትራንዚት አገልግሎትም ከኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።

@tikvahethiopia
#Hawassa

" የውሀ እጥረት በመከሰሰቱ  ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል " - በሀዋሳ  ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎች

" ከኦሮሚያ ክልል የሚመጣዉ ውሀ በመቋረጡ የድሀ ግብአታችን ላይ ከፍተኛ እጥረት ተከስቶብናል " -  የሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀዋሳ ከተማ በተለይም በጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም በአዲስከተማ ክፍለከተማ ስር ባሉ ቀበሌዎችና አዋሳኝ ክፍለከተሞች ከፍተኛ የውሀ እጥረት ተከስቷል ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሀ ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ዮሴፍ ዮንኩራ ፤ ችግሩ የተፈጠረዉ ከሲዳማ ክልል ውጭ በኦሮሚያ ክልል ከተቆፈረዉ የውሀ ጉድጓድ ይገኝ የነበረዉ ውሀ በመቋረጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ ስር ከቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሀ) በቅርብ ርቀት ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ጉድጓድ ተቆፍሮ የውሀ አገልግሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ግን የአካባቢው ማህበረሰብና አመራሮች ውሃውን መጠቀም አለብን በሚል ጥያቄ እና በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ውሀውን  መጠቀም አልተቻለም ብለዋል።

አቶ ዮሴፍ አክለዉም ፤ የዉሀ ማስተላለፊያ መስመሮች በግለሰቦች መወጋታቸዉንና ለብልሽት መዳረጋቸዉን ተከትሎም ጥገና ማድረግ አለመቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ከተማዉ እስከ ሀያ በመቶ የውሀ አጥረት መግጠሙን ፤ የተጠቀሱት ክፍለከተሞችና የጋራ መኖሪያ ቤቶችም ለችግር መጋለጣቸዉን አስረድተዋል።

የአካባቢው አስተዳደር ለውሀ ጉድጓዱ የተፈረመዉን ብድር ከፍሎ ውሀዉን እንዲጠቀም አለበለዚያም የራሱን ጉድጓድ እንዲያስቆፍር ቢጠየቅም አለመስማማቱን የሚጠቅሱት ዳይሬክተሩ ችግሩን የዉሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር ይቀርፈዋል ብለዉ እንደሚያምኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃውን የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፃፈ።

ፓርቲው በዚህ ደብዳቤው ፤ " የፓርቲ አባል ያልሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች በብልፅግና ፓርቲ ስልጠና እንዲሳተፉ የሚደረግበት አሰራር እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

ነእፓ ፤ #የመንግስት እና #የፓርቲ መደበላለቅ በለውጡ ማግስት መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን በተለይ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ብሏል።

ከቅርብ ወራት ጀምሮ ገዢው ፓርቲ እያካሄደ ባለው የአባላት ስልጠና፣ የፓርቲው አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች (Public servants) የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው ሲል አስረድቷል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ በተለያየ መንገድ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል።

ይባስ ብሎ በየአካባቢው እየተካሄዱ ያሉ ስልጠናዎች ፦
- አበል፣
- ትራንስፖርት፣
- ሆቴል እና ሌሎች የስልጠና ወጪዎች የሚሸፈኑት #በመንግስት_በጀት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ብሏል።

በመሆኑም የፓርቲ አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች የገዢውን ፓርቲ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ ህገ መንግስቱን እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ስርአት አዋጃ ቁጥር 1162/2011 የሚቃረን በመሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ድርጊቱ ይቆም ዘንድ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድም አሳስቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት፤ ገዢው ፓርቲ የስልጠናና ሌሎች ድርጅታዊ እንቅስቃሴውን በመንግስት ሀብት የሚሸፍንበት አሰራር ህግ እና ስርአትን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የፖለቲካ ሜዳውን የሚያዛንፍ በመሆኑ፣ ድርጊቱ ይታረም ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በተለይም ፦
- የምርጫ ቦርድ፣
- የገንዘብ ሚንስቴር
- የክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮዎች፣
- በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤቶች አዋጁን በማስከበር ገዢው ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሩን ከመንግስት መዋቅር ለይቶ እንዲሰራ ኋላፈነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ወደ አፖሎ አካውንት አንድ ሰው ባስመዘገቡ ቁጥር የ50 ብር ጉርሻ!

ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር  በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ መክፈል ጀምሯል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ተማሪዎች አወዳድሮ እየወሰደ ነው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ማለትም
1. ዩኒቨርሲቲ
2. ኮሌጅ
3. ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ናቸው

የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን በቀላሉ ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡
https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent

የ50 ብር ኮሚሽን አግኙ!
ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
በሃገር ልዩ ወግ እና ባህል ተውቦ፤
በደማቅ አብሮነት ታጅቦ፤
በደስታ የሚያከብሩት የልደት በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን!

እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ልዩ የገና በዓል የሞባይል ጥቅሎች በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር ወይም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻት ቦት እንዲሁም *999# ለራስዎ እየገዙ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ የበዓል መልካም ምኞትዎን ያድርሱ!

መልካም የገና በዓል!

#Ethiotelecom #telebirr #HappyHolidays
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል። ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው። ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት…
#Update

በአማራ ክልል የሚገኙ ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች መግቢያ ቀንን ይፋ አድርገዋል።

ከቀናት በፊት ባህር ዳር ፣ ወልዲያ ፣ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የመግቢያ ቀን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ማስታወሻ፦ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/84044

ከተጠቀሱት ዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ፦
* እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፣
* ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
* ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
* ወሎ ጥሪ አድርገዋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፤ የነባር መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 25 እና 26 መሆኑን ገልጿል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ትምህርት ወስደው ያለፉ እንዲሁም በዚሁ ፕሮግራም ለመማር የተመደቡ ተማሪዎች መግቢያ የካቲት 7 እና 8/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ማለትም የ2ኛ፣ 3ኛ እና 5ኛ ዓመት ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ጥር 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን ይፋ አድርጓል።

በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የማለፊያ ውጤት ያመጡ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የአንደኛ ዓመት እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ በቅርቡ ጥሪ ይደረግላቸዋል ብሏል።

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ፤  የ3ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዘባ ከጥር 16-17/2016 ዓ/ም ይካሄዳል ብሏል።

የ2ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዘገባ ከጥር 23-24/2016 ዓ/ም ነው ብሏል።

የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላቸው ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ ከየካቲት 7-8/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ አዲስ ገቢ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎችና በ2016 በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 7-8/2016 ዓ.ም መሆኑን ይፋ አድርጓል።

የሁሉም ነባር የተከታታይ ፕሮግራም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር እንዲሁም የሁሉም የመደበኛ እና ተከታታይ ድህረ-ምረቃ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 04-05/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የነባር ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ አዲስ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትለው ያለፉ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ጊዜ ጥር 7 እና 8/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በሌላ በኩል፣ በ2016 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

እስካሁን ለነባር መደበኛ ተውማሪዎች ጥሪ ያደረጉ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የትኞቹ ናቸው ?

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
ወሎ ዩኒቨርስቲ

እስካሁን ይፋዊ ጥሪ ያላቀረቡ ጎንደር፣ ደብረብርሃን እና መቅደላአምባ ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity